TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ⬆️

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን በፍቅር ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን የቅበላ ኮሚቴዉ አስታወቀ፡፡

ለአቀባበሉ የተዋቀረዉ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ አቀባበል ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል ብሏል፡፡

ታማኝ በየነ በኪነ ጥበቡ ዙሪያ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማነቃቃት፣ የመድረክ ፈርጥ ሆኖ ሌሎች ተከታዮቹን በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል፡፡

ለረጅም ዓመታት #አንድነትን#ፍቅርን#መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን በተሰጠዉ መግለጫ ተገልጿል፡፡

ይህ ኢትዮጵያዊ #ጀግና ነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የሥራ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ብለዋል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ ዕለት ተገኝተዉ በፍቅር እጃቸዉን ዘርግተዉ እንዲቀበሉት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም እደሩ!

የካቲት 7/February 14 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ነው! ክብር ለሰራዊቱ አባላት! የሰላም ፀር ሁሉ ይህን #ጀግና_ሰራዊት ሲመለከት #ይንቀጠቀጣል! እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን አደረሰን!
.
.
መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ነው!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች " የጥላቻ አስተሳሰብና የጥላቻ ንግግር ሀገራችንን ምን አይነት መቀመቅ ውስጥ እንደሚከታት በማሰብ ድርጊቱ ይቆም ዘንድ ከዛሬ ሶስት ዓመት በፊት በአስፈሪው ወቅት እንደ ዜጋ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ጥረት አድርገናል። ምንም እንኳን ሀገራችንን ከከባድ የእርስ በእርስ መጠፋፋት፣ ከጦርነት በዚህም ምክንያት በሰው ልጆች ላይ ከሚደርሱት እርዛት ፣ ረሃብ ፣ ሰቆቃ ማዳን…
የቀጠለ👇

ሀገራችን ዛሬ ላለችበት ሁኔታ እርስ በእርስ ጣት መጠቋቆም አያዋጣንም። እኔ ምን ሳደርግ ነበር ? ብለን መጠየቅ አለብን።

ከዓመታት በፊት በየሚዲያው ላይ ፖለቲከኞች እርስ በእርስ ለፖለቲካቸው ሲሉ ሲሰዳደቡ ፣ ሲናናቁ እነሱን እንደ #ጀግና ቆጥረን መልዕክታቸውን ስናጋራ ፤ የጦርነት እና የግጭት መልዕክቶችን ስናበረታታ ፤ በየኮሜንቱ ስንሳደብ ፤ ሰዎችን በማንነታቸውና አመለካከታቸው ስናንቋሽሽ ፤ የእኔ ወገን ካልሆነ ምን አገባኝ በሚል ለሚፈፀሙ ግፎች ማብራሪያ ስንሰጥ ፤ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ጥላቻን የሚሰብኩ ሰዎችን ሃሳብ/ንግግር ስናበረታታ እና ስንደግፍ ... ይህ ሁሉ ለዛሬው ቀን ምን አይነት አስከፊ ውጤት አመጣ ? በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የእኔ አስተዋፆ ምን ነበር ? ብለን መጠየቅ አለብን።

ዛሬ ሀገሪቱ ላለችበት ሁኔታ እኔ ምን ሳደርግ ነበር? ጓደኞቼስ ፣ ወዳጆቼስ ፣ የምደግፋቸው ፖለቲከኞችስ ፣ አክቲስቶችስ ፣ የምክተታላቸው ሚዲያዎችስ ? ብለን መጠየቅ አለብን። ችግር እና ሰቆቃ ሲመጣ እራስን ፃዲቅ እና ንፁህ አድርጎ ከችግሩ ራስን አርቆ ሃጥያትን ሙሉ ሌላው ላይ ለመከመር መሞከር ልክ ነው ብለን አናምንም። ችግርንም ከማባባስ ውጭ ፈፅሞ ሊፈታ አይችልም።

አሁንም ስለዛሬ ብቻ ሳይሆን ስለነገው አስከፊ ቀን በማሰብ ትውልድ መታደግ ይገባል። ዛሬ እናት ፣ አባቱን ፣ ወንድም ፣ ዘመዱ፣ አሉኝ የሚላቸውን ሲነጠቅ ፣ በለጋነት እድሜው በማንነቱ ሲሳደድ ፣ ሲፈናቀል ፣ የረሃብ አለንጋ ሲገርፈው በአእምሮው ምን ሊያስብ ይችላል ? ብለን መጠየቅ አለብን።

ይቀጥላል👇