TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram

“አረና” የመገንጠል አላማ ያላቸውን ሃይሎች አጥብቄ እታገላለሁ አለ!

በትግራይ የተለየ አስተሳሰብን የማፈን እንቅስቃሴ እንዲቆም ጠይቋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተቀነቀኑ ያሉ ፀረ አንድነት ዘመቻዎችን እቃወማለሁ ያለው አረና ትግራይ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ በትግራይ የመገንጠል አላማ ያነገቡ አደረጃጀቶች መበራከታቸው አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡ 

ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ፤ የትግራይ ክልል ህዝብን ከሌሎች ክልል ህዝቦች ጋር ለማጋጨት በመንግስታዊ ሚዲያዎችና በማህበራዊ ድረ ገፆች ጥረት እየተደረገ መሆኑን በመጠቆም፤ በማንኛውም መልኩ ህዝቦችን ለማጋጨት የሚደረጉ ጥረቶችን በጥብቅ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡ 

#በጥላቻና ባልተገቡ ዘመቻዎች #መፈናቀል የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች እርቅ ተፈጽሞ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ የጠየቀው አረና፤ የወሰን ጥያቄዎችም #በውይይትና #መግባባት መፈታት እንዳለባቸው ገልጿል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-08-06-2
" አሁንም ያለው ችግር በውይይት እና በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ " - የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቶ ነበር።

በዚሁ መግለጫው በአማራ ክልል ያለው ችግር አሁንም በ #ውይይት እና በ #ድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

መ/ቤቱ በመግለጫው ፤ " ከድርድር እና ውይይት ይልቅ መንግሥታዊ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚጥሩ እንዲሁም አጋጣሚዎችን በማቀነባበር ዝርፊያ ለመፈጸም የሚፈልጉ የታጠቁ ቡድኖች፣ ፅንፈኛና አክራሪ ኃይሎች ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ የጸጥታ ሥጋት ለመደቀን ሙከራ እያደረጉ ነው " ብሏል።

በአማራ ክልልም እየታየ ያለው ሁኔታ ይኸው ነው ሲል ገልጿል።

" ከኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥረቶች ቢደረጉም ችግሩ በሚፈለገው ልክ አልተፈታም " ያለ ሲሆን ፤ " ለዘረፋ የተደራጁ ጥቂት ኃይሎች አሁን ላይ መንግሥታዊ መዋቅሮች እንዲፈርሱ፤ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዲቋርጡ፤ አንዳንድ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚያገናኙ የመንገድ መሠረት ልማቶች እንዲዘጉ በማድረግ፤ ሕዝቡ ላይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ " ብሏል።

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅመው የጠቅላይ መምሪያ ዕዝን በማስተባበር የክልሉን ሰላምና ደኅንነትን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ስምሪት ወስዶ እየሠራ መሆኑን ገልጾ " በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲል አሳስቧል።

አሁንም በአማራ ክልል ያለው ችግር #በውይይትና #በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲል አሳውቋል።

" ለዝርፊያ ከተደራጁ ቡድኖች ጋር የሚንቀሳቀሱ አካላት ካሉ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ እና ሕግ የማስከበር ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጣላል " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia