TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው ..

- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ
- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወልዲያ
- ሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው።

#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 363 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐ-ግብሮች፤ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሶስተኛ ዲግሪ እና የስፔሻሊቲ ህክምና የሰለጠኑ ናቸው።

#አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎችን ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ8ተኛ ጊዜ ሲሆን የዛሬዎቹ ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።

#የኢትዮጵያ_ሲቪል_ሰርቪስ_ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲም በተለያየ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ የተማሩ ናቸው።

ከእለቱ ተመራቂዎች ውስጥ 153 የሚሆኑት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በውጭ ግንኙነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑ እጩ ዲፕሎማቶች ናቸው።

#ወልዲያ_ዩኒቨርሲቲ

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,537 ተማሪዎችን አስመርቋል።

#ሪፍትቫሊ_ዩኒቨርስቲ

የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 16, 967 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም አስመርቋል።

መረጃው የetv ነው።

@tikvahethiopia