TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ተጠናቀቀ
==================================
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት 10 ቀናት ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 07/2011 ዓ/ም በአገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም አዳዲስ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች ላይ ሲያካሄድ የነበረውን ስብስባው በስኬት አጠናቋል፡፡

ማእከላዊ ኮሚቴው አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የተጀመረው አገራዊ ለውጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሮ አቋም ወስዷል፡፡ ክልላዊ አደራጃጀቱን በተመለከተ ዝርዝር ሳይንሳዊ ጥናት ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ጊዜ ወስዶ በሳል ውይይት ተካሂዶበታል፤ የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል ፡፡ በማያያዝ የክልሉን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶ ጠንካራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ስለሆነም የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችንና ውጤታቸው ተጠናክረው እንዲሁም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጽናትና በመርህ ላይ ቆሞ በመታገል ለላቀ ስኬት እንዲበቃ ማእከላዊ ኮሚቴው በሙሉ መግባባብት ላይ በመድረስ ለቀጣይ ተልእኮም በቁርጠኝነት መዘጋጀቱን አረጋግጧል፡፡

ዝርዝር መግለጫው እንደደረሰ ይቀርባል፡፡

Via #ደኢህዴን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የጋምቤላ ክልል አራት የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሃላፊነት አነሳ። የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ኡዶል አጉዋ ለጀርመን ራድዮ እንደገለፁት በክልሉ በተለያዩ ጊዜዎች ከሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊ፣ የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ፣ የጋምቤላ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ከሀላፊነታቸዉ ተነስተዋል፡፡ እንደ አቶ ኡዶል ገለፃ ውሳኔው የተላለፈው የክልሉ መሪ ድርጅት፣የሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉዳዩን ከገመገመና አቅጣጫ ከሰጠ በሁላ ነዉ። በተነሱት ሃላፊዎች ሌሎች መመደባቸውንና ለጋምቤላ ከተማ ክንቲባነትም እስከ ቀጣዩ ምርጫ የሚያገለግሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሁለት ከንቲባዎች ተመድበዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ #ተጠናቋል። ዝርዝር #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ሲያካሂድ የነበረውን የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ውይይት በዛሬው እለት አጠናቋል። ውይይቱን አስመልክቶም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

Via ADP
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ የማእከላዊ ኮሚቴ አቶ ዩሐንስ ቧያለው የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል በተመሳሳይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አገኘው ተሻገርን ለአዴፓ ስራ አስፈፃሚነት እና ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት እንዲያድጉ ተደርጓል። ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደርነት ደግሞ አቶ ተመስገን ጥሩነህን በእጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የአቶ ተመስገን ጥሩነህ አጭር ፕሮፋይል!!

የትውልድ ቦታ፡- ጎጃም፣ ብቸና ደብረወርቅ ልዩ ስሙ ወይራ
የትምህርት ዝግጁነት፡- የመጀመሪያ ዲግሪ በኮምፒውተር ሳይንስ እና የሁለተኛ ዲግሪ በተቋም የለውጥ አመራር
የትዳር ሁኔታ፡- ያገባ

የሰሩባቸው ቦታዎች፡ -

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሲያገለግል እስከ ሻለቅነት መዕረግ ድረስ የደረሱ
• የሃገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ
• ኤሌክትሮኒክስ መምሪያ
• ቴክኒካል መረጃ መምሪያ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራች አመራር የነበሩ
• ከመምሪያ ኃላፊነት እስከ ዋና ዳይሬክተርነት የመሩ
በአማራ ክልል በተለያዩ የኃለፊነት ደረጃ ያገለገሉ
• የርዕሰ-መስተዳድሩ የፀጥታ እና ቴክኖሎጂ አማካሪ
• የአማራ ገጠለር መንገዶች ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ
• የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
• የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ
• የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
. የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር
• የኢትዮቴሌኮም ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
በመጨረሻም በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ሁነው ሰርተዋል።

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

በዓምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ #የፍፃሜ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ። በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እየዳኘ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማ የፍፃሜው ጨዋታ እንዲመራ በካፍ የዳኞች ኮሚቴ ተመርጧል። በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ሁለት የምድብ፣ አንድ የሩብ ፍፃሜ እና ትላንት ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ወሳኝ የነበረው የሴኔጋል እና ቱኒዚያን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን የመራ ሲሆን የፊታችን ዓርብ በካይሮ ስታዲየም በአልጄርያ እና ሴኔጋል መካከል የሚደረገውን የፍፃሜ ጨዋታም የሚመራ ይሆናል።

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ራሱን በማክሰም ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ተቀላቅሏል። ከተመሠረተ 11 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በዛሬው ዕለት ባከሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ራሱን በማክሰም ኢዜማን መቀላቀሉን የኢራፓ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት የ3ኛ ተከሳሽ ኢሳያስ ዳኘው እና የ4ኛ ተከሳሽ አብዱል ሀፊዝ አህመድ የክስ ዝርዝር በዛሬው እለት በችሎት ተነበበ፡፡

ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/FD-07-15
#udate ህንድ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስፔስ ልታደርግ የነበረውን ጉዞ ከአንድ ሰዓት በታች ጊዜ ሲቀረው በቴክኒክ ችግሮች አማካኝነት ሰርዛለች፡፡ ሳተላይቱ በምስራቃዊ ህንድ ስሪሃሪኮታ ስፔስ ሰኞ 2፡51 ለመንቀሳቀስ ፕሮግራም እንደነበረ ቢቢሲ በዘገባው ገልጿል፡፡ የተሰረዘው የስፔስ ጉዞ መቼ እንደሚደረግ በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት በአዴፓ እና በህወሐት መካከል ሰሞኑን የታየው አለመግባባት #በሰከነ መንገድ ሊፈታ ይገባል ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ አባላት ገለጹ። ችግሩ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው የዓላማ አንድነት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አፅህሮተ-ስያሜውን ያካተተው ዓርማ ከላይ የምትመለከቱ ነው፡፡ #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የሥራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴው በክልሉ ወቅታዊ እና በለውጥ ስራዎች ላይ ሲመክር ሰንብቶ ዛሬ ሐምሌ 08/2011 ዓ.ም መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ADP-07-15
#መቐለ

ሕወሃትን ከኤርትራው ሕግዴፍ ጋር ለማስማማት ያለመ ምክክር መድረክ መቐለ ላይ ተጀምሯል፡፡ መድረኩን ያዘጋጀው ሰለብሪቲ ኤቨንትስ የተባለ የግል ተቋም ሲሆን ከሁለቱ ሀገራት ምሁራን፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የማቀራረቡ ጥረት ከሁለቱ ፓርቲዎች በጎ ምላሽ እንደተቸረውም DW የመድረኩን አዘጋጅ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በቀጣይነት የሁለቱን ድርጅቶች የቀድሞ ታጋዮች፣ የጦር ጉዳተኞች፣ የቀድሞ አመራሮች የሚሳተፉበት ውይይት በአዲስ አበባና አሥመራ ለማድረግ አቅዷል፡፡

Via #wazemaradio/#DW/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ኮንጎ ውስጥ የኢቢላ ወረርሽኝን በማጥፋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁለት የማኅበረብ ጤና ሠራተኞች፣ ምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ክፍለ-ሀገር ኬቬዮ ውስጥ #መገደላቸውን፣ የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ አስታወቀ። ሠራተኞቹ ለወራት ያህል ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ይደርስባቸው እንደነበርም፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በአማራ ክልል በጥረት ኮርፖሬት ስር የሚተዳደሩ ከአስር በላይ ኩባንያዎች በአክሲዮንና ሙሉ በሙሉ በሽያጭ ወደ ግል እንዲዛወሩ መወሰኑን የኮርፖሬሽኑ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ #አባተ_ስጦታው አስታውቀዋል። በአክሲዮንና በሽያጭ ወደ ግል ከሚዘዋወሩት ኩባንያዎች መካከል አምባሰል ንግድ ስራዎች ድርጅት፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣የባህር ዳርና ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፉብሪካዎች ይገኙበታል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ #etv ዜናን ይከታተሉ #tikvahethiopia
#ከደኢህዴን_መግለጫ ~የክልል ጉዳይ

በክልል የመደራጀት ጥያቄን በተመለከተ የህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን ድርጅታችን ይገነዘባል። በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሲነሳ የነበረው ከአንድ አካባቢ ብቻ ባይሆንም ጥያቄውን በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ድርጅቱ በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በወሰደው አቋም መሰረት በዝርዝር ህዝቡን ያሳተፈ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። በጥናቱ የቀረቡ አማራጮችን በጥልቀት በመመርመር የህዝቡን የጋራና ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ አማራጭ በመውሰድ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች በሚመለሱበት አግባብ ላይ አቋም ተወስዷል። በክልላችን መላው ህዝብ ምክክርና ውይይት የሚደረግበት ሆኖ በአንድ በኩል በጥናቱ የተገኘውን የክልሉ ህዝቦች አብሮ የመቀጠል ፍላጎትን ባከበረ፤ በሌላ ጎኑ ደግሞ የጉባኤውን ውሳኔ ተግባራዊ ባደረገ መንገድና ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ የመምራት ሃላፊነት ለመወጣት ማዕከላዊ ኮሚቴው ተስማምቷል። #TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከደኢህዴን ማህከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ! #walta

@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢#የመን Yemen is seeing the world's worst humanitarian crisis, according to the #UN.

https://telegra.ph/Yemen-07-15
ፎቶ📷የመን ከጦርነት በፊትና ከጦርነት በኃላ! #YEMEN