TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ሚዲያ ሁለት #ስለት ያለው መሳሪያ ነው፤ መልካም ከሰራህበት ትውልድ ታድንበታለህ፤ መጥፎ ነገር ካሳየህበት ደግሞ ትውልድ #እንዲጠፋ ታደርግበታለህ።...በፍፁም አግላይ የሆኑ፣ ስሜታዊ የሆኑ፣ ዘርን አመላካች የሆኑ፣ የሰው ልጆችን ወደክፋት እና ወደጥላቻ ሊወስዱ የሚችሉ ድምፆችን #በፍፁም ሚዲያዎች ይዘው መውጣት የለባቸውም።" ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Euro2020

የጣልያን ብሄራዊ ቡድን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንን #በፍፁም_ቅጣት ምት በማሸነፍ የEuro 2020 ሻምፒዮን ሆኗል።

በEuro 2020 የፍፃሜ ጨዋታ 2ቱ ብሄራዊ ቡድኖች ባደረጉት ፍልሚያ በመደበኛው እና በጭማሪው ሰዓት መሸናነፍ ባለመቻላቸው (1 ለ 1) ጨዋታው ወደፍፁም ቅጣት ምት አምርቷል።

ጣልያን እንግሊዝን በፍፁም ቅጣት ምት ድል አድርጋታለች።

በእንግሊዝ በኩል ሳንቾ፣ ራሽፎርድ እንዲሁም ሳካ የፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር አልቻሉም።

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የጦር ወንጀሎችን ፈፅመዋል " - አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተዛመተው ጦርነት ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የጦር ወንጀሎች ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሷን አሳውቃለች። ይህንን ያሳወቀችው ትላንት በውጭ ጉዳይ ቢሮዳ በኩል የአገራትን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታን በተመለከተ የሚያደርገው ግምገማ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ ስታደርግ ነው። ሪፖርቱን…
#Update

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፦

• " የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት የቀረበበትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ በፍፁም አይቀበልም "

• " መግለጫው በሀገሪቱ አንድን ወገን በሌላኛው ላይ ለማነሣሣት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቆስቋሽ መግለጫ ነው "

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት " ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል " ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት #በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ መወንጀል ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ የጠቆመው።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮችን ለመለየት ብሔራዊ ምክክር ለመጀመር በተዘጋጀችበት ወቅት ላይ የወጣ በመሆኑም መግለጫው ወቅቱን ያልጠበቀ ነው ብሎታል።

በተጨማሪም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ይህን መግለጫ ለማውጣት ያሰበበት ዓላማ ምንም ይሁን ምን መግለጫው በሀገሪቱ አንድን ወገን በሌላኛው ላይ ለማነሣሣት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቆስቋሽ መግለጫ ነው ሲል ገልጾታል።

@tikvahethiopia