TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል #በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ #ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለfbc እንደተናገሩት፥ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት #ህይወት አልፏል

ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

የወገኖቻንን ህይወት እየቀጠፈ ፤ ንብረትም እያወደመ ያለው የጎርፍ አደጋ !

በያዝነው ክረምት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ ንብረትም እየወደመ ነው።

ለአብነት በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ ህፃናት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ንብረት ወድሟል፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ የአርሶ አደሮች ንብረትም እንዳልነበር ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን ማና ወረዳ ሃሮ ቀበሌ እንደተሰማው የአንድ ቤተሰብ አባላትን የሆኑ ወገኖቻችን በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አልፏል

ከወረዳዋ ከተማ የቡ ተነስተው ሃሮ ወደተባለች ቀበሌ 3 ልጆቻቸውን ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ቤተሰብ አንድ የ13 ዓመት እና ህጻን ልጅ በደራሽ ጎርፍ ሲወሰዱ አንድ ታዳጊ በህይወት ማግኘት ተችሏል።

በጎርፉ ከተወሰዱት የቤተሰብ አባላቱ የአባት አስከሬን በዕለቱ ሲገኝ፤ የሟች እናትና ሁለት ልጆች አስከሬን ትላንት ጠዋት ተገኝቷል።

የቤተሰብ አባላቱ ፤ በጎርፉ የተወሰዱት ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ በነበረበት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የወረዳውን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።

በአማራ ክልል በአምባሰል ወረዳ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እና በመሬት መንሸራተት ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል።

በአጠቃላይ 150 አባወራዎች እና እማወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከል፣ በገበሬ ማሰልጠኛዎችና በዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው በቂ ለድጋፍ የሚሆን ሐብት ባለመኖሩ ለተጎጅዎች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑን በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል ፤ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፤ ከፍተኛ የሀብት ጥፋትም ደርሷል።

በሠመራ ከተማ ብቻ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች #ህይወት_አልፏል

በኤሊደአር  ወረዳ  ዶቢ ቀበሌ ደግሞ በጎርፍ አደጋ ከ3 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የጨው ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በአካባቢው ላይ ከ300 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች በጨው ምርት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ሁለት መቶ  የሚሆኑት አምራቾች በጎርፉ ምክንያት ኪሳራ ደርሶባቸዋል።

በተጨማሪም ጨው ለማምረት ተዘጋጅተው የነበሩ የጨው ማምረቻ ቦታወችም በጎርፉ ምክንያት ተበላሽተዋል።

አንድ አምራች የምርት ቦታዎችን ለማዘጋጀት ከ200 ሺ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል የተባለ ሲሆን ባጠቃላይ አምራቾች ላይ የደረሰው ኪሳራ ቀላል ሊባል የሚችል አይደለም።

በተጨማሪም ፤ በአሳይታና አፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቤት እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አሳይታ በርጋ ቀበሌ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል፣ ቤታቸው እንዳልነበር ሆኗል ፣ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ ላይ ጉዳት አድርሶባቸዋል።

በአሁን ሰዓት ከቤታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ናቸው።

የመንግስት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሚሰጡ ተቋማት በውሃ ውስጥ ናቸው ያሉት።

በተመሳሳይ ፤ በአፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላትና በከባንድ ዝናብ ሳቢያ ቤት ንብረታቸው በጎርፍ አደጋ እንዳልነበር ሆኗል እነሱም ተፈናቅለዋል ፤ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ እነኚህ ወገኖቻችን የመንግስት ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚሁ ወረዳ 6 ሺህ ሄክታር የጥጥ እና ሰሊጥ እርሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ፣ ከኤሊዲአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን፣ ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ፣ ከአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia