TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ሳዑዲ_አረቢያ ፦ ሳዑዲ አረቢያ የሃጅ ተጓዦችን እየተቀበለች ትገኛለች። ከቀናት በፊት የመጀመሪያው የሃጅ ተጓዦች ቡድን ከኢንዶኔዥያ ወደ ሳዑዲ መግባቱ ይታወሳል። ዛሬ ባገኘነው መረጃ እስከ ትላንት እሁድ ድረስ ከተለያዩ ሀገራት ለሃጅ ጉዞ ሳዑዲ የገቡ ተጓዦች 955 ደርሰዋል። ሳዑዲ አረቢያ ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ 1 ሚሊዮን የሃጅ ተጓዦችን እንደምታስተናግድ ይታወቃል።

#ጀርመን ፦ የጀርመኑ መኪና አምራች ኩባንያ መርሴዲስ-ቤንዝ 1 ሚሊዮን ገደማ አሮጌ መኪናዎችን ለጥገና ጠርቷል። ኩባንያው እኚህ መኪናዎች ፍሬናቸው ችግር አለባቸውና ጠግኜ ልመልስላችሁ ብሏል። ኩባንያው መኪኖቹ ከፍተኛ በሆነ ዝገት ምክንያት የፍሬን ሰርዓታቸው ተገቢውን ሥራ ላይሰራ ይችላል ብሏል። ጀርመን ያሉ 70 ሺህ መኪናዎችን ጨምሮ ከ993 ሺህ በላይ መኪናዎች መጠገን አለባቸው።

#UK ፦ ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመርያ ጊዜ ኤም 270 የተባሉ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ልትሰጥ ነው። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ ሮኬት ማስወንጨፍያ መሣሪያዎች መቼ እና በምን ያህል መጠን ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አልገለጸችም።

#ሩስያ ፦ የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ሀገሪቱ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልገሳ እንድታቆም ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርሰው ጥቃት መጠኑ እየሰፋ እንደሚመጣ ገልፀዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ዘመናዊ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሲስተምን ወደ ዩክሬን ልካለች። አሜሪካ መሣሪያውን ብትሰጥም ዩክሬን ይህን መሣሪያ ወደ ሩሲያ ግዛት እንዳትተኩስ አሳስባ ነው።

#ቢቢሲ #ሳዑዲጋዜቴ #ኤፒ

@tikvahethiopia