TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማህበረሰብ ተስፋ ሲቆርጥ ምን ይፈጠራል?

"...እንደ ህዝብ ደግሞ ህዝብ ተስፋ ከቆረጠ እሴቶቹን ይጥላል፤ ነገ ለውጥ የለም፤ ምንም ተስፋ የለንም ብሎ ካሰበ፤ ይጋደላል፣ ይሰዳደባል፣ ተስፋ የቆረጠ ሰራዊት ልታይ ትችላለህ ፌስቡክም ላይ ሚዲያም ላይ፤ ህዝብ ተስፋ ከቆረጠ መከባበሩ ይጠፋል፤ ትህትናው ይጠፋል፤ ፍቅሩ ይጠፋል፤ ሚታየው ነገር የለም። ሰውን ስነ ስርዓት ከሚያሲዙትና እሴቶቹን ጠብቆ እንዲኖር ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ነገ መልካም ይሆናል የሚል #ተስፋ ነው" ዶክተር #ወዳጄነህ_ማሀረነ

#HOPE #TIKVAH/#ተስፋ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeTelegramChannel ይህ "ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር" የሚለው ገፅ ሀሰተኛ ነው። ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት "ልዩ መረጃ" በሚል ምንም አይነት የፌስቡክ ገፅም ሆነ የቴሌግራም ቻናል እንደሌለኝ እወቁልኝ ብሏል። ለቴሌግራም Report እንድታደርጉም ጥሪ እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

የተማሪዎችን ብቃት፣ ክህሎትና ተግባቦት በማጠናከር አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ያስችላሉ ተብሎ የታመነባቸው አዳዲስ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ከመጪው ዓመት ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በሶሰት ዓመት ይጠናቀቅ የነበረው የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር ወደ አራት ዓመት ከፍ እንዲል ይደረጋል ተብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-18

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ላለፉት ሁለት ቀናት በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልሎች የጋራ የሰላምና የልማት መድረክ የጋራ የልማትና የሰላም ስምምነት በመፈረም ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፓስፖርት

ከዚህ ቀደም ፓስፖርት ለማግኘት ይጠየቅ ነበረው የድጋፍ ደብዳቤ ቀርቶ በመታወቂያና በልደት የምስክር ወረቀት መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳን ኩነት ኤጀንሲን ገልጿል። ከዚህ በኋላም ፓስፖርት ለመውሰድ ጥያቄ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ሕጋዊ መታወቂያና የልደት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ተብሏል፡፡

ፓስፖርት በአስቸኳይ ለሚፈልጉ ሰዎችም ከ3 እስከ 5 በሚደርሱ ቀናት ውስጥ ምላሽ እንደሚያገኚ ኤጀንሲው የገለጸ ሲሆን በመደበኛ ጊዜም ሆነ በአስቸኳይ ፓስፖርት ለማደስ እና አዲስ ለመጠየቅ ሕጋዊ መታወቂያና የልደት የምስክር ወረቀት መያዝ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።

ይህ አሰራርም ዜጎች የልደት የምስክር ወረቀት እንዲኖራቸው እንዲሁም ሕገ ወጥ መታወቂያዎችን ለመከላከል የልደት የምስክር ወረቀቱ እንደሚያግዝ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ፓስፖርትን ያለ አሳማኝ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት ተከለከለበት ምክንያት ሕገ ወጥ ስደትን ለመከላከል ሲሆን የውጪ ምንዛሪ እጥረትም ሌላኛው ምክንያት እንደነበር የኤጀንሲው ገልጾ ነበር።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፀሎት ቀን!

በአገር አቀፍ ደረጃ የዕርቅ መንፈስ እንዲመጣ ለማስቻል ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባዔ ጋር በመተባበር የፀሎት ቀን ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ብሔራዊ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እኛ እንደ TIKVAH-ETH ቤተሰብ 6710 ላይ መልዕክት በመላክ የልብ ህሙማን ህፃናትን አለንላችሁ እንበላቸው!! በቤተሰባችን ምን ያህል አስተዋፅኦ እናደርጋለን??

የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በትንሹ 20,000 ሆነን 3 መልዕክት ብንልክ 60,000 ብር በአንድ ምሽት አስተዋፆ ማድረግ እንችላለን!!

እኔ ካለኝ ላይ አካፍያለሁ?? እናተስ??

ለአንድ መልዕክት የሚቆርጠው 1 ብር ብቻ ነው!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመልካም ተግባር ወደኃላ የማይለው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ ስራውን ጀምሯል💪 6710 የልብ ህሙማን ህፃናትን እኛ አለንላችሁ እንበላቸው!

እርሶ ልከዋል??