TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba | የታሪፍ ማማሻያ ሊደረግ ነው።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

በመዲናዋ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች #አዲስ_የትራንስፖርት_ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ ተገጿል።

ህብረተሰቡ ከሰኔ 1 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia