TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹ትብብርና ፉክክር ሚዛናዊ መሆን አለባቸው!›› አቶ ዮናስ ዘውዴ

ሀገራችን በብዙ ርዕዮተ ዓለም ሙከራ ውስጥ ብትቆይም እስካሁን ድረስ የምዕራቡን አስተሳሰብ ስንቃርም ቆይተናል፡፡ አሁን ላይ መደመር ሀገራዊ መፍትሔን ይዞ መጥቷል፡፡ መደመር የሰው ልጅ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል እንዲሁም የሰውን ልጅ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የህልውና ፍላጎቶችን በመመለስ ያምናል፡፡

መደመር መጨፍለቅ ማለት አይደለም መደመር አሀዳዊነትም ማለት አይደለም መደመር የተበታተነ አቅምን ወደ አንድ ማምጣት ማለት ነው፡፡ የመደመር መነሻ ከነበረው ነገር ላይ ነው፡፡ የተሰሩ ሥራዎችን ንዶ እንደ አዲስ አይገነባም ነገር ግን ያሉትን ይዞ ክፍተታቸውን ይሞላል እንጂ፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-21-13

#TIKVAH_ETHIOPIA

PHOTO: EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ38 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በበጎፈቃድ መሰብሰብ ተችሏል!

በትምህርት ሚኒስቴር አነሳሽነት የተጀመረው “የእኛ ለእኛ” የበጎ ፈቃደኞች መርኃግብር ላይ ላለፉት 3 ወራት ለተሳተፉ በጎፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በተገኙበት የሰርተፍኬት አሰጣጥ መርኃግር ተከናውኗል፡፡ በአጠቃላይ የበጎ ፈቃድ ዘመቻው ከ350 በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ለሚገኙት በጎፈቃደኞች ይህ መርኃግብር ተዘጋጅቷል፡፡

በሦስት ወር የበጎ ፈቃድ ስራ በትምህርት ቁሳቁስ ከ3 ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሺ በላይ የተሰበሰበ ሲሆን በአልባሳትና በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘውን ድጋፍ ጨምሮ 30 ሚሊየን የሚቆጠር ድጋፍ ማሰባሰብ ተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ግን በዚህ መርኃግብር 38 ሚሊየን ሀብት መሰብሰብ ተችሏል፡፡ በዚህም በበርካታ ቦታዎች የሚገኙ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ጉዳት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉና ችግር ለደረሰባቸው አከባቢዎች ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ በቀጣይ የትምህርት ሚኒስቴር በእኛ ለእኛ የበጎፈቃድ አገልግሎት ስር “የተማረ ያስተምር” የተሰኘ መርኃግብር የሚጀመር ሲሆን በዚህም በርካታ በጎፈቃደኞች ይሳተፉበታል ተብሎ ይታመናል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WKU ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንትነት ያመለከቱ ተወዳዳሪዎች የመጀመሪያ ዙር የውጤት መግለጫ፦

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Update!

"ቲክቫህ ኢትዮጵያ" በመጀመሪያ ዙር ሁለት ላፕቶፕ ኮምፒተሮችን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩና ዘንድሮ ለሚመረቁ አንድ ወንድ አንድ ሴት ተማሪዎች እገዛ ያደርጋል።

ተማሪዎቹ ከፍተኛ ውጤት ያላቸው፣ መልካም ስነ ምግባር የታነፁ፣ ተምረው ወጥተው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ለማገልገል ህልም ያላቸው ነገር ግን ቤተሰባቸው አቅም የሌላቸው ናቸው፡፡

በቅርቡ ዝርዝር መረጃው ከዩኒቨርስቲዎቹ የሚላኩልን ሲሆን ቀጣይ ስራዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

ምንም ወቅቱ ቢከፋም፤ በሀገራችን ወጣቶች ተስፋ አንቆርጥም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ቀነዓ፦

"በኢትዮጵያ አንፃር፤ አጠቃላይ እውነታ (universal truth) የብዙ ተማሪዎቻችን እዚህ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉት ልጆቻችን - ቤተሰቦች ድሃዎች ናቸው፤ የኢትዮጵያ ቤተሰብ ነው። የኢትዮጵያን ቤተሰብ ደግሞ ሁላችንም የምናውቀው ነው አብዛኛው ህብረተሰብ ኑሮውን እናውቃለን ምስኪን ነው፣ እናት ለፍታ፣ አባት ለፍቶ ለዩኒስቨርሲቲ ደረጃ ያበቋቸው ናቸው። ለምሳሌ ከጎንደር ደምቢዶሎ ድረስ የሚመደብ ተማሪ ምን አይነት ተማሪ እንደሆነ መገመት ይቻላል። ለመማር የሄደን ተማሪ ሀብታም ቢሆን ገንዘብ ቢኖረው ይሄን ሁሉ ርቀት አይሄዱም። ከደምቢዶሎ - ጎንደርም እንደዛው። ከጫፍ ጫፍ የሚሄዱት የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ፍለጋ የሚሄዱት ልጆቻችን የተሻለ ትምህርት፣ ሌላ ሀገር ሄዶ የመማር አቅም ቤተሰቦቻችን ስለሌላቸው ነው። ያንን እያወቅን ከጎን ያለውን #ምስኪን ሰው ለመጉዳት ማሰብ እራሱ የሞራልም የሰብዓዊነትም ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Electronic World Trade Platform (eWTP) ምረቃ!

(Eskinder - Hahau Jobs)

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ተከባብረን እንሂድ!

"ህጋዊ ስርዓት ተከትለን አዋጭ የሆነውን እንወስናለን። ህዝባችንን አማክረን የምንለው ለዚህ ነው። በግንፍልነት አንሄድም፤ በችኮላም ዝም ብለን ዘለን አንገባም፤ አጥንተን ነው፤ የማይስተካከል ከሆነ ግን እንዳልነው መድብለ ፓርቲ ስርዓት ነው፤ ብልፅግና ፓርቲም በራሱ ይሄዳል እኛም በራሳችን እንሄዳለን። እኛም ከሚመስለን ጋር አብረን እንሰራለን። ከሚቀራረቡን ጋር አብረን እንሰራለን። አማራጭ መኖሩ ጠቃሚ ነው የሚል እምነት ነው ያለን። ሁሌ አንድ ቦታ አይደለም መሰብሰብ ያለብን። ስለዚህ እንደ አማራጭ ሆኖ ነው መታየት ያለበት። ሁሉም ነገር በሰላም፣ በህግ፣ በስርዓት ነው እውቅና የምንሰጠው፤ የተጀመረው ሂደት በዚሁ እንዲጠናቀቅ ነው የምንፈልገው። አላስፈላጊ ጫናዎች ከተፈጠሩ ግን ምላሽ እንሰጣለን። በግድ እዚህ ግባ የሚባል ነገር፤ ወደ አንዱ ቋት ካልገባህ የሚባል ነገር አንቀበልም፤ በምንም አይነት! በትግል የመጣ ነው፣በመስዋትነት የመጣ ነው እሱን እናስጠብቃለን። ተከባብረን እንሂድ!" - የትግራይ ክልል ምክትል ር/መስተዳድር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day1 #ኡቡንቱ #Ubuntu

አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - #ኡቡንቱ በሚል ርዕስ ያዘጋጀነው የግንዛቤ መፍጠሪ መድረክ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ስኬታማ ነበር። ሁሉንም አካላት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን! ከወጣቶች ጋር የምናደርገው ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ እስከ ህዳር 27 ይቀጥላል።

“Ubuntu is about a community coming together to help one another.”— Paul Pierce

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ፒስሞዴል
#ጋሞዞንአስተዳደር

"ኡቡንቱ" ላይ የምንሰራቸው ሀገር አቀፍ ስራዎች ላይ አስተያየታችሁ፣ ሃሳባችሁን አካፍሉ። በምን በኩል ብንሰራ ውጤት እናመጣ ይሆን? ልታግዙን ይምትችሉ አካላትም አናግሩን! @tsegabwolde
@tikvahethiopiaBot 0919743630
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD

የመብቶችና ዲሞክራሲ ብልጽግና ማዕከል (CARD) አዘጋጅነት ዛሬ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያረቀቀው አዋጅ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ውይይቱ የማህበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች አዋጁን ይዘት እንዲተዋወቁትና ከባለሞያ ጋር እንዲመክሩበት አልሞ የተዘጋጀ ሲሆን ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዲሁም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በውይይቱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ውይይቱ በመሰንበት አሰፋ (ዶ/ር) ጹሑፍ አቅራቢነት ተጀምሮ በተሳታፊዎቹ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከህጉ አስፈላጊነት ጀምሮ አተገባበር ላይ ስለሚገጥሙት እንከኖች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉት የጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በውይይቱ ወቅት የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብዓትነት ይዘዋቸዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የምክክር መድረኩን ካዘጋጀው CARD ኤክስኪዊቲቭ ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ እንደ አቶ በፍቃዱ ገለጻ የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር በሦስት መሰረታዊ ነገሮች ላይ መሰራት አለበት ብለው ይመክራሉ እነዚህም ሀቅን ማረጋገጥ(Fact checking )፣ የሚዲያ አጠቃቀም (Media literacy) እና የመንግስት ግልጸኝነት (Transparency ) ናቸው ይላሉ፡፡

ተጨማሪ ከላይ ባለው ፋይል አድምጡ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለፍቅር እንሩጥ፤ ጥላቻን እናምልጥ!

ሚስባህ ከድር በአሸባሪነት ተከሶ በእስር የነበረ ሲሆን በቅርብ ከተለቀቁት እስረኞች አንዱ ነው፡፡ ከእስር ከወጣም በኀላ ፍቅር ያሸንፋል የሚል የሲቪክ ማህበር አብረው ከነበሩ የእስር ጓደኞቹ ጋር አቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በቅርቡም "ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ" የተሰኘ የ5 ኪሜ. የጎዳና ሩጫ አዘጋጅተዋል፡፡ ዋና አላማውም የተለያየ የፓለቲካ አቋም ያላቸውን ፓለቲከኞች፣ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ግለሰቦችን ማቀራረብ እንደሆነ በነበረን ቆይታ ገልጾልናል፡፡ በውድድሩም በሀገሪቱ ትልቁ እንጀራ ይጋገራል ይህም ሰፊ እንጀራ አለን ተካፍለን እንብላ እርስ በእርስ አንባላ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ሩጫው ጥር 17 በአዲስአበባ የሚጀምር ሲሆን በተለያዩ ከተሞችም ይቀጥላል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia