TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአማራና ትግራይ ክልሎች በጋራ እየሰሩ ነው!

የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የአማራና የትግራይ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ። የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛት አብዩ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የአማራና የትግራይ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበር መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፥ ሁለቱ ክልሎች በዓሉን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ መስማማታቸውን ተናግረዋል።

በዓሉን “የኢትዮጵያ ልጃ ገረዶች ጨዋታ” በሚል ስያሜ በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ቅርስነት ለማስመዝገብ በሁለቱ ክልሎች መካከል እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክክር ተደርጎ ስምምነት ላይ መደረሱን አክለዋል።

ዩኔስኮ በዓሉን በቅርስነት ለመመዝገብ ሒደት ላይ መሆኑን ያነሱት አቶ ግዛት፥ ኢትዮጵያም በዓሉን በቅርስነት ለማስመዝገብ ስትሰራ መቆየቷን አስታውሰዋል። #የሻደይ_አሸንዳ በዓል የሀገር ቅርስ ሆኖ በዩኒስኮ የሚመዘገብ ሲሆን፥ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚከበር መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል። የሴቶች ዕኩልነት፣ ነፃነትና አንድነት ተምሳሌት የሆነው የሻደይ አሸንዳ በዓል ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን አቶ ግዛት አንስተዋል።

በዓሉ በአማራ ክልል በወረዳና በዞን ደረጃ ከነሃሴ 16 እስከ 18 ቀን 2011ዓ.ም የሚከበር ሲሆን፥ በክልል ደረጃ ደግሞ በባህር ዳር ከተማ ከነሃሴ ከ19 እስከ 20 ቀን በድምቀት የሚከበር መሆኑ ተገልጿል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia