TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዘፈቀደ የሚተገበረው የታክሲ ታሪፍ፦

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት መጨናነቅና እጥረት መኖሩ ታክሲዎች በዘፈቀደ እንዲያስከፍሉ ምክንያት ከሆነ ሰንብቷል፡፡ በአብዛኛዎቹ የትራንስፖርት ቦታዎች ላይ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮችን ተቋቁመው አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጋፉ ሰዎችም ለስርቆት ሲዳረጉ ማየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

በአገሪቱ የሚታዩ ክፍተቶችን በመጠቀም ዋጋ መጨመርና ኅብረተሰቡን ማማረር የተለመደ ከሆነባቸው ዘርፎች አንዱ ትራንስፖርት ነው፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከሜክሲኮ ዓለም ባንክ ለመሄድ ተሠልፈው ያገኘናቸው አቶ ኬራሚድ ሙራድ፣ በተለያዩ ቦታዎች መሄድ የሚፈልጉ ተሳፋሪዎችን እንግልት በመመልከት፣ መንግሥት ካወጣው ታሪፍ በላይ በመጠየቅ ተሳፋሪውን አማራጭ የሚያሰጡ፣ በኑሮ ውድነት ላይ ሰውን የሚያማርሩ የታክሲ ትራንስፖርት ሰጪዎች መበራከታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ #ሪፖርተር_ጋዜጣ👇
https://telegra.ph/AA-07-28-3
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲሱን የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ደንብ ማስፈጸሚያ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለተቋማት ላከ!

ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያፀደቀውን የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ደንብ ማስፈጸሚያ መመርያ አርቅቆ፣ ለክልሎችና ለተለያዩ ተቋማት አስተያየት እንዲሰጡበት አሠራጨ፡፡

ከአሁን ቀደም ከ40 ዓመታት በላይ ሲሠራበት የቆየውን የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ከዘጠኝ ደረጃዎችና ከአሥራ ሁለት እርከኖች ወደ ሃያ ሁለት ደረጃዎች ብቻ በመወሰን፣ እያንዳንዱ ደረጃ ከአንድ እስከ 12 የሚደርሱ መደቦችን እንዲይዝ የሚያደርገውን ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መመርያው ከአሁን ቀደም በመንግሥት ተወስነው ይሠራባቸው የነበሩ ከ70 በላይ የደመወዝ ስኬሎችን ወደ አንድ ስኬል የሚቀይር ሲሆን፣ ቀድሞ የነበረው ስኬል ይሠራበታል ቢባልም በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ ስኬሎች በመኖራቸው፣ ከ150 በላይ እንዲሆኑ ያደረገውን አሠራርም ይለውጣል፡፡

በዚህም መሠረት በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ለተመሳሳይ ሥራዎች የተለያዩ ክፍያዎች ይፈጸሙ ስለነበር፣ የክፍያ ኢፍትሐዊነት እንዲንሰራፋ በማድረጉና ለእኩል ሥራዎች እኩል ክፍያ የሚያጎናጽፈውን ሕጋዊ መብት ወደ ጎን ያለ አሠራር ነበር ተብሎ የቀድሞው ይተቻል፡፡ አዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን በአገር አቀፍ ደረጃ ሥራዎችን በመስፈርት በመመዘን፣ እኩል የሆኑ ሥራዎች እኩል ክፍያ እንዲያገኙ ያስችላልም ተብሏል፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28
አቶ መለስ ዓለሙ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት ሆነው ሊሾሙ ይችላሉ!

ከአሁን ቀደም የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት አቶ መለስ ዓለሙ፣ ለክልሉ ምክር ቤት በፕሬዚዳንትነት ሊሾሙ እንደሚችሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ አቶ መለስ በአሁኑ ወቅት በሚኒስትር ማዕረግ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ በመሆን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28-2
በጋምቤላ ፈቃድ የሌላቸው 11 የውጭ ኮሌጆች ተገኙ!

ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ሕገወጥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋምቤላ ክልል ሲያስተምሩ እንደተደረሰባቸው፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ከተለያዩ ግለሰቦች በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወደ ክልሉ ተንቀሳቅሶ የለያቸው እነዚህ 11 ተቋማት በድኅረ ምረቃና በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እየተቀበሉ እንደሚያስተምሩ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኤጀንሲው የኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ናቸው፡፡

ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኙ ሊያስተምሩ የተገኙት 11 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በአገር ውስጥ የማይታወቁና እንግዳ መጠሪያ ያላቸውና ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹በተደጋጋሚ በደረሰን ጥቆማ መሠረት ለማጣራት ወደ ክልሉ ስናመራ የጠበቅነው አንድ ተቋም ብቻ ነበር፡፡ ስንደርስ ግን 11 ሆነው አገኘናቸው፡፡ በወቅቱ ምንም ማድረግ ስላልቻልን ለክልሉ መንግሥት ስለሁኔታው በማስረዳት የክልሉን ነዋሪዎች ከሕገወጦች እንዲጠብቅ ደብዳቤ ጻፍን፤›› የሚሉት አቶ ታረቀኝ፣ ለክልሉ ደብዳቤ ከተጻፈ ስድስት ወራት የተቆጠረ ቢሆንም ምንም ዓይነት ምላሽ ለኤጀንሲው አለመድረሱን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-08-28-3
#አቶ_ርስቱ_ይርዳው

ቀጣዩ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት ማን ይሆኑ?

TIKVAH-ETHIOPIA ከቤተሰቡ አባላት ታማኝ ምንጮች እንደሰማው ከሆነ-አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን በመተካት የደቡብ ክልልን በፕሬዘዳንትነት የሚመሩት አቶ #ርስቱ_ይርዳው ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

•በትላንትናው ዕለት #ሪፖርተር_ጋዜጣ የደቡብ ክልል ቀጣይ ፕሬዘዳንት አቶ መለስ አለሙ ሆነው ሊሾሙ እንደሚችሉ መግለጹ አይዘነጋም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የቆዩ ፈንጂዎችን ሙሉ ለሙሉ ለማፅዳት ዓለም አቀፍ ትብብር ጠይቃለች !

ኢትዮጵያ ከውጭ ከመጡ ጠላቶችና በአገር ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች መሬት ውስጥ ተቀብረው የቆዩ ፈንጂዎችን፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ለማፅዳት ዓለም አቀፍ ትብብር እየጠየቀች መሆኑ ተገለጸ፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የፈንጂ ማምከን ቢሮ ኃላፊ ኮለኔል አበራ አዘናው ፥ ኢትዮጵያ በካናዳ እ.ኤ.አ. በ2004 የፈረመችውን የፀረ ሰው ፈንጂ ማውደም ስምምነትን በተያዘለት እ.ኤ.አ. በ2020 አስወግዳ ባለማጠናቀቋ፣ ሁለተኛ የማራዘሚያ ጊዜ በኖርዌ ኦስሎ እ.ኤ.አ. 2020 እንደገና ለአምስት ዓመት ጠይቃ እስከ 2025 እንደተራዘመላት ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

በ5 ዓመታት ውስጥ አፅድታ እንድትጨርስ በስምምነቱ መሠረት ፈቃድ የተሰጣት ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ያሏት የፈንጂ ማምከኛ መሣሪያዎች ኋላ ቀር በመሆናቸውና በፋይናንስ ችግር ሳቢያ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ትብብር መጠየቋ ተገልጿል፡፡

የድጋፍ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የፈንጂ ማምከን ቢሮ የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርንና ሌሎች አካላትን ጨምሮ ከኤምባሲዎችና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍና ትብብር ለማግኘት ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ዝግ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፈንጂ ማምከን ቢሮ ኃላፊው፥ አገሪቱ ምንም እንኳ በትግራይ፣ በአፋር ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌና በጋምቤላ ክልሎች መሬት ውስጥ የተቀበሩ ወይም ተከማችተው የሚገኙ ፀረ ሰው ፈንጂዎች እንዳሉ ቢታመንም የፈንጂዎቹ ትክክለኛ መገኛ ቦታ አይታወቅም ሲሉ ለ #ሪፖርተር_ጋዜጣ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-Newspaper-05-23

@tikvahethiopia
#ከመልሚ

በከተሞች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለሚጠቀሙበት መንገድ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉበት ስርዓት እየተዘረጋ ነው።

ይህ ስርዓት ከተሞች ገቢያቸውን ለማሳደግ ሊሠሯቸው ይገባል ተብለው በዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻው የጥናት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ወ/ሪት አፀደ ኃይሉ ተናግረዋል።

የከተማ መንገድ የአገልግሎት ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚደረገው ጥናት የአዳማ፣ የድሬዳዋ እና የባህር ዳር ከተሞችን ናሙና በመውሰድ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በጥናቱ በአጠቃላይ በከተሞች ውስጥ ያለው የተሽከርካሪዎች ምልልስና በመንገዶች ላይ የሚያሳድሩት ጫና የሚዳሰስ ሲሆን መንገዶቹ ጥገና ሆነ መልሶ መገንባት ሲያስፈልጋቸው ከተጠቃሚዎች በሚያገኙት ገቢ የሚሠሩበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው ብለዋል።

በ3ቱ ከተሞች በሚወሰደው ናሙና መሠረት አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች፣ የከተማ መንገድ ተጠቃሚዎች ክፍያ ይጠይቃሉ ብለዋል።

ወ/ሪት አፀደ ኃይሉ ፤ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ተመሳሳይ ክፍያ ባይከፍሉም በጥናቱ ግኝት መሠረት በመንገዶች ላይ እንደሚኖራቸው ተፅዕኖ ክፍያ ይጠየቃሉ ያሉ ሲሆን " ክፍያው ሁሉንም ባለ ሞተር ተሽከርካሪዎች ብቻ ያካትታል። ሞተር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ አልተካተቱም " ብለዋል።

ጥናቱ ሲጠናቀቅ የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ምን ያህል መክፈል አለባቸው የሚለው ሆነ መቼና የት ይከፍላሉ የሚለው እንደሚለይና ሥርዓቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለፃቸውን #ሪፖርተር_ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
የመንገደኞች እንግልት እና የመንግስት አካላት ምላሽ !

ከአማራ ክልል በተለይም #ከሰሜን እና #ደቡብ_ወሎ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ብዙዎች እየተንገላቱ ነው።

ይህ ጉዳይ አንድ ወቅት ጠንከር አንዴ ላላ ፤ ያዝ ለቀቅ እያደረገ አሁንም ድረስ ቀጥሏል።

አንዳንዶች በብዙ ልመና ነው የሚያልፉት።

ወደ መጣችሁበት ተመለሱ የሚባሉ ወገኖች ምክንያት ቢጠይቁም በግልፅ አስረድቶ የሚነግራቸው አላገኙም።

ለመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ምን አሉ ?

👉 " ... መላ ሊባልለት የሚገባ ነገር ነው። ከደሴ ተነስተን ወደ አ/አ እየሔድን ነበር ግን " ሸኖ " ላይ የአማራ ክልል መታወቂያ ይዛችሒ አትገቡም ተብለን ስንጉላላ ቆይተን ሹፌሩ ይዘሐቸው ተመለስ ተብሏል። ሌሎቹ ተመልሰዋል። እኔ ግን ግድ መሔድ ስላለብኝ ለፈተና ባጃጅም በግሬም ኡ/ ገብቻለሁ ፡፡ እባካችሁ ዛሬ ብቻ አደለም ያዝ ለቀቅ እያደረጉ ነው እንጅ ከብዶናል "

👉 " እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም ድረስ ከወሎ መዳረሻቸውን አ.አ አርገው የሚመጡ ተሳፋሪዎች ከበኬ ኬላ አየተመለሱ አሌልቱ ላይ ብዙ እንግልት እየገጠማቸው ይገኛል "

👉 " ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለው ብዙዎች ሲንገላቱ ቆይተው ወደ ኃላ እንዲመለሱ ተደርገዋል። እኛ በብዙ ልመና ለህክምና ነው ብለን አልፈናል። "

#ሪፖርተር_ጋዜጣ ያነጋገራቸው ፦

👉 " ሐምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. መነሻችንን ከወልዲያ ከተማ አድርገን ወደ አዲስ አበባ ስንጓዝ የአማራ ክልልን አልፈን ኦሮሚያ ክልል ስንገባ ተደጋጋሚ ፍተሻ ተደርጎልናል። ለገዳዲ ከደረስን በኃላ ግን የአዲስ አበባ መታወቂያ የላችሁም በሚል ምክንያት ወደ ደብረ ብርሃን መልሰውናል። ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ነው ።

ከሸኖ ከተማ ጀምሮ እስከ ሰንዳፋ ድረስ የተደረገብን ፍተሻ በጣም አድካሚ ከመሆኑም በላይ፣ የአዲስ አበባ መታወቂያ የላችሁም በሚል ሲሳለቁብን ማየት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አሳፋሪ ተግባር ነው።

ፖሊሶች ፍተሻ ካደረጉ በኋላ የአዲስ አበባ መታወቂያ የሌላቸውን እዚያው ክልላቸው ወስደህ አውርዳቸው በማለት ለሾፌሩ ተናግሯል።

በዚህም የተነሳ በግዴታ ለገዳዲ ከደረስን በኋላ እንደገና ተመልሰን ደብረ ብርሃን ከተማ አድረናል። በስተመጨረሻም በነጋታው የቤት መኪና ተከራይተን ለቅሶ እንደምንሄድ በመናገር አዲስ አበባ ገብተናል።

የተፈጠረውን ክስተት አስከፊ ነው። በጊዜው ገንዘብ ስለነበረን ከፍለን ተመለስን ነገር ግን ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ሲደረጉ ሕፃን ልጅ የያዙ እናቶች ጭምር ለመመለሻ የሚሆን ገንዘብ አጥተው ሜዳ ላይ ወድቀው ነበር።

ይህን ያህል አማራ ምን አድርጎ ነው ? ወስደህ አውርዳቸው እንዴት ይባላል ? ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ ? ብዙ ግፍ ያለበት ክልል እኮ ነበር፣ በአማራ ላይ ይህ ሁሉ ሲደረግ ሕግ አለ ወይ ያስብላል ? "

👉 " አደራው ኃይሌ እባላለሁ ከደሴ ከተማ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝኩ ነበር 100 ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ውስጥ ከጫጫ ከተማ እስከ ለገዳዲ ከተማ ቢያንስ 7 ጊዜ ተፈትሸናል።

የመጨረሻው የአዲስ አበባ መግቢያ ፍተሻ በነበረው ለገዳዲ ስንደርስ ከጥቂት የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ ከያዙ ሰዎች ውጪ ቀሪዎቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ድርጊቱ በጣም የሚያሳዝን ነው።

ከመኪና እንድንወርድ ከተደረገ በኋላ ስልካችንን ከፍተን በውስጥ ያሉ ምሥሎችና ድምፆችን ከፍተን እንድናሳይ ተደርጓል።

👉 " ሁኔታው የሕግ ድጋፍ ያለው እንደማይመስልና አልፎ አልፎ ፖሊሶቹ በመሰላቸው አሠራር እንጂ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈቅድ ምንም ዓይነት የሕግ መሠረት ማቅረብ አይቻልም።

ድርጊቱ አሳፈሪ በመሆኑ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለጉዳዩ አፋጣኝ መልስ መስጠት ካልቻለ፣ እንደ አገር አብሮ በኖረ ሕዝብ ላይ አሁን ያለው የፖለቲካ ግለት ተጨምሮበት የባሰ ቁርሾ፣ እርስ በርስ የመለያየትና ከፋፋይ የሆነ አጀንዳ ይሆናል "

የመንግስት አካላት ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

▪️የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፦

" ጉዳዩ ስለመከሰቱ መረጃ አለኝ። ነገር ግን የሕወሓት ሠርጎ ገቦችን ለመያዝ በሚል ግልጽ ባልሆነ መንገድ ዜጎች እየተንገላቱ በመሆኑ ጉዳዩን ለኦሮሚያ ክልል መፍትሔ እንዲሰጥበት አሳውቀናል። "

▪️የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አራርሳ መርዳሳ ፦

ጥያቄ ከሰሙ በኋላ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

▪️የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ፦

" ጉዳዩ መከሰቱን መረጃ አለኝ።

ተሳፋሪዎች ደብረ ብርሃን ከተማ ካለፉ በኋላ እንዲህ ዓይነት ችግር ተፈጥሯል።

ከኦሮሚያ ክልልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ደውላችሁ አጣሩ "

▪️የአዲስ አበባ የፀጥታ ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ፦

" ስለሚባለው ጉዳይ ምንም ዓይነት መረጃ የለንም "

▪️የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፦

" የተጠቀሰው ጉዳይ አይመለከተንም "

▪️ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሪት ሰላማዊት ካሳ ፦

" ጉዳዩ የሕወሓት የሽብር ቡድን በወረራ ይዟቸው ከነበሩት የአማራ ክልል አካባቢዎች የተለያዩ የመታወቂያ ማኅተሞችና የአስተዳደር ሰነዶችን በመዝረፉና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ሐሰተኛ መታወቂያዎች ሰነዶችን የያዙ ሠርጎ ገቦች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ በመያዛቸው ምክንያት የሚደረግ የክትትል ሥራ ነው።

የጥፋት ተልዕኮ የያዙና ከአማራ ክልል ተዘርፈው በተወሰዱ ሰነዶች ተመሳስለው የተሰሩ መታወቂያዎችን የያዙ ግለሰቦች አሁንም ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዳለ ለፀጥታ ኃይሎች መረጃው በመድረሱ ይህንን ለመከላከል ጥብቅ ፍተሻዎችና ማጣራቶች እየተደረጉ ነው።

ይሁን እንጂ አዲስ አበባን የጥፋት ተልኳቸው መዳረሻ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉትን አካላት ለመከላከል በሚወሰደው ዕርምጃ፣ በመንገደኞች ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩንና ዜጎችም ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የተመለከቱ ቅሬታዎች ደርሰውናል።

ይህም በደኅንነት ፍተሻና ማጣራት አፈጻጸም ላይ መሻሻል ያለበትን ሁኔታ ለይቶ የፀጥታ ኃይሉ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወስድ ይደረጋል ። "

▪️የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የአብን ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ፦

" ... ከአማራ ክልል የወሎ አካባቢዎች ተነስተው መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዜጎች ኦሮሚያ ክልል ሸኖ ሲደርሱ መታወቂያቸው እየታየ ከተሳፈሩበት መኪና እንዲወርዱና ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን ተጨባጭ መረጃዎች አሉ።

የሚመለከታቸው የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የሥራ ኃላፊዎች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን መጉላላትና አግላይ የነውር ተግባር ታስቆሙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን ! በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦ • መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው። • የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ…
የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጥያቄ !

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ሒደቱ አሁን ምን ይመስላል ?  

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦

" በሲቪል ሰርቪስ ባለሙያዎች የሥራ መዘርዝር በድጋሚ ታይቶ ሌላ የደረጃ ምዘና ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ረዳት ምሩቅ ሁለት፣ ረዳት ሌክቸረር፣ ሌክቸረር፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርና ረዳት ፕሮፌሰር ደረጃዎች ተሻሸለዋል፡፡

የረዳት ምሩቅ አንድና የፕሮፌሰር ግን ከነበረበት ደረጃ አልተሻሻለም፡፡ ለፕሮፌሰር ደረጃ ቀድሞም በ2011 ዓ.ም. ላይ ማሻሻያ ሲደረግ ደመወዝ የተጨመረው 233 ብር ገደማ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዕድሜ ልካቸውን በትምህርት ላይ ያሳለፉ፣ እዚህ ለመድረስ ብዙ ጥናት ያሳተሙና ያማከሩ ናቸው፡፡

ውሳኔዎች ሲተላለፉ የአገር አቅም ከግምት ውስጥ የሚገባ ቢሆንም፣ እነዚህ ሰዎች ከዚህ ሌላ የገቢ ምንጭ የላቸውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ማስተርስ ያላቸው ሆነው በታወቁ ጆርናሎች ላይ ጥናታቸውን ያሳተሙ መምህራን ረዳት ፕሮፌሰር መሆን ይችሉ ነበር፡፡

አሁን በወጣው ደረጃ ግን ረዳት ፕሮፌሰር ለመሆን ሦስተኛ ዲግሪ ስለሚያስፈልግ፣ ማስተርስ ኖሯቸው ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑ መምህራን በአዲሱ ደረጃ የተቀመጠውን የደመወዝ ጭማሪ አያገኙም፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስናነጋግር የሚያነሱ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሰዎች በማስተርስ ደረጃ ረዳት ፕሮፌሰር የሚሆኑ ከሆነ ዶክትሬት ለመማር አይበረታቱም የሚል ነው፡፡

የትምህርት ዕድል ሲሰጣቸው ባለንበት ረዳት ፕሮፌሰር መሆን እንችላለን የሚሉ እንዳሉ ይነገራል፡፡

ይህንንና የረዳት ምሩቅ አንድና የፕሮፌሰር ደረጃ አለመሻሻሉን ጉዳይ ገና እየተወያየንበት ነው፡፡ "

ያንብቡ : telegra.ph/RE-08-14-3

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ / ወደ ትግራይ  የየብስ ትራንስፖርት መቼ ይጀምራል ? ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ከሰሞኑን ተገልጿል። ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልል የኮንድትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በህጋዊ…
#Update

ከ/ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት ለመጀመር የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ማህበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል።

ሪፖርተር ጋዜጣ ከአገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ማኅበራት ያገኘሁት ባለው መረጀ ፤ የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወደ ትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎትን ዳግም ለመጀመር ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ መመርያ ተላልፎላቸዋል፡፡

በዚሁ የሚኒስቴሩ መመርያ መሠረት ማኅበራቱ ለአባሎቻቸው አገልግሎቱን መልሶ ለማስቀጠል ዝግጁ እንዲሆኑ ያሳወቁ ሲሆን አሁን እየጠበቁ ያሉትም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ እንደሆነ ለማወቅ መቻሉን #ሪፖርተር_ጋዜጣ ዘግቧል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ  ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ማሳወቁ አይዘነጋም።

ቢሮው ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia