TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ "

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች#በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።

በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦
👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣
👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ሚኒስትሮች፣
👉 ሚኒስትር ዴኤታዎች፣
👉 ኮሚሽነሮች፣
👉 ምክትል ኮሚሽነሮች፣
👉 ዋና ዳይሬክተሮች፣
👉 ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም #ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ #ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር  የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ የሥራ ክፍሎች በየተቋማቸው ያለውን የሀብት ምዝገባ መረጃን ለማንኛውም መረጃ ጠያቂ እንዲሰጡ አለማድረግ፣ ወይም ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር የሕገ መንግሥቱን የግልጽነትና ተጠያቂነት ድንጋጌንና የሀብት ማስመዝገቢያና ማሳወቂያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ጽንሰ ሐሳብና መሠረታዊ ዓላማን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መረጃ ያለመስጠት ድርጊት ለተጀመረው የሙስና ትግል ምንም ዓይነት አበርክቶ የሌለው በመሆኑ የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድ ተቋሙ ጠይቋል፡፡

(የኢ/ሕ/ዕ/ጠ/ተቋም ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ ከላይ ተይይዟል)

#Reporter
#EthiopiaInstitutionoftheOmbudsman

@tikvahethiopia