TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert በሱዳን ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል። ኢንተርኔቱ የተዘጋው በአገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት የሆነውን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጁን 3 በፀጥታ ሃይሎች እና ተቃዋሚዎች የተከሰተው ግጭት ተከትሎ ነበር፡፡

ኢንተርኔት በመዘጋቱ #ክሱን ያቀረቡት የህግ ባለሙያው አብደል አዚም ሃሰን እንዳሉት የካርቱም አከባቢ ፍ / ቤት ዛየን ለተባለው ኩባንያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲለቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ለ37 ቀናት ተቋርጦ የቆየውን የኢንተንኔት አገልግሎት በከተማው መስራት መጀመሩን ተገልጿል፡፡ ፍርድቤቱ በተመሳሳይ ኤምትኤን እና ሱዳኒ ለተባሉ ተቋማትም ኢንትርኔት አገልግሎቱን እንዲለቁ ወስኗል፡፡

ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከዓለም አቀፍ ተቋማት #የኢንተርኔት አገልግለቱን ክፍት እንዲያደርግ ግፊት ሲደረግበትም ቆይቷል፡፡ ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከተቃዋሚዎች ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመጀመር ከስምምነት ደርሶ እነደነበርም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ኢስት አፍሪካ ኒውስ/ሱዳን ትሪቡን/#ENA/
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia