TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል።

የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላት #ማረጋገጥ ችሏል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት #በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ኘሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደትም እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስመቅጧል።

2ኛ. በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 /2015 እስከ ሐምሌ 13 /2015 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።

3ኛ. የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

በተጨማሪም እንደ አገር ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር ከ2016 ጀምሮ ለማስተካከል ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚሁ ማዕቀፍ አንዲያስተካክሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል።

ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የተለያዩ #ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እየሰሙ አለመረጋጋት ውስጥ መግባታቸውን ሲገልፁልን ነበር ፤ በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር / የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሚሰጡትን ትክክለኛ መረጃ #ብቻ እንድትከታተሉ ፤ በቀረው አጭር ጊዜም ዝግጅታችሁን ታጠናክሩ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል #ትክክለኝነቱን ያረጋገጠው ነው።)

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT