TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦሮሚያ! የተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ተሰምቷል።

መንገዶች እየተከፈቱ እንደሆነ ለመስማትም ችያለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍርድ! የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላልፏል። ስደተኞቹ በኮንቴይነር ተጭነው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሲሻገሩ ነው የተያዙት።

ምንጭ፦ Hahu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሴትነት! ሴትነት ሰው የመሆን ሁለንተናነት ነው። አንድ ሰው የሴትነትን ታላቅነት ካልተረዳ ገና ሰው የመሆንን ሚስጢር አልተገነዘበም ማለት ነው። ምክንያቱም ሴት እናት ነች። እናት ደግሞ የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰን የፍቅርን ምንነት መገለጫ ናት። ታዲያ ከፍቅርና ፍቅርን ከማወቅ በላይ ምን ታላቅ የህይወት ሚስጢር ይኖራል? ምንም አይኖርም።

ሌላው ታላቅ ከሚያደርጓት ነገሮች ደግሞ በህይወት ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋፍጣ በብልሃት እና አሸናፊነት የምትወጣ ጠንካራ ፍጥረትነቷ ነው።

ሩህሩህነትን ከአፍቃሪነት ጋር ታድላ የተፈጠረች ለወንድ የህይወቱ ማገር እና ምሶሶ ናት። ወንድ ያለ ሴት ሙሉነት እና የህይወት ጣእም የሌለው ያላለቀ የእግዜር ጅምር ስራ ነው።

ሴት ልጅ ስቃይዋን እና ሃዘኗን መደበቅ ካስፈለጋት መከፋትዋን ሳታሳይ ደስተኛ በመምሰል ለምትወደው ሃሴትን መስጠት የምትችል ረቂቅ ፍጠረት ናት።

ሴትነትን ሆነው ካላዩት በእርግጥ ስለ ሴትነት ሙሉ በሙሉ መናገር የሚቻለው አይኖርም። ረቂቅ እና የህይወት ጣእም ሚስጢር አድርጎ ከፈጠራት ፈጣሪ በስተቀር።

ሴት ልጅ ከወንድ የጎን አጠንት ብትሰራም በህይወት ዘመኑ የጀርባ አጥንቱ ሆና ብርታትን እና ፀናትን የምትሰጠው “ሃይል” ናት። የታላላቅ ስኬቱ ጀንበር ሆና የምትፈነጥቅለት ነገር ግን ከእርሱ ልቃ የማትታይ የመድመቂያው ጮራ መፍለቂያ ናት።

ሴት ልጅ ከልብ የመነጨ ክብር ይገባታል። ሴትን የሚያከበር ራሱን የሚያከብር ነው። ሴትን የማያከብር ቢኖር የህይወትን ጣእም እና ፍቅርን ካለማወቁም በላይ ሰው የመሆን ብቃት የጎደለው ነው።

ምንጭ ፦ ደምቢካ(ከፌስቡክ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢነርጅ ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተወያይተዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያ! የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ እርቀ ሰላም ለማውረድ ተስማሙ።

ሁለቱ ወገኖች በሃገሪቱ ቴሌቪዥን በጋራ በሰጡት መግለጫ በቀጣይ ያሉ ልዩነቶችን በውውይት ለመፍታት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ውጤቱን አልቀበልም በሚል የተፈጠረው ውዝግብ ለ150 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶሪያ! ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የተመድ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ወደ ምሥራቃዊቷ የሦርያ ከተማ ጉታ የሚሄደውን እርዳታ የጫኑ ካሜዎኖች ዛሬ ዐርብ መንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል። ነገር ግን በአካባቢው የሚካሄደው የአየር ጥቃት በአስቸኳይ የተፈለገውን እርዳታ ማራገፍ እንዳላስቻለ ታውቋል።

ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትማሩ ተማሪዎች ካላችሁ ስለ ትላንትና ማታው ጉዳይ መረጃዎችን አቀብሉኝ።

@tsegabwolde
ኦሮሚያ! ከትላንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በኦሞናዳ ወረዳ አሰንዳቦ በተባለች ቦታ በቄሮዎችና በታጠቁ የመከላከያ ሠራዊት አባላይ መካከል በተፈጠረ ግጭት ወጣቶች በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸውን ከቄሮ፣ ከወጣቶችና ከሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። በሌሎች የክልሉ ከተሞችም ግጭትና ውጥረት መኖሩን ነዋሪዎች ለVOA ተናግረዋል።

ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቲለርሰን! ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መልሱ "የበለጠ ነፃነት እንጂ መገደብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መልሱ "የበለጠ ነፃነት እንጂ መገደብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ሃገራቸው ስትገልፅ የቆየችውን አቋም ያጠናከሩት ቲለርሰን መሰብሰብንና ሃሣብን የመግለፅ
ነፃነትን የመሳሰሉትን መብቶች እንደሚገድብ አመልክተው አዋጁ በተቻለ ፍጥነት እንዲነሣ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያዊያን ዜጎችም ሃሣባቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ የመግለፅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ቲለርሰን አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዋልድባ መነኮሳት! በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ለአንድ አመት ያህል በአንድ ልብስ ብቻ በጨለማ ቤት መቆየታቸውን ለፍርድ ቤት ገለጹ።

በተለይም በአባ ገብረስላሴና በአባ ገብረየሱስ ላይ የተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት አስከፊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤቱን መልስ ከተቀበለ በኋላ ሁኔታውን መርምሮ መልስ እንደሚሰጥ ገልጿል።

እስረኞቹን ለመጠየቅ የመጡ ሰዎች ለመነኮሳቱ ልብስ እንዲሰጡም ፍርድቤቱ መፍቀዱ ታውቋል።

የዋልድባ መነኮሳት ክሳቸው እንደተቋረጠ በሪፖርትር ጋዜጣ መገለጹ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የመነኮሳቱ የክስ ሂደት ዛሬም በፍርድ ቤት መቀጠሉ ነው የተነገረው።

ትላንት የካቲት 30 በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ታዲያ የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤቱ የደረሰባቸውን እንግልትና ስቃይ ለዳኞች አስረድተዋል።

መነኮሳቱ ለአንድ አመት ያህል ልብስ እንዳይቀይሩ ከመደረጋቸውም ሌላ በጨለማ ቤት ውስጥ ተለያይተው እንዲቀመጡ መደረጉንም ነው ለችሎቱ የገለጹት።

በተለይም አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነማርያም ዞን አምስት ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት በጨለማ ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን ስቃይ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

አባ ገብረስላሴ ለአንድ አመት ያህል ልብስ ሳይቀይሩ በጨለማ እስር ቤት መቆየታቸውም ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል። ፍርድቤቱም ይህ ለምን እንደሆነ ጠይቆ ከእስር ቤቱ በደብዳቤ ምላሽ በማግኘቱ ሁኔታውን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለመጋቢት 5/2010 ቀጠሮ ሰቷል።

ዳኞቹ ለመነኮሳቱ ለምን ልብስ እንዳይገባ ተደረገ ሲሉ በጠየቁ ጊዜ ችሎቱን ሲከታተሉ ከነበሩ ጠያቂዎች አንዱ ልብስ ይዞ በመገኘቱ ዳኞቹ እንዲሰጣቸው አድርገዋል ነው የተባለው። የእስር ቤቱ ሃላፊ ልብስ እንዳይሰጣቸው ቢከለክሉም ዳኞቹ ልብስ እንዲሰጥ ማድረጋቸውን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዋልድባ መነኮሳቱ መደበኛ ክስ መጋቢት 18 እንደሚቀጥልና ምስክሮችን የመስማት ሒደት እንደሚኖርም ተገልጿል።

ምንጭ፦ አቶ ጌታቸው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትነበርሽ! ለሴቶች መብት ለአካል ጉዳተኞች መብትና ዕኩልነት ተሟጋች ጠበቃዋ፣ የትነበርሽ በማርች 08 ዓለምቀፍ የሴቶች ቀን የከፍተኛ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።

መሰረቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ሔለን ኬለር ኢንተርናሽናል የዘንድሮ ‘Spirit of Award’ የሄለን ኬለር መንፈስ ሽልማት ሰጥቷታል።

የትነበርሽም በአሁኑ ጊዜ የምትሰራበት “ላይት ፎር ዘ ዎርልድ” የተሰኘው ድርጅት ለመጀመሪያ ታላላቅ ክንዋኔዎች ላስመዘገቡ አካል ጉዳተኛ ሴቶች የሚሰጠውን አዲስ ዓመታዊ ሽልማትም አስተዋውቃለች።

ምንጭ፦ ቆንጅት ታየ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ምክንያቶች ለወራት ተቋርጦ የነበረው የTIKVAH-ETH የማስታወቂያ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል።

ይህ ቻናል ለማስታወቂያ ክፍት ነው !

በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም የምትገኙ ኢትየያዊያን በተመጣጠነ ክፍያ ምርታችሁን ለማስተዋወቅ እና ለህዝብ ለማድረስ ዝግጁ ነን።

🔘የጉዞ ወኪሎች
🔘አስመጪ እና ላኪዎች
🔘የልብስ እና የጫማ አቅራቢዎች
🔘የኤክትሮኒክስ እቃ አቅራቢዎች
🔘ሌሎችም ማንኛውም ነገሮች እንዲተዋወቅላችሁ የምትፈልጓቸው ነገሮች ካሉ ይስተናገዳሉ።

ማስታወቂያዎቹ በድምፅ አልያም በፅሁፍ ሊሆኑ ይችላሉ።

ዝርዝር ጉዳዮች ክፍያን በተመለከተ በዚህ አድራሻ ማናገር ይቻላል @tsegabwolde

@tikvahethiopia
ጥሩነሽ ዲባባ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋን አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ባራንድ አምባሳደር አድርጎ በማርች 08(በአለም የሴቶች ቀን) መርጧታል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ! የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ያደረጉትን ካራቫት ተመልከቱት...

ሀ ሁ ሂ...
ለ ሉ ሊ....
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋጋ ጭማሪ! በአዲስ አበባ ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች እና የግንባታ እቃዎች ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

ንግድ ቢሮው ጉዳዩና እና በበጀት
ዓመቱ የስምንት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

ከሰሞኑ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በግንባታ ግብአት እቃዎች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ቢሮው ማረጋገጡን ገልጿል።

በተለይ እንደ ስኳር፣ ዘይት እና ፕስታ ያሉ የፍጆታ እቃዎች እና የብረታ ብረት ላይ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ ቢሮው አመልክቷል።

ምንጭ፦ ጌታቸው ባልቻ(EBC)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቲለርሰን በኬንያ! የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴለርሰን ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኋላ ወደ ኬንያ አቅንተዋል፡፡

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ሞኒካ ጁማ እና በኬኒያ የአሜሪካ አምባሳደር ሮበርት ጎርደን አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ከፕሬዝዳት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በንግድ እና በሰላም ዙሪያ መክረዋል፡፡

የሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን መረጋጋት እና ፀጥታ ለቀጠናው ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ የሁለትዮሹ ግንኙነት በጉዳዩ ዙሪያ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም መክረውበታል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቲለርሰን በቀጣይ ሶስት የአፍሪካ ሃገራትን የሚጎበኙ ሲሆን ሽብርተኝነትን መዋጋትና የሁለትዮሽ የንግድ ምህዳሩን ማስፋት የሚመክሩባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሆኑ ኬ ቲዌንቲ ፎር ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ K24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መምህር ስዩም! ፖሊስ በጦማሪና መምህር ስዩም ላይ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠየቀ።

በአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህር የሆነው አቶ ስዩም ተሾመ ከትላንት በስቲያ የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወቅ ነው።

አቶ ስዩም በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ወደ ማዕከላዊ የተወሰዱ ሲሆን ትላንት የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ የጊዜ ቀጠሮ ፍ/ቤት ቀርበዋል።

ፖሊስ አቶ ስዩም ኦሮሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን አመፅ ለማደራጀት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ገልፆ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል።

ፍ/ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን
የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ለመጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዛሬ መጋቢት 01 ቀን 2010 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) አቶ ስዩምን ለመጠየቅ መገኘታቸውን አቶ ፋሲካ አዱኛ ገልፀዋል።

አቶ ፋሲካ አዱኛ አቶ ስዩምን ስማቸውን አስመዝግበው ከገቡ በኋላ አግኝተው
እንዳነጋገሯቸው ለዚህ ዜና ፀሐፊ ገልፀዋል።

አቶ ስዩም ወሊሶ በተያዙበት ወቅት በመከላከያ ሰራዊት አባላት መያዛቸውንና ድብደባ እንደተፈፀመባቸው እንደገለፁላቸው አቶ ፋሲካ አስረድተዋል።

ድብደባው የተፈፀመውም የላፕቶፖቻቸውን ፓስወርድ እንዲሰጡ በማስገደድ መሆኑን አቶ ስዩም ገልፀዋል።

በድብደባው ብዛትም የላፕቶፖቻቸውን ፓስወርድ እንደሰጡ አቶ ስዩም አስረድተዋል። በመኖሪያ ቤታቸው መያዛቸውን የገለፁት አቶ ስዩም የመከላከያ ሰራዊት አባላቶቹ በቤታቸው የሚገኙ ንብረቶቻቸውን ማውደማቸውን ገልፀዋል። ከቤታቸውም 3 ላፕቶፖችን እንደወሰዱባቸው አያይዘው ገልፀዋል።

አቶ ስዩም ተሾመ ባሳለፍነው ዓመት የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በጦላይ የፖሊስና ወታደራዊ ማሰልጠኛ ታስረው መለቀቃቸው የሚታወስ ነው። በጦላይ በታሰሩበት ወቅትም ከፍተኛ
ድብደባ ተፈፅሞባቸው እንደነበር ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዮኤል ፍስሀ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታሪክን የኋሊት! አፄ ዮሐንስ ፬ኛ የዛሬ 129 ዓመታት በዛሬ ቀን (10 March 1889) ነበር በመተማ ዉጊያ ህይወታቸውን ያጡት።

"አፄ የሓንስ ሞኝ ናቸው
እኛም ሁላችን ናቅናቸው፣
ንጉሥ ቢልዋቸው በመሃሉ
ወሰን ጠባቂ ልሁን አሉ"

ክብር ለሁሉም ሰማእታት ንጉሶቻችን!
*
አፄ ዮሐንስ ፬ኛ በዚህ ንግግራቸዉም ይታወቃሉ፣

“የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።“

(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስፖርት! ወላይታ ዲቻ ከወልዲያ የሚያደርገው ጨዋታ ነገ እሁድ ይደረጋል፡፡

ጨዋታው በመርሀግብሩ መሰረት ዛሬ ሊካሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን ሳይካሄድ ቀርቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦፌኮ አቋም! የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቲለርሰን አዲስ አበባን በጎበኙበት ወቅት የተቃዋሚዉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባለሥልጣናትን እንዳላነጋገሩ የፓርቲዉ መሪዎች አስታወቁ። የኦፌኮ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙላቱ ገመቹ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ የሚወገደዉ በኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በዉጪ ኃይል አይደለም። ካለፈዉ አርብ ጀምሮ በተደረገዉ አድማ እና ተቃዉሞ ሰበብ በሰዉ ሕይወት አካል እና ሐብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም አቶ ሙላቱ አስታዉቀዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት የተሸከመው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም!

"ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም። በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለበት።
.
.
መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልይ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ"

ምንጭ፦ አቡነ አብርሀም በባህርዳር ከተማ ከሁለት አመት በፊት የመስቀል በዓል ሲከበር ለህዝብ ከተናገሩት መርጬ የወሰድኩት
@tsegabwolde @tikvahethiopia