TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Alert

ይርጋለም ከተማ ያለው አለመረጋጋት እንደቀጠለ ነው ነዋሪውም በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኝ፤ የፀጥታ ሃይል በከተማው እንደሌለ ለTIKVAH-ETH መልእክት የላኩ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራና ሱማሌ ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ነገ በባህርዳር ከተማ ይጀመራል ተባለ። ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሰማሀኝ አስረስ መድረኩ የሁለቱን ክልል ህዝቦች የቆየ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ሐሚመራ ልዑክ ነገ ባ/ዳር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የሀይማኖት መሪዎችን የሀገር ሽማግሌዎችንና ኡስታዞችን ያካተተ ነው።

ም/ፕሬዚዳንቱ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የፊታችን ቅዳሜ በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ አሰማሀኝ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Waamicha Tajaajila Lammummaa

በኦሮሚያ ሁሉም አካባቢዎች ዛሬ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ መካሄድ መጀመሩን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

ጨፌ ኦሮሚያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ ማጽደቁና በኦሮሚያ ክልል የሚተገበርባቸውን ሁኔታዎች ማውጣቱ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት ከዛሬ ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በአገልግሎት አሰጣጡ አስፈላጊነት ላይ ለሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል።

ውይይቱ ከተጠናቀቀ በኋላም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ አስፈጻሚ ምክር ቤት በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ ወይም በከተማና በቀበሌ ደረጃ ይቋቋማል፤ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎችም ተግባራዊ ይሆናል።

የአገልግሎቱ ዓላማ በገዳ ስርዓት አስተምህሮት መሰረት በክልሉ ሕዝባዊ ግዴታን በመወጣት ብቁ እና እውቀት ያለው ዜጋ መፍጠር ነው።

የክልሉን ኃብትና እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እድገት ማምጣትና ትውልዱ ባህልና እሴቱን እንዲረዳ፣ ለአገሩ ፍቅር እንዲኖረውና የአብሮነት ባህሉን እንዲያጎለብት ለማድረግ ያለመም ነው ተብሏል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማበረታታት ዜጎችን የማገዝ መንፈስ እንዲዳብር ማድረግ፣ ኃላፊነት የሚሰማው፣ ግዴታውን የሚወጣና አርዓያ የሆነ ዜጋ መፍጠርም እንዲሁ።

የመንግስት አገልግሎት በማይደርስባቸው አካባቢዎች ያለውን ክፍተት መሸፈንም ሌላው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ዓላማ መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዐለም ዐቀፉ የስደኞች ድርጅት (አይኦኤም) ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከየመን ወደ ሀገራቸው መልሻለሁ ብሏል፡፡ ድርጅቱ 280 በጎ ፍቃደኛ ስደተኞን የመለሰው እኤአ ከሐምሌ 10-11 ባሉት ቀናት ነው፡፡ ተመላሾቹ በየመን ቆይታቸው ግርፋትና ስቅየት ማየታቸውን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡

Via wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking ኩዮቶ በተባለች የጃፓን ከተማ በአንድ የተንቀሳቃሽ ስዕል ስቱድዮ ውስጥ በተነሳ እሳት ቢያንስ 23 ሰዎች ሞተዋል ወይም እንደሞቱ ተገምቷል ሲሉ ባለስልጣኖች ተናግረዋል። እሳቱ ሆን ተብሎ የተለኮሰ ነው የሚል ጥርጣሪ አለ።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች በገለጹት መሰረት 13 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። የኪዮቶው የሲኒማ ኩባንያ በሚገኝበት በባለ ሦስት ፎቁ ህንፃ ከፍተኛው ወለልና ወደ ጣራው በሚያመሩት ደረጃዎች ላይ 10 ሰዎች ራሳቸውን ስተው ተገኝተዋል። ከ30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። አንዳንዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

ፖሊሶች እንደሚሉት እሳቱ የተነሳው አንድ ሰው ወደ ህንፃው ገብቶ አቀጣጣይ ፈሳሽ ካፈሰሰበት በኋላ ነው። ሰውየው በእሳት ሲያቀጣጥለው “ሙቱ” እያለ ይጮህ ነበር። እሳቱ ሲነሳ 70 የሚሆኑ ሰዎች ህንጻው ውስጥ እንደነበሩ ተገልጿል።

የተጠርጣሪው ሰው ዕድሜ 41 ነው ተብሏል። ቆስሎ ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደ ታውቋል። የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በትዊተር መልዕክት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሐዋሳ ተቃውሞ እና ግጭት!

የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ለዛሬ ለማወጅ መቀጠሩን ተከትሎ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ግጭት ተቃውሞ ተከስቷል። የጥያቄ አራማጆች ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደገለፁት የሲዳማ ሽማግሌዎች እና ወጣት የጉዳዩ አቀንቃኞች ዛሬ ጠዋት ሊያካሂዱት ያቀዱት ስብሰባ አካባቢውን በዘጉት በፀጥታ ኃይሎች ተደናቅፏል። ባለሥልጣናት ወደዚያ ባለመምጣታቸው፤ እና ወደ መሰብሰቢያው ስፍራም እንዳያልፉ ያገዷቸው የፀጥታ ኃይሎች ላይ ወጣቶቹ ድንጋይ መወርወራቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ሐዋሳ ከተማ ላይ በቁጣ ወደ ጎዳና የወጡት ዜጎች ጎማ በማቃጠል ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭትም ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱን ሌሎች ደግሞ መጎዳታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።

የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሚሶ ጭንቅላቱን በጥይት መመታቱ የተገለፀው ተጎጂ ወደ ሐኪም ቤት ከሄደ በኋላ ሕይወቱን ማጣቱን ለጀርመን ራውዮ ዘጋቢ ገልጸዋል።

«መጀመሪያ ላይ ትንሽ ጭንቅላቱ ላይ የቆሰለ ሰው ገብቷል። እሱ የመጀመሪያ ርዳታ ሰጥተን ወደ ቤቱ ሄዷል። ከዚያ ቀጥሎም ደግሞ አንድ ሴት ነበረች የመጣችው። ባጠቃላይ አራት ወንድ እና አንድ ሴት ነበር የመጡት። አንደኛው ከአዳሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመጣ ከዚያ ሪፈር የተደረገ ሰው ነበረ ጭንቅላቱ ላይ ነበር ቆስሎ የነበረው፤ ቁስሉ አሁን ሀኪሞች እንዳረጋገጡት በጥይት የተመታ ይመስላል። ከፍተኛ የሆነ ቁስል ነው። እሱ አዳሬም ወደ እኛ እንደላከ እኛ ጋርም ብዙ ሳይቆይ ሊያርፍ ችሏል።» ሌሎቹ ተጎጂዎችን በተመለከተ የሚታየው እስካሁን ለከፋ አደጋ የሚያደርስ እንዳልሆነም አክለው ገልጸዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ከፍተኛ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፌዎች በርሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን የአንዳንዶች ቤተሰቦች ተናገሩ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩላቸው ትላንት ወደ ታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ መሄዳቸው ጠቅሰው ጥያቄዎቻቸውን ተቀብለው ለጥያቄዎቻቸው አፋጣኝ ምላሽ መሰጠቱን ተናግረዋል። ዛሬ ምግብ እንደጀመሩም ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትላንትናው ዕለት ሐምሌ 10, 2011 ዓ.ም በአንድ ቀን ብቻ 310 በረራዎችን በማድረግ 29 ሺህ 528 መንገደኞችን በማጓጓዝ አዲስ ክብረ ወሰን ማሻሻሉን ገለጸ፡፡ አየር መንገዱ እንዳስታወቀው አዳዲስ ዓለም አቀፍ ተሳፋሪዎች በአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በኩል መጓጓዝ ጀምረዋል።

የቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ አደራ የአየር ማረፊያውን አቅም ከሁለት እጥፍ በላይ የሚጨምረው አዲሱ ተርሚናል በከፊል መከፈቱን ገልፀዋል። በዚህ የክረምት ወቅት ብዛት ያላቸው ተሳፋሪዎችን ማጓጓዝ በመቻላችን በጣም ደስተኞች ነን ብለዋል።

አየር መንገዱ በቅርቡ ባደረገው ማስፋፊያ በአመት 22 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረ ነው የተገለፀው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ70 አመታት ታሪኩ በአፍሪካ በፍጥነት እያደገ የመጣ አየር መንገድ ለመሆን በቅቷል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
10 ቀን ቀረው🎂የTIKVAH-ETH ሁለተኛው የምስረታ ዓመት ክብረ በዓል!!

ሁላችንም በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ማዕከል እንገናኝ!!

ተጨማሪ መረጀ ከዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ያግኙ፦ +251913134524
ትኩረት በሲዳማ ዞን ለሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች!

📣ትኩረት #ይርጋለም #አለታ_ወንዶ #ጩኮ #ለኩ #ሀገረ_ሰላም በሚባሉ ከተሞች የሚገኙ ዜጎች አሁንም ያለው ሁኔታና አለመረጋጋት እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። በአንዳንድ ከተሞች ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ጠፍቷል። ዝርፊያ ተፈፅሟል፤ ሰዎች ህይወታቸውን ሙሉ ለፍተው ያፈሩት ንብረት ወድሞባቸዋል። መልዕክታቸውን ለTIKVAH-ETH በስልክ #ደውለው የተናገሩት የየከተሞቹ ነዋሪዎች የሚመለከተው አካል በሙሉ ከዚህ የከፋ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ሁኔታዎችን ተቆጣጥሮ #እንዲያረጋጋ ተማፅነዋል። ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ አስፈሪ ነው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገር ሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል። የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን...ሌሎችም ለሀገር እና ወገን ተቆርቋሪዎች ወጣቱን በመምከር፣ በማረጋጋት ከጥፋት በመመለስ በኩል ሀገራዊ #ሃላፊነታቸው ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል...

ሀዋሳ ከተማ #የጦርነት_አውድማ እንደሆነች ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። በዚህ ፈታኝ ወቅት ሀገሪቱን ወደማያባራ ግጭት ውስጥ እድትገባ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው የፌስቡክ አርበኞች በመኖራቸው የምንሰማቸውን መረጃዎች #በደንብ ልናጣራ እና ልንመረምራቸው ይገባል።


🚫📱💻በሲዳማ ዞን እና ዙሪያው በሚገኙ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው። ከየከተሞቹ ነዋሪዎች በስልክ የሚደርሱኝን የተጣሩ መረጃዎች ወደናተ የማደርስ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አስመራ

በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያዩ።

መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተከናወነ ያለውን ዘላቂ ሰላም የማስፈን ሂደትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ነው የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ያስታወቁት።

በተጨማሪም የዛሬ ዓመት ሁለቱ ሀገራት በተፈራረሙት ባለ አምስት ነጥብ የሰላም እና የትብብር ስምምነት መሰረት ሁሉን አቀፍ ትብብር ማድረግ በሚችሉበት ዙሪያም ተወያይተዋል።

መሪዎቹ አወንታዊ ለውጥ እየታየበት ያለውን የሀገራቱን ግኑኝነት እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም የማስፈን ጥረትን የበለጠ ለማስፋት ተስማምተዋል።

በመጨረሻም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመራው ልዑክ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በባህዳር ከተማ የሚካሄደው የአማራና የሱማሌ ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ እንዲሁም የባህርዳር ዩንቨርሲቲ ምርቃት ያለ ጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ መምሪያ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
262 የክርስትና እምነት ተከታዮችን በመስጊድ እና በቤቱ በመደበቅ ከገዳዮች ለታደጉት ናይጀሪያዊው ኢማም አሜሪካ እውቅና ሰጥታለች፡፡ የ83 አመቱ አዛውንት ኢማም አቡበከር አብዳላሂ የአለምአቀፍ የሃይማኖቶች ነፃነት ሽልማት ያገኙ ሲሆን ከቆጵሮስ፣ሱዳን፣ብራዚልና ኢራቅ የተለያዩ ሽልማቶች አግኝተዋል፡፡

ኢማም አቡበከር አብዳላሂ በማዕከላዊ ናይጄሪያ ፕላትዮ ግዛት ልዩ ስሙ ባርኪን ላዲ በተባለው አካባቢ ከገዳዮች ሲሸሹ የነበሩትን ክርስትያኖች ህይወት መታደጋቸው ነው የተገለፀው፡፡ በወቅቱ ክርስቲያኖች ላይ ባነጣጠረው ጥቃት ሌሎች 80 ሰዎች መሞታቸውም ተገልጿል፡፡

ኢማም አቡበከር አብዳላሂ 262 ክረስትያኖችን ባይታደጓቸው ኖሮ የሟቾች ቁጥር ከ80 በላይ ይሆን እንደነበር ተገልፅዋል፡፡ ኢማሙ ለዚህ በጎ ድርጊት ያነሳሳቸው ከ40 ዓመታት በፊት ክርስትያኖቹ በቦታው መስጊድ ለመስራት ስለፈቀዱላቸው ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖንፕዮ ኢማም አቡበከር አብዳላሂ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል የሌላ እምነት ተከታዮች ህይወት ማትረፍ የቻሉ ራስ ወዳድ ያልሆኑ ሰው ናቸው ብለዋል፡፡ ያለሳቸው እርዳታ የሰዎቹን ህይወት ማትረፍ እንደማይቻልም አክለው ገልፀዋል፡፡ ኢማሙ ከዚህ ቀደምም ከናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ እውቅና እንደተሰጣቸውም ተገልጿል፡፡

ምንጭ ፡-ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአ/አ ከተማን ገፅታ የሚቀይሩና ከ10.7 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸው የ 6 ፕሮጀክቶች የግንባታ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ለመኖር ምቹ ፣ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከነዚህም ውስጥ በዚህ ዓመት ግንባታቸው ተጀምሮ እስከ ሁለት አመት ባለ ጊዜ ውስጥ የሚጠናቁ ስድስት ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት ግንባታውን ከሚፈፅሙ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ከነዚህም ፕሮጀክቶች መካከል፦

1.የዓድዋ 0:00 ኪ.ሜ ፕሮጀክት
በ30,300ካ.ሜ ላይ የሚያርፈው የዓድዋ ድልን ለመዘከር ታስቦ የሚገነባው ይህፕሮጀክት በከተማዋ እንብርት መሃል ፒያሳ ላይ የሚገነባ ይሆናል፡፡ ለግንባታው 4.6 ቢሊየን ብር በጀት ተይዟል፡፡

2. የአዲስ አበባ ቤተ-መፅሐፍት
ቀጣዩን አገር ተረካቢ የሆነውን ወጣቱን በንባብ ለማዳበር በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት አከባቢ በ19ሺ ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚያርፍ በቀን ከ20ሺ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቤተ-መፅሐፍት ነው፡፡

3. የአዲስ አበባ ከተማ የማዘጋጃ ቤት ሙሉ ጥገና
ከተገነባ ከ50 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ህንፃና የቴአትር አዳራሽ ሙሉ በሙሉ የእድሳት እና የፈርኒሽንግ ስራ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

4.የታላቁ ቤተ-መንግስት የመኪና ማቆሚያ
የጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት ቤተ-መንግስትን ለጎብኚዎች ክፍት ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን ታሪካዊ ቦታ ለመጎብኘት ለሚመጡ እንግዶችና ሌሎች ተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግ ባለ አራት ቤዝመንት በ 10ሺ ካ.ሜ ላይ የሚያርፍ ና 1 ሺ መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ነው፡፡ ይህ ግንባታ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
#update በአገሪቱ ከተከሰተው የሰላም እጦት ስጋት ለመላቀቅ መንግሥት በላቀ እርጋታ የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ መፍትሔ እንዲያፈላልግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ ፅህፈት ቤት ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም አባተ ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግላጫ፤ አገሪቱ የሰላም እጦት ስጋት ውስጥ መውደቋን በመግለጽ፤ ከዚህ ስጋት ለመላቀቅ መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላቀ እርጋታና የኃላፊነት ስሜት ህዝብንና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ያሳተፈ መፍትሔ ማፈላለግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

በሐዋሳ ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ። አሁንም ከሁከቱ ጋር በተያያዘ #ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው፤ በከተማይቱ የተፈጥረውን ግጭትና ሁከት ለመቆጣጠር ተችሏል ሲሉ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ተጠባባቂ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለBBC ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ(SMN) ዋና መስሪያ ቤት በትላንትናው ዕለት በወታደሮች ተከቦ መዋሉንና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በህገ ወጥ መንገድ ፍተሸ መደረጉን ከዚህ በተጨማሪም ከሚዲያው የቦርድ አባላት ሰዎች መታሰራቸውን የSMN ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆች #ጌታሁን_ደጉዬ እና #ታሪኩ_ለማ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። በውጭ ሀገር የሚገኙ የጣቢያው ተወካዮችም ትላንት በፌስቡክ ባስተላለፉት ጥሪ መንግስት በአስቸኳይ እነዚህን እና ሌሎች የሲዳማ መብት ታጋዮችን ከእስር እንዲፈታ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦንጋ

"በአሁን ሰዓት በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ያስተላለፈውን መግለጫ በመቃወም፤ መግለጫው እኛን አይወክለንም በማለት እንዲሁም ካፋ ዞን ራሱ በራሱን ያስተዳድር የክልልነት ጥያውቄው ይመለስለት "ክልላችን ካፋ ነው" በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል። የሰልፉ ተካፋዮች ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ናቸው።"

Via #SAMI

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦንጋ

•ሀገራዊ ለውጡ ይቅደም ብለን እንጂ ጥያቄያችን በበቂ ምክንያት ነው!!

•ከእንግዲህ ለግማሽ ቀን ስብሰባ ሁለት ቀን እንጓዝም!!

•የካፋ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቅም ፍትሃዊ ምላሽ እንጂ ድጋሚ ጥያት አያሻውም!!

•ክልላችን ካፋ ነው!!

•የካፋ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ታሪካዊ ልምድና አቅም አለው!!

በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። ከተለያዩ ወረዳዎችም በርካታ ሰዎች ወደ ቦንጋ እየገቡ እንደሆነ ለማውቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በሀዋሳ ከተማና አካባቢው ትናንት ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክለሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደሚካኤል ለፋና ብሮድካስት እንደተናገሩት፥ በግጭቱ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ዛሬ ላይ ከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ይታይባታል ብለዋል።

ግጭቱ ትናንት በታቦር ክፍለ ከተማ መንገድ በመዝጋት መጀመሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። እንዲሁም በግጭቱ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የፀጥታ ችግሩ ከተማዋን መነሻ አድርጎ ወደ ሲዳማ ዞን ወረዳዎች መዛመቱን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ መንገዶች በመዘጋታቸው የጸጥታው ሀይል በፍጥነት መድረስ አለመቻሉን አስታውሰዋል። በዛሬው እለት አካባቢዎቹን የጸጥታ አካላት #እያረጋጉ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ማንኛውም ጥያቄ ያለው አካል የህግ የበላይነትን ባከበረ መልኩ ማቅረብ እንደሚኖርበት ጠቅሰው፥ በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች #ሰላም መሆኑን አስረድተዋል። ነገር ግን ከዚህ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የዜጎችን ህልውና የሚፈታተኑ በመሆኑ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት፡፡ ህብረተሰቡም የሀዋሳ ከተማና አካባቢውን ሰላም እና መረጋጋት ለማስጠበቅ ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት እንዲሰራና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ካርቱም

በትናንትናው ዕለት ሱዳናውያን ወጣቶች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ #የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ ታይተዋል፡፡ ወጣቶቹ ይህን ያደረጉት በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በተደረሰው ወሳኝ ስምምነት ሂደት ኢትዮጵያ ለተጫወተችው ቁልፍ ሚና አድናቆታቸውን ለመግለፅ ነው፡፡ ወጣቶቹ በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ስልጣን ለመጋራት በተፈረመው ገንቢ ስምምነት የተሰማቸውን ታላቅ ደስታም ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia