TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አፋልጉን!

0911334007
0912466134
0912242199

#share #ሼር
6 ቀን ቀረው! #እንገናኝ

የዚህ ገፅ ባለቤቶች ሁላችሁም እንደሆናቹ ታውቃላችሁ። ላለፉት አመታት ከተቸገረው ጋር ስትቸገሩ የቆያችሁ፣ በየቦታው ሰላም ሲደፈርስ ቁጭ ባላችሁ ስትጨነቁ ስታድሩ የቆያችሁ፣ እውነተኛና በአይናቹ ያያችሁትን የተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ስታደርሱ የቆያችሁ፣ የታመሙትን #ስታሳክሙ የቆያችሁ፣ በሀዘን ወቅት #ብሄር እና #ዘር ሳትለዩ ስለሰው ልጅ ሁሉ ስታለቅሱ የነበራችሁ፣ ለሀገራችሁ ሰላም መሆን የበኩላችሁን ድርሻ ስትወጡ የቆያችሁ፣ ለመልካም ነገሮ ቀድማችሁ ስትደርሱ የነበራችሁት እናተው ናችሁ!! አዎን ክብር ይገባችኃል!! በሰውነት ጥላ ስር ያሰባሰብን፤ በልዩነቶቻችን የምንከባበርበት፤ በንግግር ችግሮችን የምንፈታበት፤ ጥላቻን የምንፀየፍበት፤ ለሀገር ሰላም ቅድሚያ የምንሰጥበት TIKVAH-ETH #ቤታችን ከተመሰረተ እንሆ ሁለተኛ አመቱን ሊያከብር ሀምሌ 21 ቀጠሮ ይዟል። የዚህ ገፅ ባለቤት #እኔም ነኝ የምትሉ ሁሉ ይህ ቀን የናተ ነውና እሁድ ሀምሌ 21 በአበበች ጎበና ሕፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት ተገኙ፤ ከእናታችሁም #ምርቃት ተቀበሉ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ

"ዛሬ ከጠዋት እስከማታ ድረስ የነበረውን ሁኔታ ስንከታተል ነው የዋልነው የስራው ባለቤት ዕድሜው ከ 24-26 የሚገመት በጣም ወጣት የሚባል አይነት ነው ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት አካባቢ በፖሊስ ታጅቦ ልደታ በሚገኘው የፍሊንትስቶንስ ህንፃ ወደተከራየው ቢሮ መጥቶ ነበር ወደ 1400 ያክል ተመዝጋቢ እንደነበር እና ወደ 3.4 ሚሊዮን ብር አካባቢ እንደሰበሰበ ሰምተናል አንዲት አብራው የምዝገባውን ስራ የምትሰራ ፀሀፊም ታስራ መጥታ ነበር የቅጥር ውል ብቻ እንዳላት እና ሌላውን ነገር እንደማታውቅ ተናግራለች ብዙ ግርግር ነበር ፖሊሶችም ክፍያውን በባንክ የፈፀመ እና ሲፒኦ እጁ ላይ የሚገኝ ተመዝጋቢ ፖሊስ ጣቢያ መጥቶ እንዲያመለክት እና ገንዘቡ ተመላሽ የሚሆንበትን መንገድ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል!" Abi ነኝ~የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል

🏷20 ሺ ሰው ይፈለግበታል ለተባለው ለዚህ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ከአዲስ አበባ ራቅ ካሉ ከተሞች /ከጎንደር እና ከነቀምቴ ሳይቀር/ ወጣቶች ለማመልከት መጥተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ለክልሉ ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአማራ መገናኛ ብዙኻን ዛሬ ባስተላለፉት ማብራሪያ የሰኔ 15ቱ የባለ ሥልጣናት ግድያ ወንጀል ምርመራ እስካሁን ያልተጠናቀቀው ወንጀሉ ውስብስብና ምርመራው ዘርፈ ብዙ ስለሆነ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርብ ዝርዝር ሪፖርት እናቀርባለን ብለዋል፡፡ ሴራውን በማክሸፋችን ክልላችን ከመፍረስ አድነነዋል፤ ባንቆጣጠረው ኖሮ ግን የባሰ ትርመስ ይፈጠር ነበር ብለዋል፡፡ እስካሁን በተደረሰበት ድምዳሜ ከጀርባ ስላሉ አካላት ይህ ነው ተብሎ የሚቀርብ ድምዳሜ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ አማራን በጎጥ ለመከፋፈል #ፌስቡክ ላይ የሚሰሩ ሃይሎች ግን ከባድ ችግር ስለፈጠሩብን መንግሥት ያግዘን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

ሶማልያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ በትንሹ 17 ሰዎች #መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘገበ። የሞቃዲሾ ትልቁ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሓመድ ዩሱፍ እንደገለፁት፣ ሌሎች 28 ቁስለኞች ሆስፒታል ገብተዋል። አደጋው የደረሰው አንድ ተጠርጣሪ አጥፍቶ ጠፊ፣ ይጓዝባት የነበረችውን ተሽከርካሪ፣ ሕዝብ በሚበዛበት የሞቃዲሾ አውራ-ጎዳና መጋጠሚያ ላይ በማፈንዳቱ እንደሆነም ተገልጿል። ለፍንዳታው አል-ሻባብ ኃላፊነት መውሰዱንም አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ካለፈው ሐሙስ ወዲህ በተከሰተ ተቃውሞ፣ ግጭት እና ሁከት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 60 መጠጋቱን ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) አስታወቀ። የሲአን ዋና ጸሐፊ አቶ ለገሠ ላንቃሞ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በይርጋለም፣ አለታ ወንዶ እና ለኩ ከተሞች እንደዚሁም ከሁላ (ሀገረ ሰላም) እና ማልጋ ወረዳዎች ባሰባሰቡዋቸው መረጃዎች የሟቾቹ ቁጥር ቀድሞ ከነበረው አሻቅቧል።

ዛሬ ወደ ማልጋ ወረዳ መጉዋዛቸውን የተናገሩት ዋና ጸሐፊው ከቀናት በፊት የወረዳው ነዋሪዎች ከመከላከያ እና ከልዩ ኃይል ጋር በተጋጩበት ወቅት ከቆስሉት መካከል የተወሰኑት በመሞታቸው በዚያ የነበረው የሟቾቹ ቁጥርም ጨምሯል። በማልጋ ወረዳ በፀጥታ ኃይሉ እና በሕዝቡ መካከል በተፈጠረ ግጭት የሞቱት ቁጥር 14 እንደነበረ የተናገሩት አቶ ለገሠ ከቆሰሉት ውስጥ 4 ተጨማሪ ሰዎች በመሞታቸው የሟቾች ቁጥር 18 መድረሱን አስረድተዋል። በሌሎች ከተሞች ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩንም ገልጸዋል።

«ማልጋ ዛሬ የሄድኩት ቀብር ነበር እና የቆሰሉ ሰዎች ነበሩ፤ በእለቱ ያልሞቱ እነዛም የቆሰሉትም ሞተዋል። በዛ ቀብር ላይም ነበርኩ። ይርጋለምም አምስት ነበር የሞተው፤ አለታ ወንዶ ላይ አንድ ሞቷል። ለኩ ላይ አምስት ሞቷል። በአጠቃላይ ከሀገረ ሰላሙ ጋር ወደ 60 እየተጠጋ ነው።» በማልጋ ወረዳ በተከሰተው ግጭት ሕዝቡ መደናገጡን የተናገሩት አቶ ለገሠ ባለሥልጣናት ህዝቡን የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ ናቸው ብለዋል። ሲአን በሲዳማ ባለው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ነገ በሐዋሳ መግለጫ እንደሚሰጥም አቶ ለገሠ ጨምረው ገልጸዋል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ/#ኢዜማ/ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል። መግለጫውን የሚሰጠው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢዜማ ጽሕፈት ቤት እንደሆነ ነው ፓርቲው የገለፀው። በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁሉም የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን እንዲገኙም ጥሪ አስተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባለ_1_መኝታ🔝

የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆናችሁ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ፦

የመከ/ሰራዊት ፋውንዴሽን #የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች እጣ የወጣላቸው እና የቤት እድለኞች ቼክሊስት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባለ_2_መኝታ🔝

የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆናችሁ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ፦

የመከ/ሰራዊት ፋውንዴሽን #የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች እጣ የወጣላቸው እና የቤት እድለኞች ቼክሊስት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባለ_3_መኝታ🔝

የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆናችሁ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ፦

የመከ/ሰራዊት ፋውንዴሽን #የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች እጣ የወጣላቸው እና የቤት እድለኞች ቼክሊስት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia