TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATAYE

"የአጣዬ ቅዳሜ ገበያ ተበትኗል፤ ነዋሪውም #እየተረበሸ ነው" አቶ ጌታቸው የሺጥላ

የታጠቁ አካላት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተኩስ ከፍተው አካባቢውን ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከተራራ ሥፍራ በመሆን ወደ አጣዬ ከተማ በመተኮስ የአካባቢውን ሰላም እየረበሹ መሆኑን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው የሽጥላ ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው እንዳስታወቁት ከተራራ ወደ ከተማዋው በተከፈተው ተኩስ ስጋት የአጣዬ ቅዳሜ ገበያ ተበትኗል፤ ነዋሪውም እየተረበሸ ነው።
የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት ሕዝቡን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነም ኃላፊው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-05-2

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATAYE

"...እንደገና የተኩስ ልውውጥ ተጀምሯል!" የአጣዬ ከተማ ነዋሪ

ኤፍራታና ግድም አካባቢ ያለውን የፀጥታ ችግር መንግሥት በአስቸኳይ ሊቆጣጠረው ይገባል ሲሉ ነዋሪዎች ጠየቁ። በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ አካባቢ ከትናንት ጀምሮ የፀጥታ ችግር መከሰቱን ይታወቃል፡፡ የፀጥታ መደፍረሱ ትናንት በቁጥጥር ሥር የዋለና ዛሬ ረፋድም አንጻራዊ መረጋጋት እንደነበረ የተገለጸ ቢሆንም እንደገና የተኩስ ልውውጥ መጀመሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አስተያየታቸውን ለአብመድ የሰጡ አንድ የአጣዬ ነዋሪም ተከታዩን ብለዋል፦ ‹‹ከቤታችን አልወጣንም፤ ከባድ ተኩስ እየተሰማ ነው፤ ማን እንደሚተኩስ አናውቅም፤ መከላከያ፣ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል አሉ፤ የታጠቁ ኃይሎችም በተራሮች አካባቢ አሉ፤ ከባድ መሣሪያ ጭምር እየተተኮሰ ነው›› በተጨማሪም አስተያየት ሰጪው ሱኒ መውጫ እና አቡበከር ተራራ አካባቢ እየተተኮሰ መሆኑን ያስታወቁት ነዋሪው ከትናንት ጀምሮ ከባድ ስጋት ውስጥ እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-06

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATAYE

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወቃል። መንግስት “ለግጭቱ ተጠያቂው ኦነግ ነው” ሲል ገልፆአል።

ኦነግ በበኩሉ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል፦

“አጣዬ #ኦነግ ምን ሊሰራ #ይመጣል፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት እንደሌለው ብዙ ጊዜ መላልሰን ተናግረናል በመሆኑም ስሞታው #ውሸት ነው” የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ

Via ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATAYE

በአጣዬ ከተማ አንድ ኮንቲነር ልባሽ ጨርቅና ሺሻ በሐሰተኛ ሰነድ በተሽከርካሪ ጭኖ ሲያጓጉዙ የነበረ ግለሰብ በተጠርጣሪነት መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ።

በቅርንጫፉ የህግ ተገዥነት ተወካይ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ እንድሪስ መሃመድ እንደገለጹት ግለሰቡ የተያዘው ጥቅምት 21/2012ዓ.ም. ነው።

የተያዘው ተጠርጣሪው ግለሰብ ኮድ 3-25275 ኢት የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ህገ ወጥ የሆነው እቃ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲያጓጉዝ ነበር ሾፌር መሆኑን አመልክተዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብ በሰጠው ጥቆማ ተሽከርካሪ ሲፈተሽ ኮንቲነሩ ሙሉውን ልባሽ ጨርቅና የሚጨሰው ሺሻ ጭኖ መገኘቱን አስረድተዋል።

ሾፌሩ በፖሊስ ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ያመለከቱት አቶ እንድሪስ “በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ስም የተዘጋጀ ሐሰተኛ የይለፍ ሰነድም ይዞ ተገኝቷል “ብለዋል፡፡

የእቃው ብዛትና ግምት ቆጠራው ሲጠናቀቅ እንደሚገጽና ህብረተሰቡ ህገ ወጦችን ለመከላከል የሚያደርገው ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ከሳምንት በፊትም 340 ሺህ ብር ግምት ያለው ህገ ወጥ የግንባታ እቃ መያዙም ተመልክቷል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia