TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።

ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበት እንዲሁም ምእመናን በተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያንን የማይመጥንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ፦
° " #ግድሉ "
° " #ዘርህ_ይጥፋ "
° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " በማለት መናገራቸውን ገልጿል።

ይህ ንግግራቸው ፦
➡️ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል፣
➡️ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ፣
➡️ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል፣
➡️ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣
➡️ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ፣
➡️ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች በተለያየ ቦታ የሚያስተለልፏቸው መልዕክቶች ቤተክርስቲያንን ለትችት እየዳረገ እንዲሁም ዋጋ እያስከፈለ ነው ተብሏል።

በቀጣይ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ ገዢ ህገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል።

ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስብከት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia