TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ #ኢቦላ መከሰቱ ተረጋገጠ፡፡ ቫይረሱ በአካባቢው ሊከሰት የቻለው አንድ ታማሚን ጨምሮ 18 ተሳፋሪዎችን ያሳፈረ ተሸክርካሪ በትናንትናው እለት ጠዋት ላይ ከቡተምቦ ተነስቶ ኖርድ ኪቩ ግዛት ውስጥ የመትገኘው ጎማ ከተማ መግባቱን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል። በዚህም ግለሰቡ ላይ በአፋጣኝ በተደረገ ምርመራ የኢቦላ ቫይረስ እንዳለበት የተረጋገጠ ሲሆን፥ ከታማሚው ጋር የተሳፈሩ መንገደኞች እና አሽከርካሪው ክትባት እንዲሰጣቸው መደረጉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ጎማ ከተማ በሀገሪቱ በዓመቱ በሁለተኛ ደረጃ ቫይረሱ ስርጭት ከተመዘገበበት አካባበቢ በስተደቡብ አቅጣጫ የምትገኝ ሰፊ ከተማ መሆኗም ነው የተነገረው። በጎማ ከተማ ቫይረሱ መከሰቱ በሩዋንዳ አወሳኝ አካባቢ እንደመሆኑ እና አካባቢው ህዝብ በሰፊው በሰፈረበት በመሆኑ በፍጥነት ይዘመታል ተብሎ ስጋት መፍጠሩም ተነግሯል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢቦላ #ኢትዮጵያ

የኢቦላ ወረርሽኝን ቀድሞ ለመከላከል የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ለቅድመ መከላከል ስራውም ከ290 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን ነው ኢንስቲቲዩቱ የገለፀው።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በየነ ሞገስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል እና የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዚህም በቦሌ፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ እና ባህር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች የተጓዦችን የሰውነት ሙቀት በመለካት የልየታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በየብስ ትራንስፖርት ወደ አገር ወስጥ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ደግሞ በ21 የፍተሻ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመጡ መንገደኞች ነጻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እስከ 21 ቀን ድረስ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። እስካሁንም ከ17 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ልየታ የተደረገባቸው መንገደኞች የ21 ቀን ክትትል ተደርጎላቸው ነጻ መሆናቸው ታውቋል።

በአጠቃላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ኬላዎች የልየታ ማዕከል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢቦላ

ሩዋንዳ ድንበሯን ዘጋች!

ሩዋንዳ በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ገለጸ። ሩዋንዳ እርምጃውን የወሰደችው በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በምትገኘው የጎማ ከተማ ሦስተኛ የቫይረሱ ምልክት በመታየቱ ነው። ኪጋሊ የወሰደችው እርምጃ የዓለም የጤና ድርጅት ወደ ኮንጎ የሚደረግ ጉዞ ላይ ገደብ እንዳይጣል እና ከሀገሪቱ ጋር ያለው ድንበር እንዳይዘጋ ካቀረበው ጥሪ ጋር የሚጻረር ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦክስፋም ማስጠንቀቂያ!

#ኢቦላ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከቁጥጥር ውጭ የመሆን አቅም እንዳለው ኦክስፋም አስጠንቅቋል። ኦክስፋም ይህን ያለው ባለፈው ማክሰኞ ኢቦላ ለሁለተኛ ጊዜ በምስራቃዊ ጎማ ከተማ  እንደተከሰተ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia