TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JIMMA ጅማ ከተማ ቤተክርስቲያን #ተቃጠለ፤ አገልጋዮችም እየታረዱና እየተገደሉ ነው፤ በሚል በፌስቡክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። ይህን ስራ እየሰሩ ያሉት ምንም ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ናቸው ያለው የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን በከተማይቱ ውስጥ ንብረት አልወደመም ሰዎች ላይም ጉዳት አልደረሰም፤ እየተናፈሰ ያለውም በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ በመልቀቅ ህዝቡን ማደናበር ነው ብሏል። በመሆኑም ሁሉም አካላት የጉዳዩን ጥንስስ አላማን በመረዳት ዋስትና ለሆነዉ ሰላምና አንድነት ተግቶ በመስራት ጅማን #ወደቀድሞ ሰላሟ ለመመለስ እየተደረገ ላለዉ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ዞኑ ጥሪ አስተላልፏል።

የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን⬆️
_______________________________________

ከጅማ ከተማ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ዝርዝር እና የተጣሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን፦

•ዛሬ በከተማይቱ አንዳንድ አካባቢዎች ለተፈጠረው ውጥረት ምክንያቱ ምንድነው?
•በእርግጥ በከተማው በአሁን ሰዓት በፌስቡክ ላይ እየተወራ እንዳለው የከፋ እና አስጊ ችግር አለ?

📑የከተማይቱን ነዋሪዎች፣ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንዲሁም የከተማው የፀጥታ ኃላፊዎች ስለተፈጠረው ሁኔታ ምን ይላሉ? የሚለውን እንዳዘጋጀንና እንደጨረስን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia