TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስ አበባ ከተማ በፒያሳ፣ በለገሐር፣ በአውቶብስ ተራ፣ በሜክሲኮ፣ በችርችል ጎዳና፣ በመገናኛ፣ በ 22፣ በቦሌ፣ በመድሃኒያለም፣ ሸጎሌ፣ አስኮ፣ በጦር ሃይሎች፣ በሶማሌ ተራ፣ ...በርካታ የአዲስ አበባ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ የታክሲ #እጥረት ተከስቶ እንደነበር ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አማራ ክልል⬇️

በአማራ ክልል የሚገኙ ከተሞች የመብራት ኃይል #እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ።

የፌዴራል መንግስትም በክልሉ ያለው ኢ-ፍትሃዊ የመብራት አቅርቦች ችግር እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሚገኙ ከተሞች በመብራት ኃይል አቅርቦትና እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ተግባር ማከናወን አልቻሉም።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የሚገኙ ከተሞች ከሌሎች ክልሎች አንጻር ፍትሃዊ የኃይል ስርጭት እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ክልሉ በከተሞች ያለው የመብራት አቅርቦት እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠይቋል ያሉት አቶ ፈንታ፤ የፌዴራል መንግስት ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የቢሮው ሃላፊ አሁን እየታየ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭትና አቅርቦት ችግር ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት ችግር በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ የማሰራጫ መስመሮችን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ከጅማ_ቤተሰቦች

"በጅማ ከተማ በችግኝ #እጥረት ምክንያት መትከል አልቻልንም" #አረንጓዴ_አሻራ #greenlegacy