TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአማራና ትግራይ ክልሎች በጋራ እየሰሩ ነው!

የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የአማራና የትግራይ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ። የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛት አብዩ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የአማራና የትግራይ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበር መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፥ ሁለቱ ክልሎች በዓሉን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ መስማማታቸውን ተናግረዋል።

በዓሉን “የኢትዮጵያ ልጃ ገረዶች ጨዋታ” በሚል ስያሜ በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ቅርስነት ለማስመዝገብ በሁለቱ ክልሎች መካከል እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክክር ተደርጎ ስምምነት ላይ መደረሱን አክለዋል።

ዩኔስኮ በዓሉን በቅርስነት ለመመዝገብ ሒደት ላይ መሆኑን ያነሱት አቶ ግዛት፥ ኢትዮጵያም በዓሉን በቅርስነት ለማስመዝገብ ስትሰራ መቆየቷን አስታውሰዋል። #የሻደይ_አሸንዳ በዓል የሀገር ቅርስ ሆኖ በዩኒስኮ የሚመዘገብ ሲሆን፥ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚከበር መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል። የሴቶች ዕኩልነት፣ ነፃነትና አንድነት ተምሳሌት የሆነው የሻደይ አሸንዳ በዓል ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን አቶ ግዛት አንስተዋል።

በዓሉ በአማራ ክልል በወረዳና በዞን ደረጃ ከነሃሴ 16 እስከ 18 ቀን 2011ዓ.ም የሚከበር ሲሆን፥ በክልል ደረጃ ደግሞ በባህር ዳር ከተማ ከነሃሴ ከ19 እስከ 20 ቀን በድምቀት የሚከበር መሆኑ ተገልጿል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NewsAlert ዛሬ የመን ኤደን ከተማ ላይ ይካሄድ በነበረ ወታደራዊ ሰልፍ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት ብዛት ያላቸው ተገደሉ። በሌላ የከተማዋ አካባቢ ደግሞ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏷"የአማራ ሕዝብ የትግራይ ወንድም ሕዝብ ነው። እኛ ሕዝቡን #ትምክህተኛ አላልነውም። በየትኛውም አለም ሕዝብ እንደ ሕዝብ ትምክህተኛም ጠባብም ወይ ሌላም ሊሆን አይችልም» ... «ወደ 1968 ዓ.ም ተመልሰው ድሮም እንደዚህ ነበራችሁ ማለት አያስፈልግም ነበረ። እኛ ያልነው አጭርና ግልፅ ነው። በውስጣችሁ ምን ችግር ነው ያጋጠመው? አጥሩት ነው ያልነው፡፡ አንድ ድርጅትና ወንድም ህዝብ ነን እኮ» ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ዲያስፖራ ሲምፖዝየም (#ሕወሓት)

Via #እሸት_በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ አስጠራው ከበደ እና በእነ ሲያምር ጌቴ መዝገብ የተጠረጠሩ የአብን አመራሮችና አባላት በዋስ እንዲወጡ የተሰጠውን ውሳኔ ውድቅ እንዳደረገ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ/አብን/ በፌስቡክ ገፁ ገለፀ።

በእነ አስጠራው ከበደ እና በእነ ሲያምር ጌቴ መዝገብ የተከሰሱት የአብን አመራሮችና አባላት በብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም አቃቢ ሕግ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ይግባኙን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የተፈቀደውን ዋስትና መብት ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል፤ ችሎቱ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ/ም መዝገቡን ቀጠሯል ሲል ንቅናቄው ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢንተርኔት #መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን #ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው #ሊዘጋ ይችላል!" ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«የጄኔራል ሰዓረ ገዳይ ወታደር መሳፍንት ጥጋቡ «ስለ ቆሰለ እስካሁን በሕክምና ላይ ይገኛል፣ የቆሰለው አንገቱ አካባቢ ስለሆነና መናገር ስለማይችል አዳዲስ ነገር አልተገኘም። በደንብ ሲሻለው የበለጠ መረጃዎች ይገኛሉ» ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግሥት:-

* የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ይሰራል

መንግሥት በቀጣይ ዓመት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር በአቅርቦት ላይ በመመስረት በስፋት እንደሚሰራ ገለጸ። በሰኔ 15ቱ ግድያ ላይ መንግሥት በቂ መረጃ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ ባለፉት 15 ዓመታት የዋጋ ንረቱ 15 በመቶ እያደገ ቢቆይም ባለፈው ዓመት ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት መቀነስ ተችሏል። ሆኖም ግን ከግንቦት/2011 ዓ.ም ወዲህ ግን አሻቅቧል ብለዋል።

የዛሬ 28 ዓመት የኢትዮጵያ ሕዝብ 48 ሚሊዮን ነበር። አሁን ከ100 ሚሊዮን በላይ ቢደርስም የሚታረሰው መሬት ግን ያው መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የፍላጎትና የአቅርቦት ያለመመጣጠንን ችግር ለማቃለል ምርታማነቱ የተወሰነ ለውጥ ቢያመጣም የሚፈለገው ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር ዝግጅቷን እያደረገች ነው!

ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል ጨዋታዎችን ለማክበር ባሕር ዳር መዘጋጀቷን የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ የልጃገረዶች ጨዋታ›› በሚል ስያሜ በዩኒስኮ ለማስመዝገብ ሙሉ መረጃ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡ የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ከባለፈው ዓመት በደመቀ መልኩ ባሕር ዳር ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል ጨዋታዎችን ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከየምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ 20 አንቀጾች እንዲሰረዙ 13 እንዲሻሻሉ በዛሬው ዕለት ጠይቀዋል ጠይቀዋል። የመንግሥት ሰራተኞች ለምርጫ ሲወዳደሩ ሥራቸውን ሊለቁ ይገባል የሚለው አጨቃጫቂ ሆኗል። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ አቶ ገረሱ ገሳ «የመንግሥት ሰራተኞች መልቀቅ ካለባቸው ከጠቅላይ ምኒስትሩና አፈ-ጉባኤው ጀምሮ መልቀቅ አለባቸው» ብለዋል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ፣ ሐምዛ ቢን ላደን፣ 'በአየር ጥቃት መገደሉ' ተነገረ!

የአልቃይዳ መስራች የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን ወንድ ልጅ፣ ሐምዛ ቢን ላደን፣ በአየር ጥቃት ወቅት መገደሉን የአሜሪካ የስለላ ባለስልጣናት ጠቅሰው የአሜሪካ መገናኛ ብዙኀን ዘገቡ። ሐምዛ መቼና የት እንደሞተ የተነገረ ምንም ነገር የለም። ፔንታጎንም በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን አልሰጠም።

የካቲት ወር ላይ የአሜሪካ መንግሥት ሐምዛ የት እንዳለ ለጠቆመ የአንድ ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር።

ሐምዛ ቢን ላደን ዕድሜው 30 የሚገመት ሲሆን፣ አሜሪካና ሌሎች ሀገራት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም የሚጠይቅ የቪዲዮና የድምፅ መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይህ ዘገባ መጀመሪያ ላይ የወጣው በኤንቢሲ እና በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ ነው።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ሆኑ የኋይት ሐውስ የሀገር ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልቶን በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ሐምዛ ቢን ላደን አባቱን በጎርጎሳውያኑ 2011 ግንቦት ወር ላይ የገደሉት አሜሪካኖች ላይ ጂሀዲስቶች ጥቃት እንዲፈፅሙ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Hamza-08-02

Via #BBC_Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

በአምስቱም የአዲስ አበባ መውጪያና መግቢያ በሮች አርሶ አደሮች ምርታቸውን የሚያስቀምጡባቸውንና ለገበያ የሚያቀርቡባቸውን ማእከላት ለመገንባት መታቀዱን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። የከተማዋ ነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለልም አንድ ሺህ 500 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

የ2011ን በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተናገሩት፤ በአምስቱም የአዲስ አበባ መውጪያና መግቢያ በሮች ላይ አርሶ አደሮች ምርታቸውን የሚያስቀምጡባቸውንና ለገበያ የሚያቀርቡባቸውን ማእከላት ለመገንባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ናቸው።

በተጨማሪምበተመጣጣኝ ዋጋ ለከተማው ነዋሪ የሚያቀርብ ግዙፍ የዳቦ ማምረቻ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ተደርጎለት ወደ ግንባታ ስራ በመግባት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን ለሚያመርቱ ሌሎች ኢንቨስትመንቶች የተለየ ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
15 ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ሞቱ!

ከዘጠና በላይ ስደተኞችን አሳፍራ #ከጅቡቲ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ የነበረች የአሳ ማስገሪያ ጀልባ በመሰባበሯ ለጠና ረሃብና ጥም መጋለጣቸውንና አንዳንዶቹም በተስፋ መቁረጥ ጭምር ራሳቸውን ወደ ባህሩ ወርውረው ለሕልፈት መዳረጋቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት /IOM/ አስታወቀ።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ UCodeGirl እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትብብር ከሐምሌ 24 እስከ ሐምሌ 28 /2011 ዓ.ም ያዘጋጁት የኮዲንግ ስልጠና እንደቀጠለ ነው!
.
.
🎁በስልጠናው #ማጠቀቂያ የስለጠናው ተካፋይ የሆኑ ሴት ተማሪዎች ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ከITU እና UN በስጦታ ይበረከትላቸዋል።

Via #DG/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴሌኮም እና የመብራት አገልግሎት ይሟላል!

#በምዕራብ እና #ሰሜን ጎንደር ዞኖች #አብዛኛዎች አካባቢዎች የቴሌኮምና የመብራት አገልግሎት #እንደሚሟላ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በስሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ባለፈው የእሳት አደጋ በደረሰበት ቦታ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ፣ የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች ችግኝ መትከላቸው ይታወሳል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎችም የተንቀሳቃሽ ስልክ ‹‹ኔትወርክ›› እና የመብራት አገልግሎት እንዲሟላላቸው ጠይቀዋል፡፡ የስልክ አገልግሎት በፓርኩ ብቻ ሳይሆን በተለይ አዲስ በተዋቀሩት ሁለቱ ዞኖች (ምዕራብና ሰሜን ጎንደር) አብዛኛዎቹ አካባቢዎች እንደሌለ ነዋሪዎቹ አንስተዋል፡፡

ለችግኝ ተከላ እና የኢንቨስትመንት አካባቢዎችን ለመጎብኘት በአካባቢው የተገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይዎት ታምሩ በቀጣይ በሁለቱም ዞኖች አገልግሎቱ ተደራሽ እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በተለይም በምዕራብ ጎንደር ዞን እየተስተዋለ ያለውን የሱዳን ሲም ካርድ ሽያጭ ለማስቆም ጥረት እንደሚደረግ ነው የተናገሩት፡፡ ከጎብኝዎች የሚገኘውን ገቢ ከፍ ማድረግ እንዲቻል ቅርሶች ባሉበት አካባቢ የቴሌኮም አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ከመብራት ተደራሽነት ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ በሁለቱም ዞኖች የመብራት መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ውይይት እየተደረገ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
553 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ተመለሱ!

አምስት መቶ 53 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ በሳኡዲ አረብያ ጂዛን ግዛት ኢዋ እና ሲጂንነዓም በተሰኙ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 280 ኢትዮጵያውያን ትናንት ከሌሊቱ በ8፡30 ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ ከ5 ዓመት እስከ 30 ዓመት ድረስ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጅዳ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት በኩል የሳኡዲ መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸው በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ኢትዮጵያዊያኑ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮንሱላር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ እና ሌሎች አካላት በተገኙበተ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በተመሳሳይ በጅዳ እና ጂዛን ግዛት ያለ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 273 ኢትዮጵያውን ረቡዕ ማታ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ከነዚህ ተመላሾች ውስጥ 75ቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ሀገራት በእስር ላይ የሚገኙ ኢትጵያውያንን በማስፈታት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩም በፈቃደኝነት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘነው መረጃ ያሳያል።

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዱባይ ፖሊስ የማኅበራዊ ድረ ገፅ ተከታዮች ለማግኘት መንገድ ላይ ገንዘብ ሲበትን የሚያሳይ ቪዲዮ አሰራጭቷል ያለውን ሰው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ኮሎኔል ፋይሳል አል-ቃሲም የተባሉ የፖሊስ መኮንን በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኘው ተጠርጣሪ ጥፋቱን መፈጸሙን አምኗል ብለዋል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀጅ ፀሎት ዝግጅት ተጠናቋል!

ሳውዲ አረቢያ በቀጣይ ሳምንት ለሚጀምረው የሐጅ ጸሎት ሲደረግ የነበረው ዝግጅት መጠናቀቁን አስታወቀች። የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ዝግጅቱ 17 ሺህ ተንቀሳቃሽ ሲቪል አደጋ ተከላካዮችን፣ በተለያዩ መስጊዶች ውስጥ የሚቀሩ 100 ሰዎችን እና 14 ሺህ የሀገር ውስጥ እና የውጭ በረራዎችን የሚያካትት ነው።

በአጠቃላይ 30 ሺህ ሠራተኞች፣ መንገድ መሪዎች እና የደህንነት አባላት እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል። የመካ ክፍለ ሀገር ገዥ ካሊድ ቢን ፈይሰል አል ሳውድ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሁሉም የሀገሪቱ የመንግሥት እና ሲቪል ተቋማት ለተጓዦች አገልግሎት እና ምቾት ለመስጠት ሁሉንም ዓይነት ዝግጅት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ባለፈው ዓመት 2.5 ሚሊዮን ተጓዦች በእስልምና እምነት ቅዱስ ወደ ሆነችው መካ ጉዞ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ ደይሊ ሜይል/etv/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
7ኛው የበጎ ሰው ተሸላሚ እጩዎች ታወቁ!

ለ7ኛው የበጎ ሰው ሽልማት 291 ሰዎች ተጠቁመው 27 እጩዎች ለዳኞች ውሳኔ ቀርበዋል ከእነዚህም መካከል፦

በመምህርነት ዘርፍ

1ኛ ፕሮፌሰር ሽታዬ አለሙ
2ኛ ወ/ሮ ህይወት ወልደመስቀል
3ኛ ዶ/ር መስከረም ለቺሳ

በሳይንስ (ህክምና፣ቴክኖሎጂ፣ፊዚክስ፣ምህንድስና፣ኬሚስትሪ፣አርክቴክቸር፣ወዘተ)

1ፕሮፌሰር ለገሰ ነጋሽ
2ኛ ፕሮፌሰርሰብስቤ ደምሴ
3ኛ ዶክተር ታደለች አቶምሳ

በኪነ ጥበብ/ሥነ ጥበብ፣በፎቶ ግራፍ ዘርፍ)

1ኛ አቶ ሚካኤል ፀጋዬ
2ኛ አቶ በዛብህ አብተው
3ኛ አቶ ዳኜ አበራ

በበጎ አድራጎት(ርዳታና ሰብአዊ አገልግሎት)

1ኛ ዶ/ር ጀምበር ተረፈ
2ኛ አብድላዚዝ አህመድ
3ኛ ላሌ ለቡኮ

በንግድና ስራ ፈጠራ ዘርፍ

1 ዳንኤል መብራቱ
2ኛ አቶ ክቡር ገና
3ኛ ነጋ ቦንገር

በመንግስታዊ የስራ ተቋማት ሀላፊነት

1ኛ አቶ በትሩ አድማሴ
2ኛ ዶር አሚር አማን
3ኛ አቶ ግርማ ወንዳፍራሽ

በቅርስና ባህል ዘርፍ

1ኛ አብዱልፈታህ አብደላ
2ኛ አድማሴ መላኩ
3ኛ ሳሙኤል መኮነን (ከጎንደር)

በሚዲያና ጋዜጠኝነት

1ኛ አቶ በልሁ ተረፈ
2ኛ አቶ አማረ አረጋዊ
3ኛ ወ/ሮ አንድነት አማረ

በኢትዮጵያ እድገት አስተዋፅኦ ያበረከቱ ዲያስፖራዎች

1ኛ አቶ ኦባንግ ኡሜቶ
2ኛ አርቲስት ታማኝ በየነ
3ኛ ፕሮፌሰር ፀጋዬ ታደሰ

በመሆን የታጩ ሲሆን ከእያንዳንዳቸው ዘርፎች 1ኛ አንደኛ የሚወጡት ደግሞ ነሀሴ 26/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አሸናፊዎች ተለይተው ይሸለማሉ፡፡

Via #ethiofm
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአገሪቱ የነበረው ፖለቲካ አለመረጋጋት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ጫና በመፍጠሩ የቱሪስቶች ቁጥር በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉን ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፉ በ2011 በነበረው የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄዷል፡፡

ሚኒስቴሩ በዓመቱ የነበረውን አፈፃፀም ከተጠሪ ተቋማት እና ከሴክተሮች ጋር በአዳማ ከተማ እየገመገመ ነው። ሚኒስትሯ ዶ/ር ሒሩት ካሳው እንዳሉት፣ በለውጡ ጉዞ በቅርስ ልማት እና ክብካቤ የሀገሪቱ ጎብኝዎቹ ቁጥር እንዲጨምር እና ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲኖር ውጤታማ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ሚኒስትሯ ተጠሪ ተቋማትን እና ክልሎችን በመደገፍ እንዲሁም የወጡ ፖሊሲዎችን በመተግበር የተደረገው ጥረት የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በበጀት ዓመቱ ችግሮችም እንደነበሩ አስታውሰዋል።

በተለይም በሀገሪቱ የተፈጠረው አለመረጋጋት በዘርፉ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያለው በመሆኑ በጎብኚዎች ቁጥር እና እንቅስቃሴ ላይ ጫና እንደፈጠረ ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት የቱሪስቶች ቁጥር በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉ ተገልጿል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏷"ጋዜጠኝነት ማህበረሰብን #የማንቂያ ሙያ እንጂ የወንጀለኞች መደበቂያ ምሽግ አይደለም" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ትላንት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

በንግግራቸውም ለአገር ሰላምና አንድነት የሚጨነቁና የሚሰሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ሁሉ፤ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ህዝብን ለማጋጨት ጊዜያቸውን በከንቱ ያጠፋሉ ብለዋል። በተለይ ጋዜጠኝነት የማህበረሰብ ማንቂያ መሆኑን ረስቶ በሙያው ስም በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ሲፈጽም የሚውል ሰው አለ ነው ያሉት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌስቡክ

ፌስቡክ ከሳውዲ አረቢያ ጋር የተገናኙ #የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የሚሰራጭባቸው መለያዎችን የሚጠቀሙ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዳሉ ደርሸበታለሁ በሚል መለያዎችን አገደ፡፡ ዘመቻው መካከለኛው መስራቅን እና ሰሜን አፍሪካ ላይ ያነጣጠረ እንደሁነና የመልዕክቱ ይዘት በአብዛኛውም በአረበኛ ቋንቋ የሚተላለፍ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል ፌስቡክ። እስካሁን ድረስም ከ 350 በላይ የሃሰት አካውንቶችን ዘግቻለሁ ብሏል። ሳውዲ ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት አስተያየት እንዳልሰጠች ተገልጿል።

Via ቢቢሲ/#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia