#ሲአን #ሲዳማ_ዞን #ሞረቾ #ወተረሬሳ #ሀገረሰላም
በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ በሞሮቾ ሶስት እና በሀገረሰላም ደግሞ ሁለት ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስረድተዋል።
በሐዋሳ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በግጭቱ የተጠረጠሩ 150 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከንቲባው ጠቁመዋል። ግጭቱን ተከትሎ የክልል እና የፌደራል አካላት ባደረጉት የማረጋጋት ስራ በሐዋሳ ከተማ እና በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን አቶ ስኳሬ ገልፀዋል። በሐዋሳ በዛሬው ዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደታየና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸው ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግን አሁንም ዝግ ናቸው።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#አዲስ_አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ የ2012 በጀት 47 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ተወሰነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማዋን የሆቴል ኢንቨስትመንት የሚያሳድግ ውሳኔም አሳልፏል።
ካቢኔው ዛሬ ሐምሌ 13 /2011 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያና የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የሆቴል ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እና ከተማዋን ግዙፍ የኮንፈረንስና የልዩልዩ ሁነቶች መስተናገጃ ወይም የማይስ(MICE) ማዕከል ለማድረግ የኮንቬንሽን ቢሮ እንዲከፈት ውሳኔ አሳልፉል፡፡ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ማሳደግ ፣ ኤግዚቢሽኖች መስፋት ፣ የንግድ ለንግድ ትስስሮች እና ኩነቶችን መጠናከር እና ወደ ከተማዋ የሚመጡ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ደረጃውን በጠበቀ ፕሮቶኮል እንዲስተናገዱ ማስቻል መዲናዋ የማይስ ማዕከል በመሆኗ የምታገኛቸው ዋና ዋና ጥቅሞች ናቸው።
በከተማው ካቢኔ የተቋቋመውን ይህን ማዕከል አቶ ቁምነገር ተከተል በዳይሬክተርነት እንዲመሩም ተሹመዋል። አቶ ቁምነገር የMICE East Africa ዋና አዘጋጅ ፣ የOZZIE ቢዝነስ አማካሪዎች ድርጅት ኃላፊ እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ልማት አማካሪ ቡድን ምክትል ሰብሳቢ ናቸው። 50ሺ ብር የሚገመት ወርሃዊ የስራ ጊዜያቸውን ለከተማ አስተዳደሩ በነፃ ለማገልገልም አቶ ቁምነገር ቃል ገብተዋል፡፡
በሌላ በኩል ካቢኔው የ2012 በጀት ዓመት የአስተዳደሩ በጀት 47.6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ወሰኗል። ረቂቅ በጀቱ በአስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።
እንዲሁም ካቢኔው ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የእዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትን በከፊል ወይም ሙሉለሙሉ ወደ ግል ለማዛወር ጥናት ተደርጎ እንዲቀርብም ውሳኔ አሳልፎዋል።
Via #ENA

TIKVAH-ETHIOPIA via @vote
8 ቀን ብቻ ቀረው! #እንገናኝ
የዚህ ገፅ ባለቤቶች ሁላችሁም እንደሆናቹ ታውቃላችሁ። ላለፉት አመታት ከተቸገረው ጋር ስትቸገሩ የቆያችሁ፣ በየቦታው ሰላም ሲደፈርስ ቁጭ ባላችሁ ስትጨነቁ ስታድሩ የቆያችሁ፣ እውነተኛና በአይናቹ ያያችሁትን የተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ስታደርሱ የቆያችሁ፣ የታመሙትን #ስታሳክሙ የቆያችሁ፣ በሀዘን ወቅት #ብሄር እና #ዘር ሳትለዩ ስለሰው ልጅ ሁሉ ስታለቅሱ የነበራችሁ፣ ለሀገራችሁ ሰላም መሆን የበኩላችሁን ድርሻ ስትወጡ የቆያችሁ፣ ለመልካም ነገሮ ቀድማችሁ ስትደርሱ የነበራችሁት እናተው ናችሁ!! አዎን ክብር ይገባችኃል!! በሰውነት ጥላ ስር ያሰባሰብን፤ በልዩነቶቻችን የምንከባበርበት፤ በንግግር ችግሮችን የምንፈታበት፤ ጥላቻን የምንፀየፍበት፤ ለሀገር ሰላም ቅድሚያ የምንሰጥበት TIKVAH-ETH #ቤታችን ከተመሰረተ እንሆ ሁለተኛ አመቱን ሊያከብር ሀምሌ 21 ቀጠሮ ይዟል። የዚህ ገፅ ባለቤት #እኔም ነኝ የምትሉ ሁሉ ይህ ቀን የናተ ነውና እሁድ ሀምሌ 21 በአበበች ጎበና ሕፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት ተገኙ፤ ከእናታችሁም #ምርቃት ተቀበሉ!

‹‹አሜሪካ የሁላችንም ናት፤ ታላቅ ሀገር የምትሆነው በብዝሃነት ስትደምቅ ነው፡፡›› ሚሼል ኦባማ
ሚሼል ኦባማ አሜሪካ የሁሉም ነዋሪዎቿ መሆኗን ተናገሩ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሰሞኑን #ስደተኞችን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ የቀደሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባለቤት ሚሼል ኦባማ ‹‹አሜሪካ የእኔም፣ የአንተም ሳትሆን የሁላችንም ናት›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡
የቀድሞዋ ቀዳማዊ እመቤት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሰሞኑን በትዊተር ገፃቸው በአራቱ ሴት የፓርላማ አባላት ‹‹አሜሪካን ለቅቀው ወደ መጡበት አገራቸው መመለስ ይችላሉ›› ማለታቸውን ተከትሎ የሰጡት መልስ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
አሜሪካ ታላቅ ሀገር የምትሆነው በብዝሃነት ስትደምቅ ነው ሲሉም ሚሼል ኦባማ ጠቅሰዋል፡፡ በሀገሪቱ የተወለደም ይሁን በስደት የመጣ ሁሉም በእኩልነት እና በአንድነት የበኩሉን ድርሻ ማበርከት ከቻለ አሜሪካዊ ለመሆንም፣ ለመባልም በቂ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- ዴይሊ ሜይል

#ኤልያስ_ገብሩ
ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡40 ሰዓት ላይ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሎ በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛና የባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ተብሎ የሚጠራው ምክር ቤት ጸሐፊ ኤልያስ ገብሩን፣ ፖሊስ ለምን እንዳሰረውና ከእስር እንደማይለቀው ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ሲሆን፣ ለትዕዛዙ መሰጠት ምክንያት የሆነው የታሳሪው ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ አካልን ነፃ የማውጣት (Habeas Corpus) አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡ጠበቃው የፍትሐ ብሔር ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 177 እና 205 ድንጋጌ መሠረት አድርገው ባቀረቡት አካልን ነፃ የማውጣት አቤቱታ እንዳብራሩት፣ ማንንም ሰው አስሮ ምርመራ የማድረግ ሥልጣን ለማንኛውም አካል የሚሰጠው በግልጽና በሕግ ብቻ ነው፡፡
ጋዜጠኛው ታስሮ የሚገኘውና ምርመራ እየተደረገበት ያለው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሲሆን፣ የተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ደግሞ የሽብር ወንጀል ነው፡፡ ይህንን የወንጀል ድርጊት ለማጣራት ኮሚሽኑ በሕግ የተሰጠው ሥልጣን ስለሌለ፣ ድርጊቱ ሕገወጥ መሆኑን ጠበቃው ገልጸዋል፡፡ ከፖሊስና ከደኅንነት የተውጣጣና በሕግ ተቋቁሞ ሰው አስሮ የመመርመርና የማጣራት ሥልጣን የተሰጠው አካል እንደሌለ የተናገሩት ጠበቃው፣ ጋዜጠኛው የታሰረው ያለ ሕግ ድግፍ በተደራጀው ግብረ ኃይል በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
Via reporter

#update የሶማሊያ መከላከያ ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎችን ገደለ። ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎች የተገደሉት በደቡባዊ ሶማሊያ አርብ ምሽት በተካሄደ ኦፕሬሽን ሲሆን የሶማሊያ ሃይል በአውድኒል ከተማ ባካሄደው ስምሪት ነው ተብሏል፡፡
የከተማዋ አስተዳዳሪ ኢብራሂም መሃመድ ኑር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የሶማሊያ ሃይል እርምጃውን የወሰደው የከተማዋ ነዋሪዎች “ጽንፈኛው አልሻባብ አስገዳጅ ግብር እንድንከፍል አድርጎናል” በሚል በሰጡት ጥቆማ ነው፡፡
“በተካሄደው ኦፕሬሽን ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ አንዱ ከነህይወቱ በቁጥጥር ስር ውሏል፤ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶችንም መያዝ ተችሏል” ያሉት አስተዳዳሪው የተያዘው ታጣቂም በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪ ለዥንዋ በስልክ በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንደተናገረው በከተማዋ በሶማሊያ መንግስት ኃይልና በአልሻባብ ታጣቂዎች መካከል አርብ ምሽቱን የተኩስ ልውውጥ እነደነበር ተናግሯል፡፡
የሶማሊያ ኃይል አሁን ከወሰደው እርምጃ በፊት በዋንሎዌይን ከተማ በሎወር ሸበሌ ክልል 15 የአልሻባብ ታጣቂዎቸን ገድሏል፡፡ የሶማሊያ ኃይል በማእከላዊና በደቡብ ሶማሊያ መጠነ ሰፊ ኦፕሬሽኖች በማካሄድ የአልሻባብ ጽንፈኞች አካባቢውን እንዲለቁ እየሰራ ነው፡፡
ምንጭ፡- ኢዜአ

ፋሲል ከነማ የኢትዮጵያ ጥሎ ማፍ ዋንጫን አሸነፈ፡፡ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫን ፋሲል ከነማ ሐዋሳ ከተማን በመለያ ምት አሸንፎ አነሳ፡፡ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በማጠናቀቃቸው ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡ በመጨረሻም ፋሲል ከነማ 4ለ2 በድምሩ 5ለ3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚወክል ይሆናል፡፡ ጨዋታው በቢሾፍቱ ስታዲዮም ነበር የተካሄደው፡፡
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደራርቱ_ቱሉ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን
ትናንት ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ጽ/ቤት ልዩ የዕውቅና ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፦
• ፍልቅልቋ ዝምተኛ ጀግና አትሌት ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት የኦሎምፒክ የወርቅ መዳልያ አሸናፊ በመሆኗ ከአፍሪካ ኅብረት ጽ/ቤት ልዩ ሽልማት አበርክቶላታል፡፡ እንዲሁም የዲሲ ከንቲባ ጽ/ቤት በክብር ሠርተፍኬት አበርክቶላታል፤
• ተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ደግሞ በምሽቱ ሦስት ሽልማቶችን ተሽልሟል፡፡ በሙዚቃ ሥራው ለአፍሪካውያን ወጣቶች አርአያ በመሆኑ ከአፍሪካ ኅብረት ልዩ ዋንጫ ሲሸለም፤ የዲሲ ከተማ ከንቲባም የእውቅና ሠርተፍኬት አበርክቶለታል፡፡
የሜሪላንድ ኢትዮጵያውያንም ለቴዲ አፍሮ ልዩ ስጦታ ሰጥተውታል፤ ቴዲ አፍሮ (ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን) ባደረገው ንግግር፤ ሽልማቱን ላበረከቱለት ሁሉ አመስግኖ ሽልማቱን ለአፍሪካውያን ወጣቶች መታሰቢያ እንዲሆን አበርክቷል፤
Via #GETU_TEMSEGEN

#Congratulations አድማስ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን እና ያሰለጠናቸውን 6,848 ተማሪዎች አስመርቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #ሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ
ተመራቂ ተማሪዎች ያስተማራቸውን ህዝብና ሀገራቸውን #በቅንነትና #በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም #ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም አሳስበዋል። የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸው 1ሺህ 495 ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።
በምርቃው ስነስዓት ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት ሚኒስትሯ እንዳሉት መንግስት ለትምህርት ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶና ሰፊ ሀብት መድቦ እየሰራ ይገኛል። በዚያው ልክ ተመራቂ ተማሪዎችም ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነት በማገልገል ኃላፊነታቸውን በቅንነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

#Congratulations የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ10 ሺ በላይ ተማሪዎች ትላንት በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።
Rift Valley University has graduated more than ten thousand graduates on July 20,2019 at Millennium Hall. The graduating students were from fifteen RVU campuses that are located in Addis Ababa and the surrounding Oromia special Zones campuses. The graduating students have attended TVET, undergraduate and postgraduate programs.
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/RU-07-21

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#Congratulations ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ/Fasil Kenema Football Club የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ItIsTimeToGetOurHandsDirty
#Joint
#RotaryEthiopia
#RotaryInternational
#GreenRotaract
#CommunityService
Date: July 27, 2019
Time: 8:00 AM
Place: Guskuwam area in front of St. Peter specialized hospital
@RotaractEvent

#አድማስ_ዩኒቨርሲቲ~የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና አድማስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ባስመረቀበት ወቅት በእንግድነት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ድህነትንና ኋላቀርነትን ከሀገራችን ለማጥፋት ዕውቀት ሰፊውን ሚና እንደሚጫወት ጠቁመው መንግስትም ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ነው ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ADU-07-21
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ADU-07-21
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አልጄሪያውያን የአፍሪካ ዋንጫን አሸንፎ የተመለሰውን ብሔራዊ ቡድናቸውን ለመቀበል አደባባይ ወጥተዋል። እ/አ/አ ከ1990 በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈው የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አልጀርስ ሲደርስ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር ጨምሮ በበርካቶች የሞቀ አቀባበል ተደርጎለታል። በሰንደቅ አጊጠው አደባባይ የወጡ ደጋፊዎች “ኮርተንባችኋል’’ ሲሉ ለቡድኑ አባላት አዚመውላቸዋል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ግድያውን ብርጋዴር ጄኔራል #አሳምነው ጽጌ ብቻውን መርቶታል ማለት ከባድ ነው›› አምሳል ጌትነት ከበደ (ኢንጂነር)፣ የቀድሞ ፖለቲከኛ
.
.
አቶ አምሳል፡- "አምባቸው እንዲህ በአጭር ጊዜና ባልተጠበቀ ሁኔታ ይገደላል ወይም ይሞታል ብዬ አልገመትኩም፡፡ ይሁንና የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ሁኔታ ግን አይጥመኝም ነበር፡፡ አምባቸውን፣ እዘዝን ወይም ምግባሩን ይገድላቸዋል የሚል ጥርጣሬ አልነበረኝም፡፡"
ሪፖርተር ጋዜጣ ከኢንጂነር አምሳል ጌትነት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ👇
https://telegra.ph/BGAT-07-21

#ባህር_ዳር
የአማራ ክልልና የሱማሌ ክልሎች ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በምክክር መድረኩ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት ላቀ አያሌው የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልልና የሱማሌ ክልሎች ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በምክክር መድረኩ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት ላቀ አያሌው የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር
በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሕዝብ ለሕዝብ ውይይቱ ለሶማሌ ክልል የልዑክ አባላት #ሥጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የአማራ ክልል ለሶማሌ ክልል ሁሉም የልዑክ አባላት አገልግል እና የዘጌ ቡና በስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር የተመራው የሶማሌ ክልል ልዑክ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትሥሥር የሚያጎለብት ውይይት ተካሂዷል፡፡