#update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር በየተቋማቱ የአካዳሚክ ነፃነት ሊኖር እንደሚገባ ምሁራን አሳሰቡ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከዚህ በኋላ ሁሉም አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንዳሉት፤ መንግስት በተማሪዎች ህብረት ስም ለፖለቲካ ጥቅም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት።
በዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የተማሪዎች ህብረት የሚባሉ ማህበራት በቡድን ተድራጅተው ተማሪዎችን እርስ በእርስ ሲያጋጩ እንጂ መፍትሄ ሲያመጡ አላየንም ብለዋል ፕሮፌሰሩ። “በዩኒቨርሲቲዎች ሰላም ስለመደፍረሱ መስማት ያሳፍራል” ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ መንግስትም ለተማሪዎች የአካዳሚክ ነጻነት ሊሰጣቸው ይገባል ነው ያሉት።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በአልሸባብ ላይ ጥቃት መፈፀሟን አሜሪካ ገለፀች!
ዛሬ በተካሄደ ድንገተኛ የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂ ህይወት ማለፉን አሜሪካ ገልፃለች። በአፍሪካ የአሜሪካ የጦር አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዊሊያም ጌለር እንዳስታወቁት ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሊያ የመንግስት ወታደሮች ጋር በጥምረት ነው። በጥቃቱ በንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት አለመድረሱንም የጦር አዛዡ አስታውቀዋል። በተከታታይ እየተፈፀመበት ባለው ጥቃት የተነሳ የአልሸባብ ነፃ እንቅስቃሴ መገታቱንም ተናግረዋል።
ዛሬ በሶማሊያ ቁንያ ባሮው በተባለ አካባቢ በተፈፀመ የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂ ህይወት ማለፉንም ገልፀዋል። አሁን ላይ ከአል ቃይዳ ጋር ትሥሥር ያለው አልሸባብም ሆነ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች አቅም እየተዳከመ እንደሆነም ነው የተዘገበው። ባለፈው ሳምንት በሶማሊያ ታችኛው የሸበሌ ቀጣና አልሸባብ በመንግስት ወታደሮች መጠለያ ላይ በወሰደው እርምጃ 50 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን፤ ለዚህም ኃላፊነት እንደሚወስድ መግለፁ ይታወሳል።
አልሸባብ ከ2007 (እ.አ.አ) ጀምሮ የሀገሪቱን #ያልተረጋጋ መንግስት ለመጣል እየተዋጋ የሚገኝ ታጣቂ ቡድን ነው። ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሥጋት ተደርጎ የተፈረጀውን ታጣቂ ቡድን ለማጥፋትም 20 ሺህ የሚሆኑ የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት ወታደሮች እና የተባበሩት መንግስታት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ አልጀዚራ/AMMA

በተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ!
ተከሳሽ አብዱራህማን ዩኑስ ከሚመከለተው የመንግስት ፈቃድ ውጪ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲል ተይዞ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጥቷል፡፡
ተከሳሽ 53 ቱርክ ስሪት ሽጉጦችንና 35 ሺህ 766 ጥይቶችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A50931 አ.አ በሆነ ላንድክሩዘር መኪና ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲሞከር በተደረገው ክትትል በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ክልል ልዩ ቦታው ጣፎ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተሸከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል፡፡
ተከሳሽ ክሱ በችሎት ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ ድርጊቱን ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ ምስክሮች አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሽጉጥና ጥይት በመኪና ደብቆ በፍተሻ ስለመያዙ በመረጋገጡና መከላከልም ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ጥፋተኛ መሆኑን በይኗል፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመመልከት ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
ምንጭ፡- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

እገዳ የተጣለባቸው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወሙትና ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል። የበላይ አካል ጉዳዩን ይወቅል፤ ችግራችንን ይረዳልን ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፦
"ደብተር ይዞ ግቢውስጥ መንቀሳቀስ ለህይወት አስጊ ነበር፤ በለሊት በተኛንበት ፌደራል ፖሊስ ምንም መረጃ ሳይኖራቸው የዶርማችንን በር ሰብረው ተቀጥቅጠናል ይሄም ተማሪው ለብዙ ቀናት ከግቢ ውጪ እንዲያድር እና እስኪረጋጋ ሲጠብቅ ነበር፤ በጊዜው ኢንተርኔት ተዘግቶ ስለነበር ጩኸታችንን የሚሰማን አካል አላገኘንም። ከአንዴም ሁለቴም የተማሪውን የተስማማበትን ፊርማ አስገብተናል ግን ቀና ምላሽ አልተሰጠንም። በአጠቃላይ ውሳኔውን እንቃወማለን የበላይ አካል አቤት ይበለን።"

የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች የጋራ የሰላምና የልማት ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ ዞኖቹና ወረዳዎቹ ስምምነቱን የፈጸሙት ላለፉት ሁለት ቀናት በአሶሳ ሲካሄድ የቆየው የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ዛሬ ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡ ከኦሮሚያ በኩል ስምምነቱን የፈጸሙት የምዕራብ ወለጋ እና የምስራቅ ወለጋ ዞኖች እና በዞኖቹ ውስጥ የሚገኙ ጎራባች ወረዳዎች ሲሆኑ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል የካማሽ ዞንና አሶሳ ዞኖች በየዞኖቹ ውስጥ የሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች ናቸው፡፡
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአውሮፕላኖች በረራ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በመላ አገሪቱ በሚገኙ 12 ኤርፖርቶች ላይ ፍላይት ካሊብሬሽን እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል። ከሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የበረራ አጋዥ መሳሪያዎች ፍተሻ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ጅግጅጋ፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱም፣ ሰመራ፣ አዋሳ፣ ጅማናና አርባ ምንጭ ኤርፖርቶች ነው።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግሥት ችላ ያለው የኑሮ ውድነት!
መንግሥት በገበያ ንረት ላይ አጥኚ ቡድኖችን አሰማርቻለሁ ቢልም የኑሮ ውድነት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ የኅረተሰብ ክፍሎችን ሕልውና ፈተና ውስጥ እያስገባ ነው፡፡ ባለፉት ሦስትና አራት ወራት የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱንና ባላቸው ገቢ መጠን ለመኖር መቸገራቸውን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው፡፡ በተለይ ጤፍ መቶ ኪሎ 3500 ብር፣ስንዴ 2000 ብር፣በቆሎ 1500 ብር፣ቀይ ሽንኩርት አንድ ኪሎ 30 ብር፣ነጭ ሽንኩርት 160 ብር፣ቲማቲም 25 ብር፣አንድ ሊትር ዘይት 100 ብር፣አንድ ኪሎ ሙዝ 30 ብር…እየተሸጠ ነው፡፡ መንግሥት ጣልቃ በመግባት ሕገ ወጦችን አደብ አስገዝቶ ገበያውን ማረጋጋትም አልቻለም፡፡
Via Yegize Welafen
እናተስ ስለጉዳዩ ምን ትላላችሁ?

የኢትዮጵያ አውሮፕላን ኪስማዮ ውስጥ እንዳያርፍ ተከለከለ!
ወታደሮችን አሳፍሮ ደቡብ ሶማሊያ ኪስማዮ ውስጥ ሊያርፍ ነበር የተባለ የኢትዮጵያ አውሮፕላን በኬንያ ኃይሎች በሚደገፉት የጁባላንድ ክልላዊ ወታደሮች መከልከሉን የዓይን ምስክሮች ገለጹ።
ወደ ኪስማዮ ያቀናው አውሮፕላን 'ከ90 በላይ ኮማንዶዎችን አሳፍሮ ነበር' የተባለ ሲሆን ተገቢውን መረጃ ቀድሞ አልሰጠም በሚል ምክንያት ነው እንዳያርፍ የተከለከለው ተብሏል።
ከምሥራቃዊ ኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ተነስቶ ወደ ሶማሊያ እንደበረረ የሚነገርለት ይህ አውሮፕላን ኪስማዮ እንዳያርፍ በመከልከሉ ወደ ደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በማቅናት ባይዶዋ ውስጥ እንዳረፈም ተነግሯል።
በኪስማዮ አየር ማረፊያ ሰራተኛ የሆነ ግለሰብ አውሮፕላኑ ከኢትዮጵያ መነሳቱንና በኋላም ወደ ባይዶዋ መሄዱን ለሮይተርስ አረጋግጧል። ነገር ግን አውሮፕላኑ የሲቪል ይሁን ወታደራዊ የታወቀ ነገር የለም።
#ቢቢሲአማርኛ
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20

#update ቅራኔዎችን በመፍታት የሀገሪቱን አንድነት ለማስቀጠል የተቋቋመው የማህበራዊ እሴቶች አፈላላጊ ኮሚቴ ስራ ጀመረ። በእረቅ ሰላም ኮሚሽን የተቋቋመው የማህበራዊ እሴቶች አፈላላጊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በቀጣይ ሊሰራቸዉ በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው። በውይይት መድረኩ ላይ ከመንግሥት ተቋማት ፣ ከሰላም ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የመጡ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የሚታዩ የሰላም መደፍረስ እና ቁርሾ አዘል ግጭቶች በእውነተኛ ዕርቅ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተፈተው በህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።
Via #ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያውያኑ ከከፋፋይ ሀሳቦች ይልቅ በአንድነት ላይ እንዲያተኩሩ ተጠየቁ!
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ #በዴንቨር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ትናንት አወያይተዋል። በውይይቱም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመተባበር ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ አምባሳደሩ ጠይቀዋል።
#ጥላቻ እና #ከፋፋይ ሀሳቦችን በመተው ወደ አንድነትና የሚያስማሙ ሀሳቦች ላይ እንዲያተኩሩም ነው መልዕክት የተላለፈው። ለዚህም በአንድነት መሥራት እንደሚገባቸው አምባሳደር ፍፁም ጠይቀዋል። #በዴንቨር የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትም ኢትዮጵያዊነትን መሠረት ያደረገ ውይይት መዘጋጀቱ ተገቢ መሆኑን መናገራቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል።
Via #AMMA

አልቀመስ ያለው ኑሮ!
ለዓመታት በአገሪቱ የታየው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ መናር ዕለት ተዕለት እየጨመረ መጥቶ፣ የሚሊዮኖችን ህልውና #በመፈታተን ላይ ይገኛል። የምግብ ነክ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሬ እጥረት፣ የትምህርት ቤት ክፍያዎች ማሻቀብና ሌሎችም ማኅበረሰቡን ሰቅዘው ከሚገኙት ችግሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። የገንዘብ የመግዛት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ሲሔድ እንጂ ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር ሲጣጣም አይታይም።
ዕድሜው በ30ዎቹ መጨረሻ ላይ የሆነው ተዘራ ዓለምነው ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ዘወትር ከታዛው ሥር የሦስት ሕፃናት ልጆቹ ከርታታ ዓይኖች ይጠብቁታል። ወጣት ነው፤ ግን ቋሚ ሥራ የለውም። በሥራ አመራር የትምህርት ዘርፍ በዲፕሎማ የተመረቀ ቢሆንም ቅሉ፣ በቀን ሠራተኝነት በሚያገኘው አነስተኛ ገቢ ኑሮን ለመግፋት ይታትራል። የኑሮው ውድነት ግን ፈፅሞ አልገፋ ያለው ይመስላል።
“ከወራት በፊት 14 ብር ይሸጥ የነበረው ሽንኩርት 28 ብር ገብቷል፣ 70 ብር የሚሸጠው ዘይት 95 ብር እየተሸጠ ነው፣ ኩርማን የምታክል ዳቦ በ3 ብር መግዛት ከጀመርን ወር ሆኖናል፤ ጤፍ 2300 ብር እንገዛው የነበረው 3500 ብር እየተባለ ነው፤ ታዲያ በዚህ ዋጋ ገዝቼ ልጆቼን መመገብ እችላለሁ?” ሲል የሚጠይቀው የሦስት ልጆች አባት የሆነው ተዘራ፣ ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን ሳይሆን፣ ለመኖር የሚያበቃ አመጋገብ እየመገባቸው መሆኑን ይገልጻል።
/በአዲስ ማለዳ ጋዜጣ/
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-3

#update የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል በማይዳሰስ ወካይ ባህላዊ ቅርስነት በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት /UNESCO/ እንዲመዘገብ እና የአለም ቅርስ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ታሪኩ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ “ የልጃገረዶች በዓል”በሚል ስያሜ የሚከበረው በዓልን የሁሉም ቅርስ ለማድረግ ከአምና ጀምሮ በጽሁፍ እና በምስል መረጃ በማሰባሰብ እና በማደራጀት የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት መረጃዎች መላካቸውን አቶ ታሪኩ ገልጸዋል፡፡
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbebaUniversity
ለዕድሳት #ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ መኮንን አዳራሽ ሙዚየም ዕድሳቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ከዛሬ ጀምሮ ለጉብኝት ከፍት እንደሆነ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም አስታወቀ። ለሙዚየሙ ዕድሳት 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን የዕድሳት ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያና በጃፓን መንግስት መካከል በተደረገ ስምምነት የተካሄደ መሆኑ ታውቋል።
Via #ኢዜአ

ፓስፖርት ለማውጣት የልደት ማስረጃ የሚጠየቁት እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 አመት ለሆናቸው ዜጎች ብቻ ነው ተባለ!
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዜጎች ፓስፖርት ለማውጣትና ለማደስ ሲመጡ የሚያቀርቡት የነዋሪነት መታወቂያና የድጋፍ ደብዳቤ ህገወጥ አሰራር እንዲበራከት በማድረጉ፤ ከዚህ በኋላ የልደት ሰርተፊኬትና መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ማለቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም የልደት የምስክር ወረቀት የትና እንዴት ማግኘት ይቻላል፣ የተወለድንበትን ቀንና አመተ ምህረት በትክክል አናውቅም፣ እና መሰል ጥያቄዎች ከህብረተሰቡ እየተሰሙ ነው፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኤጀንሲው ህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ታሬሳን ስለጉዳዩ ጠይቆ ነበር። የልደት ምስክር ወረቀት በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በወረዳ ወሳኝ ኩነት መ/ቤቶች አማካይነት የሚሰጥ በመሆኑ፤ የተወለዱበትን ቀን የሚገልጽ የሆስፒታል ማስረጃ ይዘው በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ ብለውናል፡፡ ለዚህም ስራ ሲባል ኤጀንሲው የሰርተፊኬት ወረቀቶችን በነጻ ማሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡
የተወለድንበትን ቀን አናውቅም እና ሆስፒታል አልተወለድንም ለሚሉ ጥያቄዎች ሲመልሱም ይህን ታሳቢ በማድረግ እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑትን አንጠይቅም ብለዋል፡፡ ወደፊትም አዳዲስ ማሻሻያዎች ካሉ እናሳውቃለን ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

#update በለገዳዲ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ በተከሰተ የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ከነሔሴ 11ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ አዲስ አበባ የውሃ አገልግሎት መቋረጡን የአዲሰ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው ለኤፍቢሲ እንደገለፁት ፥በጥልቅ የውሀ ጉድጓዱ በተከሰተ የሃይል መቋረጥ በየካ አባዶ፣ በየካ አያት፣ በየካ ጣፎ፣ በቦሌ ሃያትና በቦሌ አራብሳ በሚገኙ የግልና የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውሃ አገልግሎቱን ማድረስ አልተቻለም።
ላለፉት 4 ቀናት የዘለቀውን የሃይል መቋረጥ ችግር ለመፍታትም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎችና አመራሮች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሯ፥ ችግሩ እንደተፈታ ውሃ ወደ ማሰራጨት ስራ ይገባል ብለዋል።
የሃይል መቋረጡ በዛሬው ዕለት ይስተካከላል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም፥በተለይ 4ተኛና 5ተኛ ወለል ላይ ለሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውሃ ለማዳረስ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል በመሆኑ ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ አሳስበዋል።
Via #FBC

የመቐለ ከተማ ሴቶች የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሰማዕታት ሐውልት ግቢ ችግኝ ተከሉ። ሴቶቹ ችግኞቹን የተከሉት በዓሉን ከማድመቅ በተጨማሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራምን ለማሳካት እንደሆነም ተገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአንድ ቦታ፣ በአንድ ጊዜ አራት የመኪና አደጋ ደረሰ!
በባሕር ዳር ዙሪያ በተከሰተ የመኪና አደጋ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የመኪና አደጋ ተከስቷል።
አደጋው የተከሰተው ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር እየሄደ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሸዋ ሮቢት ቀበሌ ላይ ዛሬ 8፡20 አካባቢ በመጀመሪያ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው።
አውቶብሱ ከጎንደር አቅጣጫ እየመጣ ከነበረ ሲኖ ትራክ መኪና ጋርም ተጋጭቷል። አደጋው በዚህ አላበቃም፤ ከባሕር ዳር አቅጣጫ በፍጥነት እየተሽከረከረ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ፣ ተጋጭቶ ከቆመው ሲኖ ትራክ ጋር መጋጨቱም አራተኛ አደጋ ፈጥሯል።
በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዘጋቢያችን ተመልክቷል፤ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሰው ህይዎት እንዳላለፈም ነው ዘጋቢያችን መረጃ ያደረሰን።ተጎጅዎችም ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው። የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ከስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ጥረት ብናደርግም አሁን መረጃ መስጠት የሚችሉበት ደረጃ ላይ አለመሆናቸውን አሳውቀውናል።
Via #አብመድ

#ጥንቃቄ_ይደረግ
"ሱሉልታን ከአ/አ የሚያገናኘው መንግድ በጎርፍ በመሙላቱ መኪናዋች ቆመዋል።" #TIKVAH_ETHIOPIA #AHMUU

#update በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ በአዋሽ ወንዝ መሙላት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። የአዋሽ ወንዝ መሙላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ በርካታ ዜጎችን ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ የተዘሩ የተለያዩ ሰብሎችንም ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ይታወቃል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#P1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2012 የትምህርት ዘመን በሚያስጀምራቸዉ የመንግስት የአዳሪ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ላይ መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የቅበላ መስፈርት!

#P2