TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የካንሰር ህክምና . . . #በኢትዮጵያ

#ጥቁር_አንበሳ

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፤ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ መኖራቸውን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ክፍል ኃላፊ ኤዶም ሰይፉ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" የተለያዩ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠብቁ ከ2013 መጨረሻ፣ 2014 ዓ.ም. እና 2015 ዓ.ም. ወረፋ ያልደረሳቸው አሉ፡፡

ይሁን እንጂ በየዕለቱ የሚመጡ ድንገተኛ የካንሰር ታካሚዎች በመኖራቸው በቅድሚያ ለእነዚህ ታካሚዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል።

በሆስፒታሉ ቆይተው መታከም ይችላሉ ተብለው የተለዩት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ ጥረት እየተደረገ ነው።

ለዚህ ወረፋ መብዛት ዋነኛ ምክንያት ብለው ያቀረቡት በሆስፒታሉ የሚገኘው መሣሪያ #አንድ ብቻ መሆኑን ነው።

በዚህ ዓመት ብቻ በተደረገው ማጣራት የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠበባቁ 5,000 ታካሚዎች ሲኖሩ፣ በማዕከሉ በቀን በአማካይ ከ300 በላይ ታካሚዎች ይስተናገዳሉ።

ከእነዚህ የካንሰር ታካሚዎች መካከል 70 በመቶ የጨረር ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፣ ኬሞ ቴራፒ የሚያስፈልጋቸው የታካሚዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም ።

በማዕከሉ አገልግሎት ለማግኘት የ2014 ዓ.ም. እና በ2015 ዓ.ም. ሕክምና ለማግኘት የተመዘገቡ ደግሞ ከ10,000 በላይ ናቸው። "

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ስፔሻላይዝድ_ሆስፒታል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክሊኒካል ኢንኮሎጂስት ዶ/ር አማረ የሺጥላ ምን አሉ ?

"  በሆስፒታሉ የሚሰጠው የካንሰር ሕክምና ኬሞ ቴራፒና ቀዶ ጥገና ነው።

የጨረር ሕክምና ለመጀመር የማሽን ተከላ ላይ እንገኛለን። 60 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ታካሚ እስኪጠናቀቅ እየተጠባበቁ ነው።

በሆስፒታሉ ካንሰር ሕሙማን ሕክምና አንዱ የሆነው ኬሞ ቴራፒ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ በዛ ከተባለ ከሳምንት አይበልጥም።

ይሁን እንጂ ለካንሰር ሕሙማን የሚሰጠው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመጠባበቅ ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ያስፈልጋል። "

#በሐሮሚያ_ዩኒቨርሲቲ_ሕይወት_ፋና_ሆስፒታል

በሐሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል በካንሰር ሕክምና ረዳት ፕሮፌሰር ሚካኤል ሻውል (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በሆስፒታሉ የኬሞ ቴራፒና የጨረር ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን እየተሰጠ ነው።

የጨረር ሕክምና ከተጀመረ ስድስት ወራት አስቆጥሯል ፤ የታካሚዎች መጠነ መጠበቅ ከሦስት ወራት አይበልጥም።

በሆስፒታሉ በዓመት እስከ 6000 የካንሰር ታካሚዎች ሕክምና ያገኛሉ። በተለይ ደግሞ ጨረር ሕክምና ከተጀመረ በኋላ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ በምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜያት ብቸኛው የካንሰር ሕክምና መስጫ በመሆኑ ከሶማሌላንድና ከሌሎች አገሮች እየመጡ አገልግሎት የሚያገኙ ነበሩ። "

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia