ፌደራል ፖሊስ~ድሬዳዋ ቅርንጫፍ‼️
በሕገ-ወጥ መንገድ ከድሬዳዋ ተጭኖ ወደ ሐርጌሌ ሊጓጓዝ የነበረ ነዳጅና አምስት #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የጽህፈት ቤቱ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ አቶ #ሞገስ_አያሌው ለኢዜአ እንዳመለከቱት ከከተማው ሊወጣ ሲል የተያዘው 20ሺህ ሊትር ናፍጣ፣ 16 ጀሪካን የሞተር ዘይትና በድርጊቱ የተጠረጠሩት ግለሰቦች ናቸው፡፡ በተለይ ነዳጁ የተያዘው በአንድ የጭነት መኪና ከነተሳቢው በጄሪካን ተጭኖ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ነዳጁን በከተማው ከሚገኝ አንድ ነዳጅ ማደያ ገዝተው ሊያጓጓዙ የነበሩት ግለሰብና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ለግለሰቡ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ መሰጠቱ አግባብ አለመሆኑን ያስረዱት ባለሙያው፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ነዳጅን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚከናወነውን እንቅስቃሴ በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም ሕገ-ወጥ ተግባር ለፖሊስ በማሳወቅ ትብብሩን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
ነዳጁ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ጥቆማ ከሰጡት አንዱ ለኢ ዜ አ እንዳስታወቁት በከተማዋ #የነዳጅ_እጥረት የሚከሰተው በሕገ ወጥ መንገድ በሚካሄደው ንግድ ነው፡፡ ”የቤንዚኑ ችግር ሳይፈታ ናፍጣ ቢወደድ ሌላ ችግር ስለሚፈጥር ጉዳዩን ጠርጥረን ለፖሊስ አሳውቀናል። ትብብራችንም ይቀጥላል”ብሏል፡፡
#ሐርጌሌ በሶማሌ ክልል ከድሬዳዋ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ መንገድ ሊጓዝ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia