TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፓልም ዘይትን አስመልክቶ በአንዳንድ ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ኢንስቲትዩቱ ከገለጸው ውጪ በመሆኑ #ሊታረም እንደሚገባው የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰጠው መግለጫ እንዳለው፤ ፓልም ኦይል እየተባለ የሚጠራውን ዘይት በየቀኑ መጠቀም ዘይቱ በውስጡ ካለው ሳቹሬቲድ ፋቲ አሲድ አንፃር በረዥም ጊዜ መጠቀም የኮልስትሮል መጠንን ከፍ ያደርጋል ተባለ እንጂ ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም አላልከኵም ብሏል።

በአንዳንድ ሚዲያዎች “ኢንስቲትዩቱ የሚረጋውን ዘይት ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ” ተብሎ የተላለፈው ዘገባ “ከእውነታው የራቀ” መሆኑን የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛህኝ ተስፋዬ አስረድተዋል።

Via waltainfo
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ተቋርጦ የነበርው የኢትዮ-ጁቡቲ የምድር ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የትራስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የጀመረው የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ጉብኝት ካደረጉ በኃላ ነው ተብሏል። የባቡር ትራንስፖርቱ የሀገሪቱን የገቢና የወጪ እቃዎች በማሳለጥ ረገድ ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፡- የትራንስፖርት ሚ/ር
🗞ቀን 14/10/2010 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#1 በአዲስ አበባ ከተማ #ከሰኔ 30 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው የሞተር ብስክሌትና የጭነት ተሽከርካሪዎች መመሪያ:-
#2 በአዲስ አበባ ከተማ #ከሰኔ 30 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው የሞተር ብስክሌትና የጭነት ተሽከርካሪዎች መመሪያ:-
TIKVAH-ETHን በተወዳጁ #ሜዳ_ቻት ላይ ማግኘት ትችላላችሁ...

ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት👇
https://meda.im/join/tikvahethiopia1
#update የኤሌክትሪክ የፈረቃ ስርጭት ምናልባትም ከሰኔ 30 በፊት ፈረቃው ሊቀር እንደሚችል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል።

"ግድቦች እየሞሉ ስለሆን እስከዛም ላይቆይ ይችላል።"

Via #ሸገር102.1
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ በነገው እለት በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ለአገልግሎት ክፍት ሆነው ይውላሉ።

የከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ነው ነገ ቀኑን ሙሉ አገልግሎቱን የሚሰጠው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፍሬህይወት ገብረህይወት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በእለቱ የመዲናዋ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የሙሉ ቀን ነፃ አገልግሎት ይሰጣሉ።

በእለቱም ህብረተሰቡ በነዚህ ተቋማት ተገኝቶ መደበኛ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችልም ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው።

Via ኢ.ፕ.ድ
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አክሱም #Axum

በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የተመራ ልዑካን ቡድን #የአክሱም_ሀውልትን ጎበኘ። ለስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኘው በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒትሯ አማንኤላ የተመራው ቡድን የአክሱም ሀውልት ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በቅርሱ ላይ እየታየ ያለውን ችግር በባለሞያዎቹም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የልዑካን ቡድን አባላቱ ቅርሱ የተደቀነበትን ችግር በአስቸኳይ ለመንግስታቸው በማሳወቅ ቅርሱ ጥገና የሚደረግበትን መንገድ እናመቻቻለን ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ዉስጥም ባለሞያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩም ተናግረዋል።

ልዑካን ቡድኑ በቅርሱ በአካል የተመለከቱትን ችግር ለመንግስታቸው አቅርበው ምላሽ እንደሚያገኙ እምነት እንዳለቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር የባህል ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ ክብርት ቡዝነሽ መሰረት ተናግረዋል።

ቅርሱ በዋናነት የከርስ ምድርና የገፀ ምድር ውሃ መጠን መጨመር ምክንያት በሀውልቱ ስር ያለውን አፈር የመሸርሸር አደጋ በማጋጠሙ ሀውልቱ ላይ የመዝመም አደጋ እንዲከሰት አድርጓል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
2 ዓመት🎂ሀምሌ 19 ~ TIKVAH-ETH

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ የተመሰረተበት ሁለተኛ ዓመት የፊታችን ሃምሌ 19/2011 ዓ/ም ይከበራል። ቤተሰባችን በሁለት አመት ቆይታው ከ300,000/ሶስት መቶ ሺ/ በላይ አባላትን መቀላቀል ችሏል።

የTIKVAH-ETH ቻናል ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በመከባበር፣ በመዋደድ፣ በመቻቻል እና በአንድነት ላይ ተመስርተን እጅግ የሰለጠነችዋን #ኢትዮጵያ ለመገንባት ስለተሰባሰብን እጅግ ኩራት ይሰማናል!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#warning

አዲስ አበባ : መኪና በቁሙ እየጠፋ ነው

#ETHIOPIA | ባለመኪና፤ የሆናችሁ ተጠንቀቁ

#ናፍቆት ዮሴፍ (ጋዜጠኛ - አዲስ አድማስ)
በራይድ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ እየሄድኩ ከሹፌሩ ጋር እያወራን ነበር።

በኔ በኩል ያለውን መስታወት ከፍ አድርጌ ዘጋሁና "ደሞ አንዱ ሌባ ስልኬን እንዳይመነትፈኝ!" ስለው

ምን አለኝ መሰላችሁ

"አንቺ የስልኩ ይገርምሻል እንዴ?! ... መኪና በቁሙ እየጠፋ ነው"

"እንዴት!?" አልኩት

ሁሉንም የመኪና አጣቢዎች ባይመለከትም፤ አንዳንድ መኪና አጣቢዎች ከሌባ ጋር እየተመሳጠሩ ነው"

"እኮ እንዴት?" ቀጠልኩ ጥያቄዬን

"አንቺ የረጅም ጊዜ ደንበኛዬ ነው ብለሽ መኪናሽን ከነቁልፉ ሰጥተሽ አጥቦ እስኪጨርስ ሌላ ቦታ ሻይ ቡና ለማለት ትሄጃለሽ። ሌባው ያኔ በፍጥነት ቁልፍሽን አስቀርፆ ይመጣል። ታርጋሽን ይጽፋል። በአንድ በተረገመ ቀን አንድ ቦታ አቁመሽ ዞር ስትይ እንደራሱ መኪና አስነስቶ እልም!"

"ከዛስ?"

"ከዛማ ለዚሁ ሥራ በቡድን የተከራዩት ግቢ ውስጥ አስገብተው፤ ይፈታቱና ወደሚረከባቸው አካል ይወስዳሉ። የመኪናው ቦዲ የማን ይሁን የማን በምን ይለያል?" አለኝ::

Via Getu Temesgen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎርፍ አደጋ ይከሰታል ተብሎ ተገምቷል...

በ143 ቦታዎች የጎርፍ አደጋ ይከሰታል ተብሎ ተገምቷል። ከነዚህ ውስጥ 43ቱ ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ በቅርቡ አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ #ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ተጠቁሟል። የጎርፍ አደጋውን ለመከላከል አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም የብሔራዊ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል ሰኔ 15 የሚከበርዉን ሰምዐታት ቀን በማስመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስተላለፉት መልዕክት።

#PMOEthiopia
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️

ዶ/ር ጀማል አብዱል ቃድር በአዲስ አበባ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ዶ/ር ጀማል የአፋርኛ ቋንቋ ከ45 ዓመታት በፊት በላቲን ከመፃፍ ጀምሮ የክልሉ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ከማብቃታቸውም ባለፈ በዩኒቨርስቲ በዲግሪ ደረጃ እንዲሰጥ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡

የክልሉ የአፋርኛ ቋንቋ ጥናት እና ማበልፀጊያ ማዕከል በማቋቋም የመሩ ሲሆን ቋንቋው በላቲን የተፃፈበት 45ኛ ዓመት እየተከበረ ባለበት በአሁኑ ወቅት መሞታቸው ለቋንቋው ተናጋሪዎች አሳዛኝ ዜና ሆኗል፡፡

ዶ/ር ጀማል አብዱል ቃድር ሬዶ የዘጠኝ ልጆች አባት ሲሆኑ የቀብር ሰነ-ስርዓታቸው ነገ ቤተሰቦቻቸው ፤ ወደጅ ዘመድ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል መንግስት ስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በአዋሽ ከተማ ይፈፀማል፡፡

Via #etv
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጣና ሐይቅን እምቦጭ ለመከላከል አዲስ የመረጃ ቋት ሥርዓት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ የመረጃ ሥርዓቱን የቀረጸው ዐለም ዐቀፍ የጣና መልሶ ማቋቋም ማኅበር ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ነው፡፡ ማኅበሩ ከአየር ጠቃሚ መረጃዎችን የሚሰበስብ ሰው አልባ በራሪ ካሜራም ወደ ሀገር ማስገባቱን የአማራ መገናኛ ብዙኻን ዘግቧል፡፡ ሥርዓቱ ስለ እምቦጭ አረም የሚቀርቡትን የተለያዩ መረጃዎችና አሃዞችን ፈትሾ መፍትሄዎችን የጠቆመ ሲሆን ዐለም ስለ ጣና ከሚሰበሰበው የመረጃ ቋት በቀጥታ በኢንተርኔት መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል- ብለዋል የማኅበሩ ሊቀመንበር ዶክተር ሰለሞን ክብረት፡፡ ለመረጃ ቋቱም በቅርቡ ድረ ገጽ ይዘጋጅለታል፡፡

Via AMMA/wazema/
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመልካም ወጣት ፕሮጀክትና የማርሲል ቴሌቪዥን መስራች ዮናታን አክሊሉ ዛሬ ከምክትል ጠ/ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግስት መክረዋል።

በዘንድሮው የመልካም ወጣት ስልጠና መርሀግብርና በወጣት ማዕከሉ ግንባታ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡር አቶ ደመቀም መንግስት ፕሮጀክቱን ለማገዝና የማዕከሉም ግንባታ እስኪጠናቀቅ አስፈላጊውን እገዛ ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል እንደገቡ #ክርስቲያን ቲዮብ ዘግቧል።

Via Getu Temsgen
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 7ኛ መደበኛ ጉባኤው አንድነት፤ ምክንያታዊነትና ተጠቃሚነት በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ነው።

🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በአፍሪካ ህብረት ሊሸለም ነው!
---------------------------------------------------------------
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለወጣት አፍሪካዊያን አርአያ በመሆን ላበረከተው አሰተዋኦ በአፍሪካ ህብረት የዋሽንግተን ዲሲ ፅህፈት ቤት የእውቅና ሽልማት ሊበረከትለት ነው።

ህብረቱ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኢትዮጵያም አልፎ ለመላ አፍሪካ ወጣቶች በአርዓያነት የሚጠቀስ አርቲስት መሆኑን አመላክቷል።

በመጪው ሃምሌ ወር በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው የአፍሪካ ሩጫ ጋር ተያይዞ በሚሰናዳው ዝግጅት ላይ ሽልማቱ እንደሚበረከትለት ታውቋል።

በዋሽንግተን የአፍሪካ ህብረት ፅህፈት ቤት ዋና ተጠሪ ዶክተር አሪካና ችሆምቦሪኮ ሽልማቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኢትዮጵያም አልፎ ለመላ አፍሪካ ወጣቶች አርዓያ ነው።

አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን በሙዚቃው ዘርፍ ተግቶ በመስራት ለአፍሪካ ወጣቶች ያበረከተዉ አስተዋፆ የጎላ በመሆኑ የሚሰጠው እዉቅና ትርጉም ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።

በአፍሪካ ህብረት የዋሽንግተን ዲሲ ፅህፈት ቤት የላከለትን መግለጫ ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው።

Via #ENA
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ👆

የሰማእታት ቀን ለ31ኛ ጊዜ መቐለ በሚገኘው የሰማእታት ሃውልት ዛሬ ተከብሯል። በበዓሉ ከፍተኛ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮችና የከተማው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ አመራሮች፣ የሰማእታት ቤተሰቦች፣ ነባር ታጋዮችና አካል ጉዳተኞች ጨምሮ የተለያዩ አካላት በሃውልቱ ስር የጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል።

"የሰማእታትን በዓል ስናከብር የወደቁለትን አላማ ከዳር ለማድረስ ቃላችንን በማደስ ሊሆን ይገባል’’ ም/ር/ መስተዳድር ደብረ ጽዮን
.
.
NB. በዛሬው ዕለት የሚታሰበው የሰማዕታት ቀን የደርግ መንግሥት ሰኔ 15 ቀን 1980 በሐውዜን ከተማ ገበያ ከ2ሺህ 500 በላይ ሰላማዊ ዜጎችን በጦር ሄሊኮፕተሮች ድብደባ የጨፈጨፈበት ቀን በመሆኑነው።

Via ኢዜአ
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቤተሰቦች በደቡብ ኢትዮጵያ! በምስሉ ላይ የጋሞዎችን የባህል ልብስ “ዱንጉዛን” ለብሰው የምናያቸው ቀዳማዊት እመቤት ሳባ ሀይለ፤ አብርሃም ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ብርሃነ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ኤልሳ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። በቅርብ ሳምንታት በደቡብ ኢትዮጵያዊ ተገኝተው ጉብኝት አርገው ነበር።

Via Petros Ashenafi Kebede
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሥራ አቆመ!

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ በመምህራንና ሰራተኞች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሥራ አቁሟል፡፡ በመምህራን ላይ የመደፈር፣ ንብረት የመዘረፍና ከሥራ ገበታቸው የመባረር ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ነው የተባለው፡፡ የተለያዩ ሦስት ባንኮችም የዝርፊያ ሙከራ እንደተደረገባቸውና ጭንብል ያጠለቁ የተደራጁ ቡድን ከጥበቃዎች ላይ ማሳሪያ እየለቀመ መውሰዱም ተገልጿል፡፡

Via #VOA
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የሚከለክለውን መመሪያ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በሞተር ብስክሌት ከሚተዳደሩ ዜጎች የወጣት ጥላሁነ ታደሰ አጭር ታሪክ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል።

Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethipia