TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SolianaShimeles

የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት ፦

ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ (የምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ) ስድስተኛው (6) አገራዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ለኢፕድ ተናግረዋል።

ለምርጫው የተገዙት ቁሳቁሶቹ እንዲሁም ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶች እና ህትመቶች የተለዩ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ብለዋል።

የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ እና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው ፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝ እና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱት ምርጫዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማጭበርበሮችን የሚያስቀሩ የምርጫ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል። ~ EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#SolianaShimeles #NEBE

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚሰበስበው የእጩዎች ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሀይማኖት ስብጥር አያሳይም ሲሉ ተናገሩ።

ኃላፊዋ ይህን ያሉት ሀገራዊ ምርጫውን የሚሳተፉ እጩዎችን ቦርዱ በሀይማኖት ለይቶ እንደመዘገበ የሚጠቁም መረጃ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተነገረ መሆኑን ተከትሎ ስለጉዳዩ እውነትነት ከኢትዮጵያ ቼክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነው።

አንዳንድ አካላት የእጩዎችን የ "ሀይማኖት ስብጥር ዝርዝር" ያሳያል ያሉትን መረጃ ከምርጫ ቦርድ እንዳገኙ በመጥቀስም ሲያሰራጩ ነበር።

ወ/ሪት ሶልያና ፥ "ቦርዱ ሲጀምር በጠቅላላ 9 ሺ የሚሆኑትን የእጩዎች ዝርዝር መረጃን እስካሁን ይፋ አላረገም" ብለዋል።

አክለውም፥ ቦርዱ የሚሰበስበው የእጩዎች ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሀይማኖት ስብጥርን አያሳይም ሲሉ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ፥ "እኛ የእጩዎች ሃይማኖት የሚጠይቅ ዶክመንት አንጠይቅም ፣ ስለዚህ ከምርጫ ቦርድ ተገኘ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የሀሰት ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

#ኢትዮጵያ_ቼክ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ማስታወሻ ፦

ከነገ ሀሙስ ጀምሮ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም።

- ሁሙስ
- አርብ
- ቅዳሜ
- እሁድ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም።

ይህ ማለት፦ ፓርቲዎች ማንኛውም አይነት ስብሰባ ማድረግ አይችሉም ፣ ቤት ለቤት እየሄዱ ምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም፣ ወረቀት ፍላየር መበተን አይችሉም፣ የአደባባይና የአዳራሽ ስብሰባ ማድረግ አይችሉም፣ የኢንተርኔት (ኦንላይን) የማህበራዊ ሚዳያ የምረጡኝ ዘመቻ ማድረግ አይችሉም።

#SolianaShimeles #ሰኔ14እመርጣለሁ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ #ምርጫ_እንዳይካሄድ ተወስኖባቸዋል።

- ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር አይተው ተገኝቷል፤ በዚህ ምክንያት 3 አስፈፃሚዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ደብዳቤ ተፅፏል።

ደምቢያ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን መነካካት ፣ መክፈት በጥብቅ የተከለከለ የወንጀል ተግባር በመሆኑን አስፈፃሚዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው ተልኳል።

በደምቢያ ምርጫ ክልል ምርጫው #አይካሄድም

- ተውለደሬ 1 እና 2 ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያሉእጩዎች እነማን እንደሆኑ ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ያሉትን እጩዎች የማየት (ፓርቲዎች ቅሬታ አለን ስላሉ ነው እዩ ተብለን ነው) በሚል ተክፍቶ ታይቷል።

በዚህ ምክንያት ተውለደሬ 1 እና 2 ነገ ድምፅ አይሰጥም፤ ታግዷል።

- ግንደበረት (ኦሮሚያ) ነገ ድምፅ #አይሰጥም ፦ ድምፅ የማይሰጥበት ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀት እና ቁሳቁስ ስለተከፈተ ሳይሆን የአስፈፃሚዎች እጥረት ነበር። ከዚህ ውጭ ግን ወረዳው አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ ለማስፈፀም ለማሰማራት ሲል በመገኘቱ ገንደበረት ላይ ድምፅ አይሰጥም።

- ነገሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ-ኦሮሚያ) ፦ በምርጫ ክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ቦርዱ ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮታል።

#TikvahEthiopia #SolianaShimeles

@tikvahethiopia
#SolianaShimeles

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 /2014 ዓ/ም ለሚያካሂደው ምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ ምርጫው በሶማሊ፣ ሐረሪ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በተያዘለት መርሀ ግብር መስከረም 20/2014 ይካሄዳል ብለዋል።

አስፈላጊው ዝግጅትም ከወዲሁ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ በዕለቱ ከምርጫው ጋር ጎን ለጎን አብሮ እንደሚካሄድ ወ/ሪት ሶሊያና ገልፀዋል።

Credit : ኢፕድ
Photo : Tikvah Family

@tikvahethiopia