TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚያገናኘው የየብስ መንገድ በአዲስ ዓመት ይመረቃል!

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በየብስ የሚያገናኛትን ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አጠናቃ፣ በመጪው መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም እንደምታስመርቅ ተገለጸ፡፡ 

ባለፈው አመት ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረው የ90 ኪ.ሜትር የመንገድ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ መጠናቀቁን የዘገበው ኤርትሪያን ፕሬስ፤ ቀሪው 10 በመቶ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት  ውስጥ ይጠናቀቃል ብሏል፡፡ 

ኤርትራን ከኢትዮጵያ በየብስ እንደሚያገናኝ የተነገረለት ይኼው መንገድ፤ ቀደም ሲል በ6 ሜትር ስፋት የተሰራ ሲሆን አሁን በተደረገው ማሻሻያና ተጨማሪ ግንባታ፣ በእጥፍ ጨምሮ፣ ከ12 እስከ 20 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጓል፤ 25 አዳዲስ ድልድዮችም ተገንብተዋል ተብሏል፡፡

በሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ #ወሳኝ ሚና እንዳለው በሚነገርለት በዚህ የመንገድ ግንባታ ላይ በርብርብ የተሳተፉት 5 የኤርትራ የመንገድ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን ጨምሮ የአገሪቱ መከላከያ ሀይል መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ 

የመንገዱ እድሳትና ግንባታ አንድ አመት የፈጀ ሲሆን ሙሉ ወጭው በኤርትራ መንግስት መሸፈኑ ታውቋል፡፡ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የመንገድ ግንባታው በአዲሱ ዓመት መስከረም 1 እንደሚመረቅና አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ኤርትሪያን ፕሬስ/addisadmas
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ለመፈለግ እና ችግሩን በሰላማዊ ድርድር ለመቋጨት በፌዴራሉ መንግስት የተቋቋመው " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ላይ ከተጠቀሱ #ወሳኝ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ፦

• ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የትግራይ፣ የአፋር፣ የአማራ ክልል አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ዜጎች በእለት ተእለት ኑሮዋችው ላይ እየገጠማቸው ያለውን ችግር መቀረፍ እንደሚገባ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተማማኝ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ፣ እንዲሁም የመሰረተ ልማት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመር አስቻይ የሆነ ሁኔታ በፍጠነት ለመፍጠር ፤ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት ላይ በአጭር ጊዜ ላይ መድረስ እንደሚገባ አጽኖት ሰጥቷል።

• ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርስ የሚችል እና ለቀጣይ የፖለቲካ ውይይቶች መሰረት የሚጥል የሰላም ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት በማድረግ የምክረ ሃሳብ ሰነድ አጽድቆዋል።

• የሰላም ምክረ ሃሳቡ በተቻለ ፍጥነት ለአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ወኪል እንዲቀርብ ወስኗል።

• ወደተኩስ አቁም ስምምነት ሲገባ በሚፈጠረው አስቻይ ሁኔታ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በተቻለ_ፍጥነት መልሶ ማቅረብ ይቻል ዘንድ፣ አስፈላጊ ቅደም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጿል።

• የአፍሪካ ህብረትም የሰላም ንግግሩ በአስቸኳይ ተጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል ዘንድ፣ የሰላም ንግግሩ የሚካሄድበትን ቦታ እና ጊዜ በፍጠነት ወሰኖ ንግግሩ እንዲጀመር፣ ይህን ማድረግ ይቻል ዘንድ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሆነ ገምግሟል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU የ " ኢትዮጵያ መንግስት " እና የ " ህወሓት " ን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫው ምን አሉ ? - የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል። - በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)…
#PeaceTalks

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህበረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

እስካሁን የንግግሮቹን ይዘት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም። በዛው ያሉ ሚዲያዎችም ስለ ሰላም ንግግሩ እና ስለሂደቱ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እንዳይኖር ተደርጓል።

የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ እንደሚቀጥል ነው የሚጠበቀው።

የደቡብ አፍሪካ/ፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ አመቻችነት ነው እየተመራ የሚገኘው።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN)፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ደግሞ በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

በሌላ በኩል፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ለስራ ጉብኝት ወደ ካናዳ (ኦታዋ) በሄዱበት ወቅት በዛው ከነበሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ውይይት እንዳካሄዱ ገልፀዋል።

ፋኪ በውይይቱ ፤ ለአፍሪካ ሰላም የፖለቲካ ሂደትን በተመለከተ እንዲሁም በታህሳስ ወር ለሚካሄደው የአፍሪካ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

የደ/አፍሪካው ሰላም ንግግርም "ወደ ተኩስ አቁም ይመራል " የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሊቀመንበሩ (ሙሳ ፋኪ መሀመት) እና የአፍሪካ ህብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን #ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ፎቶ ፦ ሮይተርስ/AU

@tikvahethiopia