TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ

" በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። 

እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተበዳዮች ገልፀዋል።

የሚጠቀሙት የማጭበርበር ስልት ምንድነው ?

አጭበርባሪዎቹ በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይ በፌስቡክ እና በቴሌግራም ሌሎች ሰዎችን ለመሳብ " እኔ 10 ሺ ብር ኢንቨስት አድርጌ 180 ሺ ብር አግኝቻለሁ እናንተም ኢንቨስት አድርጉ " የሚል የምስክርነት ቪዲዮ አሰርተው ይለቃሉ።

መልዕክቶቹንም በፌስቡክ #Sponsored በማድረግ ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ እንዳደረጉት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።

አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን የሚቀርቡት ስማቸውን ፤ አድራሻቸውን ፤ ፎቶአቸውን የውጪ ሀገር ዜጋ አስመስለው ሲሆን በተጨማሪም የውጪ ሃገር የቢዝነስ አማካሪ እንደሆኑ ጭምር ያስመስላሉ።

አጭበርባሪዎቹ የውጪ ሃገር ሰው እንደሆኑ ያስመስሉ እንጂ ገንዘቡን የሚያስልኩት በሀገር ውስጥ ባንኮች መሆኑን ተበዳዮች ለቲክቫህ ከላኩት ማስረጃ ማየት ተችሏል።

በርካታ ተበዳዮች ስለ ፎሬክስ አሳሳች የቪዲዮ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎችን ተመልክተው 10ሺ ብር ለቡድኑ በመላክ መጭበርበራቸውን ገልፀዋል።

ተበዳዮች ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ ገንዘባቸው ኢንቨስት ስለተደረገ ገንዘቡን ለማስለቀቅ ተጨማሪ 36ሺ ብር ሲጠየቁ ሌሎች ተበዳዮችን ደግሞ "10 ሺ ኢንቨስት አድርጌ 180ሺ አትርፌአለሁ" የሚል የቪዲዮ ምስክርነት በኢንግሊዝኛና አማርኛ ቋንቋ ቀርፀው ከላኩ ገንዘቡን እንመልሳለን ብለው እንዳታለሏቸው አስረድተዋል።

ተበዳዮች ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ገፍተው መጠየቅ ሲጀምሩ ቡድኖቹ አድራሻቸውን አጥፍተው እንደሚሰወሩ ተበዳዮች ሲገልፁ ቀርፀው የላኩትን ቪዲዮ ሌሎችን ለማታለል እያዋሉት እንደሆነ በማየታቸው ሌሎች ሰዎች በእንደዚህ አይነት ማታለያ ከመጭበርበር እራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አስጠንቅቀው ፥ አጭበርባሪዎቹን የሚመለከተው የህግ አካል ሊከታተላቸው እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ ምንድነው ?

- ማኛውም ገንዘባችሁን አምጡ እያሉ በኦንላይን ለሚጠይቁ አካላት ፦
• ማንነታቸውን በትክክል የሚገልፅ መታወቂያ እንዲልኩ
• የሚሰሩበትን አድራሻ (ሀገር፣ ከተማ፣ አካባቢ) እና ከትክክለኛው አካል ህጋዊ ፍቃድ እንዳላቸውና እሱን እንዲልኩ መጠየቅ ይገባል።

- በተለይም በቴሌግራም ሆነ ፌስቡክ የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት (✅️) መግዛት ቀላል ስለሆነ ይህ ምልክት ያለበት ሰው እውነተኛ እና ታማኝ ነው በሚል የተሳሳተ አመለካከት እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ። ማንኛውም ሰው ይሄን ምልክት እየገዛ የተረጋገጠና እውነተኛ ታማኝ ሰው ለመምሰል ይሞክራል።

- " በትንሽ ብር ብቻ እጅግ ብዙ መቶ ሺዎች የሚገኝበት ነው " ስንባል እንዲህ የሚሉንን ሰዎች በበቂ ጥያቄ ማፋጠጥ፣ እያንዳንዱ አካሄዳቸውን መመርመር፣ በሌሎች በርካታ መንገዶች ሰዎቹን በጥያቄ መፈተሽ ይገባል።

ይወያዩ ፦ @BirlikEthiopia

Via 👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM