TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እናት ነበረች ልጇን የገደለችው-ደሴ‼️

‹‹ፖሊስን #በማድከሜ እና ህዝቡን #በተሳሳተ መረጃ በማስቆጣቴም ተጸጽቻለሁ፡፡›› እናት
.
.
.
ባለፈው ሳምንት ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ላይ አንድ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መፈጸሙን ተዘግቦ ነበር፡፡ ድርጊቱም አንዲት የ7 ዓመት ህጻን #ከተደፈረች በኋላ እንደተገደለች የሚገልጽ ነበር፡፡

በዕለቱም ተጠርጣሪዉ በፖሊስ መያዛቸውን እና ድርጊቱም ነዋሪዎችን ማስቆጣቱን ነበር የተዘገበው፡፡

አሁን ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ደግሞ ጥርጣሬው ወደ ሌላ አካል እንዳመራ ያስረዳል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራትም የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረጃ አሰፋን አነጋግሯል፦ ኮማንደሩም መረጃው ትክክል መሆኑን ነው ያረጋገጡት፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው ጥቅምት 24/2011 ዓ.ም ነበር፡፡ ቦታውም ደሴ ከተማ ነው፡፡ በዕለቱም ወላጅ እናት ‹‹ልጄ ጠፋችብኝ›› ብለው ለፖሊስ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ፖሊስም የምርመራ መጀመሪያውን እናት በሚሰጡት #ጥቆማ ላይ ያደርጋል፡፡የእናት ጥቆማ ደግሞ የቀድሞ የትዳር አጋራቸው ላይ ያርፋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ከዚህ በፊት በህጻኗ ላይ ይዝቱ ነበር የሚል ነው፡፡

ፖሊስም ጥቆማውን ተቀብሎ ምርመራውን ይቀጥላል፡፡ ከዚህ ላይ አሳዛኝ ድርጊት ተፈጽሞ ይገኛል፡፡ህጻኗ ተገድላ እና ተጥላ ነበር ፖሊስ ያገኛት፡፡ ፖሊስም ለምርመራ አስከሬኑን ወደ ደሴ እና ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ይልካል፡፡

በዕለቱ ደግሞ ተጠርጣሪው በግምት ከምሽቱ 3፡00 አካባቢ በቁጥጥር ሰር ይውላል፡፡ ፖሊስም ምርመራውን ይቀጥላል፡፡ እየተገኙ የነበሩ ቁሳቁሶችና መረጃዎች ግን ፖሊስ ምርመራውን በእናት ላይም ማድረግ እንዳለበት ፍንጭ የሚሰጡ ነበሩ፡፡ በሂደትም ምርመራውን በእናት ላይ ይጀምራል፡፡ የፖሊስን ጥርጣሬ የሚያጎላ መረጃም ያገኛል፡፡አሁን የመጀመሪያው ጥርጣሬ ሚዛን ወደ ሌላ አቅጣጫ ይዞራል፤ እናት የሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ሌላ ገጽታ ነበረውና፡፡

እናት ይነገራሉ ‹‹ልጄን #የገደልኳት እኔ ነኝ፤ ድርጊቱን የፈጸምኩት ግን ልጄን ለመቅጣት እንጂ ለመግደል አስቤ አልነበረም፤ እስካሁን ፖሊስን በማድከሜ እና ህዝቡን በተሳሳተ መረጃ በማስቆጣቴም ተጸጽቻለሁ›› ነበር ያሉት
ይላል የፖሊስ መረጃ፡፡

እናት በሰጡት ቃል እንደተመላከተው ለልጃቸው ልብስ ከገዙላት በኋላ ‹‹ለምን ጫማ አልተገዛልኝም?›› በሚል ጭቅጭቅ ይፈጠራል፡፡ መግባባትም አልቻሉም ነበር፡፡ በዚህም እናት በልጃቸው ላይ አካላዊ ቅጣት ይፈጽማሉ፤ በድንገትም ህጻኗ እስከወዲያኛው ታሸልባለች፡፡

በድረጊቱ የተደናገጡት እናት የልጃቸውን አስክሬን ከአካባቢው ሰውረው ነበር ለፖሊስ ጥቆማውን ያቀረቡት፡፡ እናት ቃላቸውን ለደሴ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤትም ሰጥተዋል፡፡ ተጠርጣሪዋም ለጊዜው በደሴ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፖሊስ ግን ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ጠይቋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከሆስፒታሉ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን እስከሚያገኝ እና መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙት ሁለተኛ ተከሳሽ ላይም ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ ስለፈለገ ነው ብለዋል ኮማንደር ደረጀ አሰፋ፡፡ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ግን ወደ ፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ (አስማማው በቀለ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia