TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል። ሚኒስቴሩ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ዋጋ #በጥቅምት_ወር በነበረው እንደሚቀጥል ገልጿል። የነዳጅ ዋጋው ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቅ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015…
#ነዳጅ

ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም ገባ።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የዋጋ ክለሳ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ሕብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር መደረጉንም ገልጿል።

በዚህም በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15 ከ 76 ሳንቲም ወደ ብር 17 ከ 33 ሳንቲም እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19 ከ02 ሳንቲም ወደ ብር 22 ከ 68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።

በቀጣይ ፤ ሦስተኛ ዙር እና ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ÷

- ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ብር ከ 30 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 67 ብር ከ30 ሳንቲም

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ67 ሳንቲም፣

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 48 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 67 ብር ከ91 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #Update

ወደ ትግራይ ክልል #ነዳጅ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፤ ወደ መቐለ 10 ቦቴ ነዳጅ መግባቱን ያመለከተ ሲሆን ወደ ኩዊኃ እና ዓጉላም ነዳጅ መግባት መጀመሩን ጠቁሟል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጥሩ ትብብር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮ " እናተ ጋር ካለው ችግር አንፃር ቅድሚያ እንሰጣለን " ተብለናል ሲል ገልጿል።

ጦርነት ለመፈጠሩ በፊት በወር 12 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ይገባ እንደነበር የገለፀው ቢሮው አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ ከሚፈለገው አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ብሏል።

መቐለ ውስጥ ካሉት 15 ማደያዎች ነዳጅ የገባው በ4ቱ ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ነዳጅ ለማግኘት እነማን ቅድሚያ አላቸው ?

አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ በተወሰነ መልኩ ስለሆነ ፦

- አምቡላንስ
- እሳት አደጋ
- ውሃ አቅራቢ ቦቴዎች
- የመንግስት ተሽከርካሪዎች
- የእርዳታ አከፋፋይ አካላት
- ባንክ፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል
- በትራንስፖርት ቢሮ ታሪፍ የወጣላቸው ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቅድሚያ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

የፋይናንስ እጥረት በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን ያሳወቀው ቢሮው ችግሩን ለማፍታት ከባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቤንዚን እና ናፍጣ ስንት እየተሸጠ ነው ?

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከፌዴራል መንግስት ለክልሉ እንደተላከ ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ #ቤንዚን በሊትር 60 ብር ከ57 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን #ናፍጣ 66 ብር ከ58 ሳንቲም እየተሸጠ መሆኑን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit : Tigrai Television

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል።

ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን እና የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር እንደሚያደርግ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።

የነዳጅ ግብይቱ በ #ቴሌብር አማራጭ የሚከናወን ነው የተባለ ሲሆን በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሁሉም የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ የትራንስፖርት ትኬት በዲጂታል እንደሚጀመር አሳውቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል። ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል። ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን…
#ነዳጅ

" ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ #በኤሌክትሮኒክስ_የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ገልጾ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም አሳውቋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ #ከሐምሌ_አንድ ጀምሮ #በአስገዳጅነት እንደሚተገበር ተጠቁሟል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በ " ቴሌ ብር " ውጤታማ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በ " ቴሌ ብር " ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አመልክቷል።

የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገንባቱንም አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር ደግሞ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያለ ሲሆን በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን ይፈታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ሲል አሳውቋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ " ቴሌብር " ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። በ " ቴሌብር " ነዳጅ ስለ መቅዳት አሸከርካሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው ? ☞ በቅድሚያ የ " ቴሌብር "ተጠቃሚ መሆን፤ ☞ በቂ ክፍያ የቴሌብር አካውንት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ፤ ☞ የ " ቴሌብር " የሚስጥር…
#ነዳጅ #አዲስአበባ

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል አማራጭ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ከቴሌ ብር በተጨማሪ ሌሎችም የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ክፍያ በ " ቴሌ ብር " ብቻ እንደሚፈፀም እያሳወቀ ይገኛል።

ባለፉት ተከታታይ ቀናትም ቢሮው የመኪና ባለቤቶች በቀሩት ጥቂት ቀናት የነዳጅ ክፍያ በ" ቴሌ ብር ብቻ " እንደሚከፈል በመገንዘብ ከእንግልት ለመዳን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ እያሳወቀ ነው።

ቢሮው መሰል መልዕክቶችን በተረጋገጠ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ ነው ለህዝብ እያሰራጨ የሚገኘው።

ለመሆኑን የነዳጅ ክፍያ ከ " ቴሌ ብር " ውጭ መፈፀም አይቻልም ?

ኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ለዚሁ አገልግሎት የሚውል " #ነዳጅ " የተባለ የሞባይል መተግበሪያ ማቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መተግበሪያው ተገልጋዮች የነዳጅ ክፍያቸውን ከንግድ ባንክ አካውንታቸው የተርጋ ቁጥራቸውን ብቻ በመጠቀም መክፈል ያስችላል ያለ ሲሆን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የነዳጅ ክፍያው " በቴሌ ብር ብቻ " ነው የሚፈፀመው እያለ ለህዝብ እያሰራጨ ያለው መልዕክት ትክክል እንዳልሆነ አስረድቷል።

" ነዳጅ " የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ከክፍያ አማራጭነት በተጨማሪ አሽከርካሪዎች አቅራቢያቸው የሚገኙትን ማደያዎች ከአቅርቦታቸው ጋር ማግኘት የሚችሉበት አማራጭም እንዳለው ድርጅቱ ገልጾልናል።

የክፍያ አማራጩ በሀገሪቱ ከሚገኙ ማደያዎች 60 በመቶ ማዳረስ መቻሉንም ጠቁሟል።

መተግበሪያው የት ይገኛል ? https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር መተግበሪያ አማካኝነት ነዳጅ ለመቅዳት የሚያስችል አዲስ የዲጅታል አሠራር መዘርጋቱን ገልጿል።

ክፍያውም በማንኛውም ስልክ በሲቢኢ ብር አጭር ቁጥር ወይም በሞባይል መተግበሪያው መፈጸም ይቻላል ተብሏል። አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተጠቆመው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ከነገ ሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ብቻ ይደረጋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያቀረበውን #ነዳጅ የተባለ መተግበርያ በመጠቀም ከ900 በላይ የሚሆኑ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ግብይት መፈፀም የሚያስችል አሰራራር አስተዋውቋል።

የነዳጅ መተግበሪያን በመጠቀም እንዴት መገበያየት ይቻላል ?

- በመጀመሪያ የነዳጅ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ያውርዱ፤

- ሙሉ መረጃዎን በማስገባት መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ ወዲያውኑ የነዳጅ መለያ ቁጥር በ አጭር የጽሁፍ   መልዕክት ይደርስዎታል።

- በመቀጠል መተግበርያው ላይ የተሽከርካሪዎን የሰሌዳ ቁጥር በማስገባት ተሽከርካሪዎን ይመዝግቡ።

- የነዳጅ መለያ ቁጥርዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ Utility ውስጥ በመግባት Utility payment በመምረጥ በመልእክት የደረሰንን የነዳጅ ID አስገብተን Link ማድረግ ወይንም በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።

ከዚህ በኋላ ቀጥታ ከሂሳብ አካውንትዎ ግብይት መፈጸም ብቻ !

- ነዳጅ ለመቅዳት ማደያ በሚሄዱበት ወቅት የነዳጅ ቀጂ ባለሙያው የሰሌዳ ቁጥርዎን ፣  የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን በ(ነዳጅ ቀጂው) መተግበሪያ ላይ በማስገባት ግብይቱን ያስጀምራል።

- ወዲያውኑ በሚደርስዎት የአጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ የሚስጥር ቁጥሩን(OTP) ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው በመንገር ግብይቱን ያጠናቅቁ።

ነዳጅን ለየት የሚያደርገው ፦

አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት መሆኑ!

በአቅራቢያዎ ያሉ ነዳጅ ማደያዎችን እንዲሁም ነዳጅ መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋግጠው መሄድ የሚያስችሎትን አማራጭ ይዞ መምጣቱ!

አንዴ በመተግበሪያው ላይ ከተመዘገቡ በኋላ የስማርት ስልክ አለማስፈለጉ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ?

ፕላይ ስቶር:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

አፕስቶር : https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ማከናወን ይቻላል።

#ነዳጅ #CBE #ኤግልላየን
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ለማስፈጸም ከትናንት በስቲያ ጀምሮ መተግበር የጀመረው አሠራር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎችን እያጨናነቀ እና ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆነ እንዳለ ተገልጿል።

ተገልጋዮች ከመጠን በላይ የነዳጅ ግዥ እየፈጸሙ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ማደያዎች የነዳጅ እጥረት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዲጂታል ክፍያ መተግበሪያውን ለመጠቀም የተፈጠረው ብዥታም በብዙ ማደያዎች ረዣዥም ሠልፎች እንዲታዩ ከማድረጉም በላይ ቶሎ ነዳጅ ቀድቶ ለመሄድ አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ አሁን ያለው መጨናነቅ የተፈጠረው አገልግሎቱን ለማስጀመር በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱና አሽከርካሪዎች አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት እንዲዘጋጁ ባለመደረጉ ነው ብሏል።

" ይሄንን ሥጋታችንን ቀደም ብለን  አሳውቀናል " ያለው ማህበሩ " አሁን ብዙዎች ወደ ሲስተሙ እየገቡ ቢሆንም ከሥጋት አንጻር የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " ሲል አሳውቋል።

ድርጊቱ የነዳጅ እጥረት ሊያስከትል ይችላል ተብሎ እንደሚሠጋ የገለፀው  የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆን እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል፥ ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ሲል ማህበሩ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ከዚሁ የነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም አሠራሩን ከመተግበር አንጻር ያለውን መጨናነቅ ለማስቀረት በሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎች #ባለሙያዎችን በማሰማራት ለተገልጋዮች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ደኤታው አቶ ኦዴኦ ሐሰን ፥ ይህን አገልግሎት ለመተግበር #መንገራገጮች ቢኖሩም፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው አዲስ አሠራር ከግንቦት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋጋጠዋል፡፡

የአገልግሎቱ መጀመር ዘመናዊ ግብይትን ከማሳለጥ ባለፈ ከነዳጅ ሥርጭት ጋር በተያያዘ ሲፈጠሩ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችንና ብክነትን ከማስቀረት አኳያ፣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

ይህንን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት መተግበሪያዎቹን ይፋ ባደረገበት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በሁለት ቀናት 43 ሺህ  የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ የግብይት  ልውውጥ  መካሄዱን አሳወቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ / ኢብኮ በሰጠው ቃል ነው።

ሚኒስቴሩ ምን አለ ?

- በ2  ቀናት ብቻ 43 ሺህ  የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ የግብይት  ልውውጥ ተካሂዷል። በዚህም 80 ሚሊዮን ብር የሚሆን ሽያጭ ተካሂዷል።

- አፈፃፀሙ ከቀን ወደ ቀን  መሻሻሎች እየታዩበት ነው።

- ለዝግጅት የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ ባለመጠቀም ከነዳጅ ማደያ ቀጂዎች  በኩል የመተግበሪያው አጠቃቀም ውስነት፣  የሰው ሀይል ቁጥር ማነስ  እና አንዳንድ አሽከርካሪዎች መተግበሪያው ሳይኖራቸው ለአገልግሎት መቅረባቸው ፤ የአገልግሎት አሰጣጡ እንዲስተጓጎልና ሰልፍ እንዲፈጠር አድርጓል። አሁን ላይ አፈፃፀሙ ከቀን ወደ ቀን መሻሻሎች  እየታዩበት  ነው።

- አንዳንድ  አሽከርካሪዎች በቂ ነዳጅ እያላቸው የክፍያ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ  መደገፉን ተከትሎ በመደናገጥ  የመሰለፍ ሁኔታ በግንዛቤ እጥረት የተፈጠረ በመሆኑ እርምት ሊወሰድበት ይገባል።

- ነዳጅ የሚገዙት እና የሚሸጡት አካላት  ልምድ እያገኙ ሲሄዱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ችግሩ ይቀረፋል።

- ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በክልሎች ጭምር የነዳጅ ግብይቱ  በኤሌክትሮኒክስ መካሄድ ይጀመራል። አሁን ያጋጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ  ከወዲሁ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በሰፊው እየተሰራ ነው።

#የንግድ_እና_ቀጠናዊ_ትስስር_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ

⛽️ " አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበተለሁ " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

⛽️ " ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ።

" በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለ " የሚለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህ እየታወቀ የነዳጅ ዕጥረት ይከሰታል የሚሉ አዋኪ መልዕክቶች ሆነ ተብለው የሚነዙ መሆኑን ሕብረተሰቡ ይገንዘብ ሲል አሳስቧል፡፡

በቀጣይ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እና ዕጥረት መፍጠርን የመሳሰሉ ችግሮች በሚፈጥሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እወስዳለሁ ሲልም አስጠንቅቋል።

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት ካለመክፈት ጋር የተያያዘ እንጅ የነዳጅ ዕጥረት አይደለም ሲል አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፤ ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው ብሏል።

አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥
" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆንም እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል " ያለ ሲሆን " ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የተደረገው የዲጅታል የነዳጅ ግብይት ከነገ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በመላ_ሀገሪቱ ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።

ነገ በመላው ሀገሪቱ በሚጀምረው የዲጂታል የነዳጅ ግብይት በሁሉም ክልሎች ያሉ ነዳጅ ማደያዎች ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር።

የዲጂታል ነዳጅ ግብይት ከነገ ጀምሮ በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል።

እንዴት በዲጂታል መንገድ የነዳጅ ግብይት ማካሄድ ይቻላል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አብሯቸው ከሚሰራቸው ኢትዮ ቴሌኮም / ቴሌብር ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኤግል ላይን ቴክኖሎጂ / ነዳጅ / በኩል የነዳጅ ግብይቱን በተመለከተ ተከታዩን መልዕክት ያስተላልፋል።

#ቴሌብር

- በቴሌ ብር ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ነዳጅ ማደያ ስትሄዱ በቅድሚያ ፤ የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል የቴሌብር አካውንት በቀላሉ ክፈቱ፤

- ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች ከሚገኝ የባንክ አካውንታችሁ፤ በየነዳጅ ማደያዎቹ በተመደቡ የቴሌብር ወኪሎች ወይም የአገልግሎት ማዕከሎች አማካኝነት ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ፤

- የነዳጅ ማደያ ሠራተኞች ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ በስልክዎ በሚደርስዎ የማረጋገጫ መልዕክት ላይ የገንዘብ መጠኑ ትክክል መሆኑን በማየት የሚስጥር ቁጥር ማስገቢያ ሳጥኑ ውስጥ የሚስጥር ቁጥር (ፒን) በማስገባት ያረጋግጡ፡፡

በመጨረሻም ክፍያው መፈጸሙን የሚያረጋግጥ አጭር መልዕክት የሚደርስዎ ሲሆን ከቴሌብር ሱፐርአፕም ደረሰኝ ማግኘት ይችላሉ፡፡

#ነዳጅ_መተግበሪያ

በነዳጅ ከነገ ጀመሮ በመላ ሐገሪቱ በሚገኙ 1100 በላይ የነዳጅ ማድያዎች ነዳጆን መቅዳት ይችላሉ።

- አንድ ጌዜ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ  አካውንቶን Link አርገው የሚጠቀሙበት፤

- በነዳጅ STANDBY( ፈጣን) ፈጣን አግልግሎት የሚያገኙበት ነው።

ከPLAY STORE እና APP STORE አውርደው ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ ፦

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#CBE_BIRR

በሲቢኢ ብር ነዳጅ ሲቀዱ ሁለት አማራጮች አሉ።

የመጀመሪያው ፦

ራስዎ ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያዎ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ክፍያ ፈጽመው ነዳጅ የሚቀዱበት ነው፡፡

ሁለተኛው ፦

ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ߹ የሰሌዳ ቁጥርዎን እና የሚቀዱትን ነዳጅ የገንዘብ መጠን አሳውቀው በሚደርስዎት አጭር መልእክት መሠረት የገንዘብ መጠኑን ትክክለኛነት አረጋግጠው ክፍያውን በመፈፀም ነዳጅ የሚቀዱበት አማራጭ ነው።

የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን ፦

ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

ለአፕል ስልኮች ፦
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

@tikvahethiopia