TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የሱዳንን አብዮት የመሩት ሴቶች ናቸው" - የአፍሪካ ህብረት ልዑክ
.
.
የሱዳን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የመረጧቸውን የካቢኔ አባላት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

እጩዎቹን ለማጥናት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት በማስፈለጉ እነርሱን ይፋ የማድረጊያው ጊዜ ዘግይቷል ነው የተባለው፡፡

በሱዳን ወታደራዊ እና ተቃዋሚ ቡድኖች በተፈረመው የአገሪቱ ህገ-መንግስት ማሻሻያ አዋጅ መሠረት 40 ከመቶ የሚሆነው የሚኒስትሮች እና የመንግስት የስራ ቦታዎች በሴቶች አንደሚያዙ ነው የተገለፀው፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሴቶች የሰላምና ደህንነት ልዩ መልዕክተኛ #ቢኒታ_ዲዩፕ በካርቱም የሚገኙ ሲሆን መንግስት 40 ከመቶ የሚሆኑ ሴቶችን በካቢኔው በሚያካትትበት አግባብ ላይ ከሱዳን ሴት ፖለቲከኞች ጋር ተወያይተዋል፡፡ "አብዮቱን የመሩት ሴቶች ናቸው" ሲሉ መልዕክተኛዋ ለቢቢሲ ኒውስዴይ ተናግረዋል፡፡

ሴቶቹ ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መገናኘታቸውን የገለፁት መዝ ዲዩፕ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

"እሷ አጋር መሆኗን አረጋግጠዋል፤ ስለ ሥርዓተ-ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን ስለማብቃት ያውቃሉ፤ ከወታደራዊው ኃይል ጋር ለመደራደር የሚያስችል ኃይልም ያላቸው ይመስለናል" ብለዋል መዝ ዲዩፕ፡፡

ምንጭ᎓- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን ሸገር ራድዮ ዘግቧል። ስብሰባው የተጠራው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ባጸደቀው የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና አሠራር አዋጅ ላይ ለመነጋገር ነው ተብሏል። በርካታ የጋራ ቃል ኪዳን ስምምነቱን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ የጸደቀው ቀደም ሲል ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ከተስማማንበት መንፈስ ውጭ ነው በማለት እንደሚቃወሙት በጋራ ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

Via #ShegerFM/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴፒ ወጣቶች...

"እኛ የቴፒ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን የወጣቶች ህብረት የከተማችንን መልካም ገፅታ ከመገንባት አንፃር በራስ ተነሳሽነትና በበጎ ፈቃደኝነት ሌሎች ወገኖችን በማስተባበር ዛሬ ጥዋት ላይ " አከባቢያችን የአስተሳሰባችን ውጤት ነው ! ስለዚህ ቆሻሻዎችን በማስወገድ ከተማችንን እናስውብ፣ ጤናችንንም ጥንጠብ በሚል መሪ ሀሳብ ከተማችንን በማፅዳትና ቆሻሻዎችን በማስወገድ የፅዳት ዘመቻ ያደረግን ሲሆን ከዚህም በተጨመሪ የችግኝ ተከላም አድርገናል። በዚህ የበጎ አድራጎት ስራ ላይም የተለያየ እምነት ተከታዮች የሆኑ ሙስሊሞችና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑ ወገኖቻችንም አብረውን ሲሰሩ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እኛ የቴፒ ወንጌላዊያን ክርስቲያን ወጣቶች በከተማችን ለሚገኙ ከ2000ሺ በላይ ለሆኑ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የሚሆን ደብተርና እስኪቢርቶ እንደመሁም የተለያዩ የትም/ት ቁሳቁሶችን እያሰባሰብን ነው ዛሬ ከሰዓታት ብኀላ ደግሞ የደም ልገሳ እናደርጋለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ደም በመለገስ የእናቶችን ሞት እንቀንስ"

በሐረሪ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ የአመራር ስልጠና ላይ ያሉሁት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና ማረሚያ ኮሚሽን አባላት ደም በመለገስ የእናቶችን ሞት እንቀንስ በሚል መነሳሳት ደም ልገሳ አድርገዋል።

Via #ADUU/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የአንበሳ መንጋ በሰውና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው!

በጋምቤላ ክልል አበቦ ወረዳ አንበሶች በሰውና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን የወረዳው ፖሊስ ገለፀ።

በጋምቤላ ክልል ፔርፔንጎ ወረዳ ቁጥሩ ከአምስት በላይ የሆነው የአንበሳ መንጋ በተለያዩ ቀበሌዎች በመዘዋወር ሰዎችንና የቤት እንስሳትን እየተተናኮሉ  ማስቸገራቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡጁሉ  ታታ ይናገራሉ።

በወረዳው ፔርፔንጎ ቀበሌ ሀምሌ 21 ቀን 2011  ዓም ምሽት አካባቢ ሶስት አንበሶች በድንገት መጥተው በአንድ ባለሀብት እርሻ ስራ የነበሩ  በርካታ ሰዎችን በማሳደድ አንዱን ግለሰብ  ይዘው በአሰቃቂ ሁኔታ በልተውታል።

በወረዳው በተለይም መንደር 11እና12 በተባሉ ቀበሌዎች አንበሳዎቹ በተደጋጋሚ ጊዜ በቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱ መቆየታቸውን ኢንስፔክተር ኡጁሉ ያስታውሳሉ።

እንደ ወረዳው ነዋሪዎች አገላለፅ ከሆነ ደግሞ ካለፈው አመት ጀምሮ ከ300 በላይ የቤት እንሰሳት በአንበሶቹ ተበልተዋል። አንበሶቹ በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትሉ በማሰብ የፖሊስ አባላቱን በጥበቃ ላይ እንዲሰማሩ ማድረጉን ኢንስፔክተሩ ይናገራሉ።

ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከልም ከኢትዮጵያ የዱር እንሳስት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የጋምቤላ ብሄራዊ ፖርክ ጽህፈትቤት ጋርበ መነጋገር ላይ እንደሚገኙ አሰታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-29-5
የሰላም ሚኒስቴር ለወጣቶች ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ የስነ ጽሑፍ ወርክሾፕ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የስነ ጽሑፍ ችሎታና ፍላጎት ያላችሁ በ0912632913 ደውላችሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን።

የሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ሚኒስቴር ለወጣቶች ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ የቪዲዮግራፊና ፎቶግራፊ ወርክሾፕ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የችሎታውና ለቪዲዮ/ፎቶ የተሟላ መሣሪያ ያላችሁ በ0929009002 ደውላችሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን።

የሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በድህነት ተምራ 3.96 የመመረቂያ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ!

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ላይ የመማር አቅም አጥተው የነበሩና በሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ለመርዳት በተቋቋመ “የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት” ድርጅት ታግዛ የፍተኛ ትምሕርቷን ያጠናቀቀችው መሰረት መራዊ “ስለ ትምሕርቴ ብቻ በማሰብ ለዚህ በቅቻለሁ” ትላለች።

VOA ወጣቷን አንጋግሯታል ከላይ የተያያዘው የድምፅ ፋይል ከፍተው ያድምጡ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2019/20 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሆኗል። #TIKVAH_SPORT

የስፖርት ገፃችንን ጎብኙ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
ቤተክርስቲያኗ በነፃ የመማር እድልን ለመስጠት ቃል ገባች!

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ውጤት ከ8ኛ ወደ ዘጠነኛ ለሚያልፉና ከፍለው መማር ለማይችሉ በከተማዋ ለሚገኙ ተማሪዎች በነፃ የመማር እድልን ለመስጠት ቃል ገባች።

የነፃ የትምህርት እድሉ በቤተክርስያኒቷ ስር በሚተዳደሩ ት/ቤቶች የሚሰጥ ይሆናል። ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ሱራፌል ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያናት ሊቀጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ኢ/ር ታከለ ኡማ ቫቲካንን እንዲጎበኙ የላኩትን ጥሪ ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ለከንቲባው አቅርበዋል። ኢ/ር ታከለ በፖፕ ፍራንሲስ የቀረበላቸውን የቫቲካን ጉብኝት ጥሪ በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ላይ እየሰራ ያለውን ስራ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደምትደግፈው ካርዲናል ብርሀነ እየሱስ ሱራፌል ተናግረዋል። በመጨረሻም ካርዲናሉ ከከተማ ልማት ጋር የተገናኙ መፅሐፍትን በስጦታ ለኢ/ር ታከለ ኡማ አበርክተዋል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ #ግጭቶችና አለመግባባቶችን ለመከላከልና ይቅር መባባልን ለማጎልበት የሠላም ግንባታ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ፡፡ የጉባኤው ከፍተኛ አመራሮች በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ከተማና ሁላ ወረዳ ተከስቶ በነበረው ሁከት የተጎዱ ዜጎችን ጎብኝተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012

ከመቶ ሀምሳ ዓመታት በሀኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ሊከበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢሬቻ በዓል እንደ ትልቅ እድል ሊታይ ይገባል እንጂ የስጋት ምንጭ መሆን እንደሌለበት የገዳ አባቶች አስገንዝበዋል፡፡

#OBN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የASTU/AASTU የመመዝገቢያ መስፈርት!

ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ!

የምዝገባ ጊዜ፡- ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 03

የምዝገባ ቦታ፦

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.aastu.edu.et,  www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡-

በማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲዎቹ ዌብሳይት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-

በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

•ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣

•ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡-

www.aastu.edu.etwww.astu.edu.et
እንደአመቺነቱም በስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

•አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም የመሰናዶ (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡

•ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

•አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ዋጋ ስንት ነው?

#የባህርዳር_ወጣቶች ያዘጋጁት የምዕራፍ ሁለት የጎዳና ላይ የሰላም ጉባኤ ተካሂዷል። #PEACE #ሰላም #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አረንጓዴ ጎርፍ በራባት!

እንኳን ደስ አለን!

1. Tsehay Gemechu ETH 31:56.92
2. Zeneiba Yimer ETH 31:57.95
3. Dera Dida ETH 31:58.78

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች በቪዲዮ ይመልከቱ👆

እንኳን ደስ አለን!

ቪድዮ፦ African Athletics United/Bezuayhu Wagaw/

TIKVAH ስፖርት👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!

"ከሰሞኑን በሞባይል ካርድ ላይ Fake መስራት ተጀምሯል። 50 ወይም 100 ብር ካርድ ብለክ ገዝተህ የ50 ብሩ ካርድ ተፍቆ ላዩ ላይ የ5 ብር ወይም የ10 ብር ሚስጥር ቁጥር አድርገውበት እሱን ሸፍነው ነው የሚሸጡት። ለምሳሌ እኔ 50 ብር ገዝቼ ስሞላው የ5 ብር ነው። ሰዎች ካርድ ሲገዙ አጠገባቸው ሆነው ይሙሉ። በተጨማሪ ፎቶው ላይ እንደሚታየው ካርድ ቁጥሩ አካባቢ ምንም አይነት የተፋቀ ነገር እንደሌለው ያረጋግጡ" ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#2 እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ተፍቀው ጥቅም ላይ በዋሉ የሞባይል ካርዶች ላይ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በሚፋቀው ቦታ ላይ ተመሳሳይ ቀለም ወይም ስቲከር በመቀባትና በመለጠፍ ጥቅም ላይ ካልዋሉ አዳዲስ ካርዶች ጋር በማመሳሰል ወደ ገበያ በማሰራጨት ደንበኞቻችንን እያጭበረበሩ መሆኑን ደርሰንበታል። ስለሆነም ክቡራትና ክቡራን ደንበኞቻችን የሞባይል ካርዶችን ስትገዙ በሚፋቀው የሚስጥራዊ ቁጥር ቦታ ከተለመደው የተለየ ቅብ ወይም ተለጣፊ ነገሮች አለመኖራቸውን አስተውላችሁ እንድትገዙ በተቻለ መጠን ካርዱን ከገዛችሁበት ቦታ ወዲያውኑ እንድትሞሉ እየጠየቅን ሂሳቡ በትክክል ከተሞላ በኃላ ካርዱን በመቅደድ በተገቢው የቆሻሻ መጣያ ውስጥ በመጣል ለአጭበርባሪዎች ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እንጠይቃለን።

#ETHI_TELECOM #ኢትዮ_ቴሌኮም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ጥቂት ሰዎች በሚረጩት የተሳሳተ መረጃ እንቅፋት እየገጠመው መምጣቱን የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልጿል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በክልሉ ህገ ወጥ ስደትን ለመከላከል የተደረገው ጥረትና የተገኘው ውጤት የሚገመግምና በአዲሱ ዓመት የዘርፉ እቅድ ዙሪያ ትናንት በማይጨው ከተማ ውይይት ተካሔዷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
”ኢመደበኛ አደረጃጀቶች #ሥርዓት ካልተበጀላቸው ለአገር ከፍተኛ አደጋ ይሆናሉ"- ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
.
.
የአገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ በየአካባቢው ያሉ በግለሰብ የሚመሩ የወጣት ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ተቋማዊ እንዲሆኑ ስርዓት ካልተበጀላቸው ለአገር ከፍተኛ አደጋ እንደሚሆኑ ተጠቆመ። የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ መንግስት በቅንነት ሽማግሌዎችን እና የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን እያቀረበ ነው። አንዳንድ የምሁራን ማህበር እየተባሉ ኢመደበኛ በሆነ መልኩ የሚሳተፉ አሉ። በተለያዩ አካባቢዎች ሌሎችም መደበኛ ያልሆኑ የወጣት አደረጃጀቶች አሉ። ወደፊትም ሌሎች ሊፈጠሩ ይችላሉ።

ነገር ግን ከማናቸውም አደረጃጀቶች ጀርባ የግለሰቦች ፍላጎቶች መኖራቸው መዘንጋት የለበትም። ያንን መዘወር የሚፈልጉ የፖለቲካ ሃይሎች ይኖራሉ። እነዚህ አደረጃጀቶች ከጠነከሩ ማዕከላዊ መንግስቱ ያዳክማሉ።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ-ጃፓን ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ!

በዮኮሃማ ጃፓን እየተካሄደ ካለው 7ኛው የቲካድ ስብሰባ ጎን ለጎን ዛሬ ሁለተኛው የኢትዬ-ጃፓን የቢዝነስ ፎረምና ኤግዝቢሽን ተካሂዷል። በዚሁ ፎረም 180 የጃፓን ባለሃብቶች እንዲሁም 43 የኢትዮጵያ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን እንዲሁም የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) ፕሬዚዳንት ንግግር አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ የጃፓን ባለሃብቶችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናን አንስተው ፤ ባለሃብቶቹ ይህንን ምቹ ሁኔታ እንዲጠቀሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን በበኩላቸው ቶኪዮ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ የጃፓን ባለሃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከተለያዩ ጃፓን ኩባንያዎችና ተቋማት ለሚደረግላቸው ድጋፍ በማመስገን ኤምባሲው ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ያለውን አመቺ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲጠቀሙ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነፃ የህክምና አገልግሎት!

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል “ጳጉሜንን ለጤና” በሚል መርሀ ግብር ከአዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ለተወጣጡ አንድ ሺህ ዜጎች ነጻ የምርመራና የህክምና ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተጠቆመ።ማዕከሉ አስረኛ ዓመቱን ‹‹አስር መልካም ነገሮችን በመስራት›› ሊያከብር ነው።

የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ኃይሉ የማዕከሉን አስረኛ ዓመት የበጎ አድራጎት መርሀ ግብሮች ዝርዝር አስመልክተው ትናንት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ማዕከሉ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ያለውን የጤና ክፍተት ለመሙላት “ጳጉሜንን ለጤና” በሚል መርሃ ግብር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለተውጣጡ አንድ ሺህ ዜጎች ከጳጉሜን 1 እስከ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ነጻ የምርመራና የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ምርመራው አጠቃላይ የውስጥ ደዌን ጨምሮ የአንገት፣ የጉበት፣ የካንሰር፣ የጨጓራ፣ የልብና መሰል የጤና እክሎችን የተመለከተ መሆኑን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia