TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UpdateSport UEFA Champions League------Quarter Final Draw

AFC Ajax vs Juventus
Liverpool FC vs FC Porto
Tottenham Hotspur vs Manchester City
Barcelona vs Manchester United

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን የዩጋንዳ አቻውን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፏል፡፡ የኦሎምፒክ ቡድኑ በቶኪዮ 2020 ለሚካሄደው የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በአፍሪካ ዞን የምድብ 1 የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከዩጋንዳ አቻው ጋር አድርጎ ተጋጣሚውን አሸንፏል፡፡ ዛሬ ከቀኑ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመጀመሪያውን ግብ ናሙኪሳ አይሻ በራሷ ጎል ላይ ስታስቆጥር ቀሪዎቹን 2 ግቦች ሎዛ አበራ እና ሰርካዲስ ጉታ አስቆጥረዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ቅ/ጊዮርጊስ ከወላይታዲቻ የ15ሳምንት ጨዋታ ዲቻ ቅጣት ላይ ያለ ተጫዋች አስልፎአል በሚል ለቅ/ጊዮርጊስ ያልተጠበቀ 3ነጥብ አግኝቶ ቢያድርም ሲነጋ ቅጣትተገቢ አይደለም ተብሎ ውሳኔ ተገልብጦአል።

Via ታደለ አሰፋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በአዘርባጃኗ ዋና ከተማ ባኩ መካሄዱ ብዙ ቅሬታዎችን አስነስቷል።

የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ለመታደም ብዙ እንግሊዛውያን ወደ ስፔኗ መዲና ማድሪድ እንደሚጎርፉ ይጠበቃል።

ነገር ግን ዛሬ የሚካሄደውን የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለማየት ወደ አዘርባጃን መዲና ባኩ መምጣት የሚችሉት የአርሰናልና የቼልሲ ደጋፊዎች ቁጥር ከ6000 እንደማይበልጥ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የአርሰናሉ ሄነሪክ ሚኪታሪያን #በአርሜኒያዊ ዜግነቱ ምክንያት ደህንት አይሰማኝም በማለት ወደ አዘርባጃን እንደማይሄድ አስታውቋል። አርሜኒያ እና አዘርባጃን 'ናጎርኖ ካራባክ' የተባለው #ክልል የይገባኛል ፍጥጫ ውስጥ ያሉ ሲሆኑ የሚኪታሪያንም #የስጋት ምንጭ ይሄው ነው።

ብዙዎችም የፍጻሜ ጨዋታውን ለምን በአዘርባጃን ማካሄድ አስፈለገ? በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ግን ሃገሪቱ ለምስራቅ አውሮፓ ሩቅ በመሆኗ ምክንያት ውድድሩን ከማዘጋጀት ልትታገድ አይገባም ብሏል።

ባላት የነዳጅ ሃብት ምክንያት እጅግ የበለጸገችው አዘርባጃን ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን ፈሰስ በማድረግ በዓለማቀፍ ስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ያላትን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ እየሰራች ነው።

Via #ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡ የዘንድሮው የአፍሪካ ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ግጥሚያ በሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች መካከል ይከናወናል፡፡ በደርሶ መልሱ የመጀመሪያ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ ራባት ላይ የቱኒዚያውን ኤስፔራስ ስፖርቲቭ ዴ ቱኒስን አስተናግዶ በአንድ አቻ ውጤት መለያየቱ ይታወሳል፡፡ የመልሱ ጨዋታ በቱኒዚያ መዲና ቱኒስ በሚገኘው ስታዴ ኦሊምፒክ ዴ ራዴስ ዕኩለ ሌሊት ላይ ይከናወናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-SPORT
#UpdateSport የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲለያዩ ደጋፊዎች አላስፈላጊ ምልክቶችን በማሳየት ከጨዋታው በፊትም መጠነኛ ግጭት መከሰቱ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ ከዚህ ቀደም በጸጥታ ስጋት የተነሳ ተሰርዞ የፕሬሚየር ሊጉም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር።

Via #DW
@tikvahethsport
#UpdateSport መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ ደደቢትን ተከትለው ከፕሪሚየር ሊጉ ወርደዋል። #FBC

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
#UpdateSport የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል፡፡

ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች ጨዋታወችን ባስተናገደበት ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አላስተናገደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

እንዲሁም በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ የተሰጠው ፎርፌ አግባብነት የሌለውና አድሏዊ መሆኑንም ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡

አዲስ ከመጡት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመተባበር፣ በመቻቻል እና በመተጋገዝ ለመስራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷልም ነው ያለው፡፡

በመሆኑም ፌዴሬሽኑ የወሰናቸውን ኢ – ፍትሃዊ እርምጃዎችን እንዲመረምር እና ያላአግባብ የተወሰነበትን ፎርፌ እንዲያነሳ የጠየቀ ሲሆን ያቀረባቸው ቅሬታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
#UpdateSport ትናንት ምሽት #በሉዛን በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በወንዶች 5 ሺህ ሜትር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ አሸንፏል። ዮሚፍ ርቀቱን በ13 ደቂቃ ከ56 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።አትሌት ሰለሞን ባረጋ ደግሞ 13 ደቂቃ ከ1 ሰከንድ ከ99 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን 2ኛ በመሆን አጠናቋል። አትሌት ጥላሁን ሃይሌ 13 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ ከ9 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዟል።በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ አትሌት አያንለህ ሱሌይማን 3 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ ከ79 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድደሩን በሶስተኝነት ጨርሷል።

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
#updatesport በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ከጅቡቲ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ በአስቻለው ታመነ ጎል 1-0 አሸንፋለች፡፡ የመልሱ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ በቀጣ ሳምንት ይደረጋል፡፡

IVia Soccer Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia