#ላልይበላ
ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከ45 ሽህ በላይ የውጭ ሃገር ዜጎች ላልይበላን መጎብኘታቸውን የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የቅዱስ ላልይበላንና በዙሪው ያሉ ድንቅ ቅርሶችን 45,144 ጎብኝዎች መጎብኘታቸውን ከጽፈት ቤቱ የተገኘው መረጋጃ ያመለክታል፡፡ ጽ/ቤቱ እንዳመለከተው በየዓመቱ የጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀ ሲሆን የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜም ለማራዘም እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ለዚህም ደግሞ የሆቴሎችን አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሳደግ በተሰራው ስራ 5 ሆቴሎች በኮኮብ ደረጃ እንዲመደቡ የጎደላቸውን በሱፐርቪዥን ቡድን በተሰጠው ግበረ መልስ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም አስታውቋል፡፡
በተያያዘ መረጃ...
ባሳለፍነው 2011 በጀት ዓመት የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲናትና በዙሪው የሚገኑ ታሪካዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብለው በእቅድ ከተያዘው 48,3167 የሃገር ውስጥ ጎብኝዎች ውስጥ 211,909 የሃገር ውስጥ ጎብኝዎች መጎብኘታቸውን ከላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ መረጃው እንደሚመለክተው በየአመቱ የጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል፡፡ በበዓላትና በሌሎችም ቀናት ቅርሶችን የሚጎበኙ ዜጎችም መጨመራቸው ነው ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
Via Lalibela Government Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ላልይበላ_ፖሊስ
የላል-ይበላ ፖሊስ በከተማው የእየሱስ ክርስቶስ እና የቅዱስ ላል-ይበላን የልደት በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲከበር ለማድረግ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታወቀ፡፡
በዓሉን ለማክበር በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ላልይበላ ከተማ እየገቡ ነው፡፡
ሁሉም የጸጥታ ተቋማት ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን የተገለፀ ሲሆን ከጸጥታ አካላት በተጨማሪ የትራፊክ ፍሰቱን ጤናማ እንዲሆን ለማድግ የተማሪ ትራፊኮችን በማሰልጠን በቂ ዝግጅት መደረጉን ተገልጿል።
የጥበቃ ቀጠናዎችን በመለየት እንዲሁም የአካባቢውን ወጣቶች በማስተባበር ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቷል ተብሏል።
ማህበረሰቡ የተለየ እንቅስቃሴ ሲኖር ጥቆማ መስጠት አለበት ተብሏል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#ገና #ላልይበላ
ቀደም ባሉት ዓመታት (ዘመናት) ሁለት ሚሊዮን ምዕመናን ይታደሙበት የነበረው በላልይበላ የሚከበረው የገና በዓል ዘንድሮ ግን ታዳሚው እስከ 300 ሺህ ሊወርድ እንደሚችል የቅዱስ ላልይበላ ገዳም ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዋና አስተዳዳሪ አባ ህርያቆስ ፀጋዬ ለጋዜጣው ምን አሉ ?
" ዘንድሮ ክልሉ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ምክንያት በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ቁጥራቸው ከ300 ሺሕ ላይበልጥ ይችላል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ይህ በዓል የእምነቱ ተከታዮችና ከእምነቱ ውጪ ያሉ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ የሚገኙ እንግዶች የሚታደሙበት ታላቅ በዓል ነው። " ያሉ ሲሆን ፦
* ከጎጃም፣
* ከጎንደር፣
* ከሰሜን ሸዋና ከወሎ አካባቢዎች የተወሰኑ ምዕመናን በእግርና በተሽከርካሪ ሊመጡ ይችላሉ የሚል ግምት መኖሩን ገልጸዋል።
በበዓሉ ከሚታደሙ ምዕመናን አብዛኛዎቹ በአውሮፕላን ከሩቅ እንደሚመጡ የገለፁ ሲሆን ፤ " በዚህ ሁለትና ሦስት ሳምንት ምን ሊፈጠር እንደሚችል አናውቅም፡፡ ምናልባት የፀጥታ ችግሩ ከተረጋጋና እንደ ቀድሞው ከሆነ የምዕመናን ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር ይችላል " ብለዋል።
ወጣቶች በተለያዩ ችግሮች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የፈለሱ ቢሆንም፣ ያሉትን በማስተባበር የእንግዶችን እግር ለማጠብና ሌሎች የተለመዱ መስተንግዶዎችን ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አባ ህርያቆስ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በዓሉ ሲከበር " የሚያሠጋ ነገር አልነበረም " ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ " ከትግራይ በኩል ያሉ ወገኖቻችን መሳተፍ አልቻሉም ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ምዕመናን በርካታ ነበሩ " ብለዋል፡፡
" በአሁኑ ወቅት ያለየለት የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ብንሆንም፣ ወደ በዓሉ በሚመጡ ወገኖች ላይ አስቦ ጉዳት የሚያደርስ ኃይል አለ ብለን አናስብም " ያሉት አባ ህርያቆስ፣ ነገር ግን በድንገት የተኩስ ልውውጥ ካለ የሚሞቱት ንፁኃን ዜጎች በመሆናቸው ሥጋት ሊኖር ይችላል ስሉ አስረድተዋል፡፡
ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪ የሚመጡ ምዕመናን ቁጥር ሊቀንስ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡
" በዓሉ የበረከት ነው " ያሉት አባ ህርያቆስ፣ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን ለማድነቅ ብቻ ሳይሆን የእምነትን ፍሬ ለማግኘት የሚመጡ ምዕመናን በእግዚአብሔር ተማምነው በመምጣት የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአካባቢው ማኅበረሰብም በዓሉን በታላቅ ተስፋ ስለሚጠብቅ እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀቱን ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።
ይህ መረጃው ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia