TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት #የአገልግሎት_ክፍያ በወቅቱ ካልከፈሉ ደንበኞች 340 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ። የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ አገልግሎቱ ከዚህ በፊት ያልከተፈሉ ውዝፍ ገንዘቦችን እየሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል። እስከአሁን ባለው ጊዜም 340 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ከደንበኞች ያልተሰበሰበ ውዝፍ ክፍያ መኖሩን ገልፀዋል። መስሪያ ቤቱ ውዝፍ እዳ ያለባቸውን ማስከፈል ሳይጀምር በአጠቃላይ 700 ሚሊየን ብር እንደነበር እና አሁን ላይ ግን ግማሹን ማስከፈል እንደተቻለ ነው የተገለጸው።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM