TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#SecurityAlert www.tikvahethiopia.net በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የፀጥታ እና የደህንነት ችግር መኖሩን እያሳወቁን ይገኛሉ። ታጣቂዎች በሰውና በንብረት ላይ ጥቃት እያደረሱ እንደሆነም ገልፀውልናል። ጉዳዩ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግም አባላቶቻችን ጥሪ አቅርበዋል። በየአካባቢው ያሉ የፀጥታ…
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "መተከል ዞን" ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በተፈፀመው ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች መቁሰላቸውን ፣ ንብረት መውደሙን የቲክቫህ አባላት በፎቶ አስደግፈው አሳውቀዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን የምንለዋወጥ ይሆናል።

www.tikvahethiopia.net ላይ በየአካባቢያቹ ያለውን ማንኛውም የፀጥታና የደህንነት ስጋት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል።

እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦

• አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

• አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

• አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

• አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

• አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

#BenishangulGumuz #MetekelZone

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል። እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦ • አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ • አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ…
#Metekel

ዛሬ ጥዋት 2 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ግዢ እና ንብረት ማስወገድ ዋና ዳይሬክተር ገመቹ አመንቴ እንዲሁም የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አድማሱ ሞርካ ናቸው።

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ የተፈጠው ችግር ከተከሰተ በኃላ እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች #እጃቸው_አለበት ተብለው ተጠርጥረው ነው የታሰሩት።

አመራሮቹ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

በቀጣይም ከህብረተሰቡ በሚሰጥ ጥቆማ ለችግሩ መባባስ ድርሻ አላቸው የተባሉ የትኛውም የቤጉ ክልል አመራር ሆነ የፀጥታ አካል ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድበታል ብሏል ክልሉ።

በትላንትናው ዕለት አምስት የክልሉ አመራሮች በቀጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Metekel

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ.ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መሆኑን የቡለን ወረዳው ኮሙኑኬሽን አሳውቋል።

በጥቃት ፈጻሚዎቹ በሰዓታት ውስጥ በተፈጸመው ጭፍጨፋ በቀበሌው ውስጥ ነዋሪ ከሆኑት ሰዎች መካከል 207ቱ በጥቃቱ መገደላቸውንና ሥርዓተ ቀብራቸው ትናንት፣ ሐሙስ መፈፀሙ ተገልጿል።

በተፈጸመው የጅምላ ጥቃት የተገደሉት የሦስት የተለያዩ እምነት ተከታዮች ቢሆኑም ለይቶ የተናጠል ቀብር ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ በጅምላ እንዲቀበሩ መወሰኑ ተሰምቷል። (BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በከፋ ችግር ውስጥ ያሉ የቡለን ወረዳ ተፈናቃዮች ! በቡለን ወረዳ "በኩጂ ቀበሌ" በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቻችን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ እየተናገሩ ነው። የቡለን ወረዳ አስተዳደር ለዜጎቻችን አስቸኳይ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ በማድረግ ወገንን እንታደግ ሲል ጥሪ አቅርቧል። እስካሁን ለተፈናቃዮች ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች ምንም የተላከ የምግብ ድጋፍ የለም። መንግስትም…
#Metekel

በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው።

• ስንዴ 875 ኩንታል፣
• ዱቄት 1751 ኩንታል ፣
• ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት 7 የሚደርሱ መኪናዎች ድጋፉን ጭነው ወደ ቦታው አቅንተዋል።

ከሰሞኑ በቡለን ወረዳ በተፈፀመው የንፁሃን ጥቃት 35 ሺህ ዜጎቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በቡለን ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።

በአጠቃላይ በመተከል ዞን 56ሺ የሚደርሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

[በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን]
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው። • ስንዴ 875 ኩንታል፣ • ዱቄት 1751 ኩንታል ፣ • ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።…
#Metekel

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የፌዴራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ያደረገው ድጋፍ አየተሠራጨ ይገኛል።

ድጋፉ በቡለን ወረዳ ተፈናቅለው ቡለን ወረዳ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሠራጨ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ከ2 ሺህ 180 ኩንታል በላይ የስንዴ ፣ የበቆሎ ፣ የፋፋ ዱቄት በቡለን ወረዳ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በመድረስ ላይ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

ሌፍተናንት ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በጠ/ሚሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን አስታውቀዋል።

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፣ የንጹሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት እና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሌፍተናንት ጄኔራሉ ተናግረዋል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Metekel

በመተከል ዞን ከ97 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ከ58 ሺ በላይ ዜጎች ግልገል በለሰ ከተማ ይገኛሉ ፤ 39 ሺህ 679 ተፈናቃዮች በአማራ ክልል አዊ ብሔርስብ አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ።

ዜጎች ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ ያተደረገ ድጋፍ ፦

• በግልገል በለሰ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ33 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ ፣ 4 ሺ 38 ኩንታል ዓልሚ ምግብ እና 187 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

• አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ሺህ 404 ኩንታል ስንዴ እና 10 ሺህ 316 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ለአብመድ አሳውቋል። #MinistryOfPeace

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Metekel

በድባጤ 'ዚጊ ቀበሌ' ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ንፁሃን ሲገደሉ አንድ ሰው ቆስሏል።

ጥቃቱ በትላንትናው ዕለት ማለዳ ላይ እንደተፈፀመ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።

የሟቾች የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ አንደኛው ባለትዳር እና 5 ልጆች አባት እንደሆኑ ወንድማቸው ትላንት ምሽት በተሰራጨ መደበኛው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ሲናግሩ ተደምጠዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ ጥቃቱን አረጋግጠዋል ፥ እሳቸውም በድባጤ ወረዳ በዚጊ ቀበሌ ወደ ማሳቸው በሚሄዱ 3 ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ 2ቱ መገደላቸውን አንደኛው መቁሰሉን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ትላንት የመተከል ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር በዞኑ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT