#update በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ሳቢያ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በሽታው ከሚያዝያ 18/ 2011 ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ እንደተከሰተ የኢንስቲትዩቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የኅብርተሰብ ጤና ስጋት ቅብብል ባለሙያ አቶ አሞኘ በላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"እስካሁን በሦስት ወረዳዎች እነሱም በሰሜን ጎንደር ጠለምት እና በይዳ ወረዳዎች እንዲሁም በዋግህምራ ዞን ደግሞ አበርገሌ በሚባል ወረዳ በሽታው ስለመከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል" ብለዋል።
በጤና ተቋምና ባለሙያዎች ቤት ለቤት እየሄዱ ባደረጉት ሪፖርት መሠረት፤ እስከትናንት ድረስ 190 ገደማ ሰዎች በአተት መያዛቸውን ባለሙያው ገልጸዋል። "በአተት ምክንያት በተቋም ደረጃ መሞታቸው የተረጋገጠው 5 ሰዎች ናቸው" ብለዋል።
አቶ አሞኘ እንደሚሉት፤ በሽታው የመቀነስ እዝማሚያ እያሳየ ቢሆንም በቁጥጥር ሥር ማዋል ግን አልተቻለም። "አሁን ባለው ሁኔታ ሰሜን ጎንደር ላይ ተቆጣጥረነዋል ማለት ይቻላል። እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ ምንም አይነት ህመምተኛ ሪፖርት አልተደረገም" ይላሉ።
ሆኖም አበርገሌ ላይ አልፎ አልፎ ሪፖርት እንደሚደረግ ያስረዳሉ።
"ትናንት ሪፖርት አልነበረም። ቆሟል ማለት አይቻልም። አሁን ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ነገር ግን ቆሟል ከእንግዲህም አይነሳም የምንልበት ሁኔታ የለም። ምክንያቱም ሰፊ ሥራ ይጠይቃል" ሲሉ አቶ አሞኘ ይገልጻሉ።
የተከሰተው አተት ነው ወይስ ኮሌራ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ "አተት በተለያዩ ነገሮች ሊከሰት ይችላል። በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፕሮቶዞዋ ወይም በምግብና ውሃ መመረዝ ሊከሰት ይችላል።
አተት ከሚያመጡት ውስጥ አንዱ ባክቴሪያ ሲሆን፤ ከባክቴሪያዎቹ ውስጥ ደግሞ አንዱ ኮሌራ ነው፤ ልዩነታቸው ይሄ ነው። አተት ሰፊ ነው። በብዙ ነገሮች ሊከሰት የሚችል ማንኛውም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ማለት ሲሆን፤ ኮሌራ ማለት ግን አተትን ከሚያስከትሉ ባክቴሪያዎች አንዱና በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት ነው" ብለዋል።
አተት በብዙ ነገሮች ሊከሰት ስለሚችል እያንዳንዱ ኮሌራ እየተባለ ሪፖርት በቢደረግ ስህተት ሊፈጠር እንደሚችልም ተናግረዋል።
አክለውም "ናሙና እየወሰዱ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፤ ማንኛውንም ምልክት የሚያሳይ ሰው አተት በሚል መረጃውን እየተቀባበልን የመከላከልና መቆጣጠር ሥራ እንሠራለን" ብለዋል።
ማንኛውም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ያለበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ እንዳለበት አቶ አሞኘ አሳስበዋል።
አሁን የተከሰተውን ችግር ለመከላከል ባለሙያዎችና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደቦታው በመላክ ከአጋር ተቋማት ጋር እየሠሩ መሆኑንም ባለሙያው ገልጸዋል።
Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ካሳዬ አራጌ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና የስራ አመራር ቦርድ በአዲስ መልክ ካዋቀራቸው ኮሚቴዎች ውስጥ የእግር ኳስ ኦፕሬሽንና ቴክኒክ አስተዳደር ኮሚቴ (ቴክኒክ ኮሚቴ) አንዱ ነው። ይህ ኮሚቴ በቦርዱ በተሰጠው መመሪያ መሰረት የመጀመሪያ ስራ የአሰልጣኝ ቅጥርን ማከናወን ነበር።
በዚህም መሰረት በ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን አሰልጣኝ ለመምረጥ የተለያዩ መመዘኛዎች በማውጣትና የኢትዮጵያ ቡና የሚታወቅበትን የጨዋታ ዘይቤ በጥልቀት ይረዳል በሚል መነሻነት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና የመሀል ሜዳ ቴክኒሻን ካሳዬ አራጌን መርጧል። ከሚኖርበት ሀገረ አሜሪካ በፍጥነት መጥቶ ባለው አጠቃላይ ሁኔታዎች ከቦርዱ ጋር ከተነጋገረ እና ስምምነት ላይ ከተደረሰ የ2011ዓ.ም የውድድር አመት ሳይጠናቀቅ የተጫዋቾች ምርጫ እንዲያደርግ ዛሬ ከውሳኔ ተደርሷል።
Via Ethiopian Coffee Sport Club - Team Page

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሊቨርፑል እና የቶተናም ደጋፊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ...
በነገው ዕለት በእንግሊዞቹ ሊቨርፑልና ቶተንሃም ክለቦች መካከል በስፔኗ መዲና ማድሪድ ለሚካሄደው የአውሮፓ ቻምፒዬንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ለመታደም የሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሲጓዙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
UEFA Champions League
Liverpool FC Totenham #UCLfinal #Madrid #UCL #ChampionsLeague #LIVTOT
Via #PetrosAshenafi

"ተፈናቃዮች ያለፍላጎታቸው እየተመለሱ በሚል በአንዳንድ ወገኖች የሚሰራጨው አሉባልታ ሀሰት ነው"-- ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
ተፈናቃዮች ያለፍላጎታቸው እየተመለሱ በሚል በአንዳንድ ወገኖች የሚሰራጨው አሉባልታ ሀሰት መሆኑን ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታውቀዋል።
በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት 2 ሚሊዮን 332 ሺህ 936 ዜጎች መፈናቀላቸውን ጠቁመው፣ ከነዚህ ውስጥ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑት የተፈናቀሉት ከመጋቢት 2010 ዓ.ም በፊት ሲሆን፣ 1.1 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም ወዲህ መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከተፈናቃዮቹ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በዛው በክልላቸው ውስጥ የተፈናቀሉ ሲሆኑ፣ ቀሪዎች ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የተፈናቀሉ መሆናቸውን ወ/ሮ ሙፈሪሃት አስታውቀዋል፡፡
Refugee International የተባለ አለም አቀፍ ተቋም ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግስት ተፈናቃዮችን በግድ ወደመጡበት እየመለሰነ ነው ብሎ መግለጫ አውጥቶ ነበር።
Via FBC

ፎቶ: ለዛሬው የሻምፒዎንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ 800 ያህል በረራዎች ወደ ማድሪድ፣ ስፔን ይደረጋሉ። ድሮ ድሮ የምእራባውያን አየር መንገዶች በብዛት ተቆጣጥረውት የነበረውን ይህን አይነት ሰሞንኛ የበረራ አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተቀላቅሏል። ከእንግሊዝ ወደ ስፔን በርካታ በረራዎችን እያደረገ በዛውም የድርሻውን እያገኘ ነው። አለም አቀፍ ድርጅት ሲኮን እንዲህ ነው።
Via @eliasmeseret
Photo:Ethiopian Airlines
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via @eliasmeseret
Photo:Ethiopian Airlines
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ በቦሌ ክ/ከተማ በመንግሥት በጀት እና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ በርካታ ፕሮጀክቶችን ስራ አስጀምረዋል፡፡
-
ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ ተቋማትን በአንድ አከባቢ በመገንባት ለህብረተሰቡ ምቹ እና ፈጣን አገልግሎት እንዲሰጡ ታስቦ የተገነቡ ናቸው፡፡
ዛሬ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል 10 ጤና ጣቢያ ፣ 98 የንግድ ሼዶች ፣ 9 የአንደኛ እና ሁለተኛ የመማርያ ት/ቤቶች ፣ 6 የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች እና 13 የወሳኝ ኩነት ማዕከላት ይገኙበታል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አሰተዳደሩ የህብረተሰቡን አቅም ባገናዘበ መልኩ ጥራት ያለው ትምህርትን በመንግስት ት/ቤቶች ለመስጠት ከምን ጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሰራ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
በ2012 የትምህርት ዘመን የከተማ አስተዳደሩ 600ሺ ለሚሆኑ በከተማዋ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ (ደብተር ፣ እስክርቢቶ ፣ እርሳስ እና የመሳሰሉትን) እንደሚያቀርብም አስታውቀዋል፡፡
በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የክረምት የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የአከባቢው ነዋሪዎች ፣ ወጣቶች እና መምህራን እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via @mayorofficeAA

"ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ባለሃብቶችን እና ለጋሾችን በማስተባበር የትምህርት ቁሳቁስ(ደብተር ፣ እስክርቢቶ እና እርሳስ) በነፃ እናቀርባለን፡፡" ኢ/ር ታከለ ኡማ
.
.
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከቦሌ ክፍለከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በተለይም በማስፋፍያ አከባቢ በጋራ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ያለባቸውን የመሠረተ ልማት ችግር ፣ የገበያ ማዕከላት የትምህርት ቤት ና የእምነት ተቋማት በአቅራቢያቸው አለመኖር ፣ የትራንስፖርት ችግር እና የኑሮ ውድነት ዙሪያ ጥያቄአቸውን ለኢ/ር ታከለ አቅርበዋል፡፡
ኢ/ር ታከለ በበኩላቸው በከተማዋ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
የመሠረተ ልማትን በተመለከተ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት እና ጤና ተደራሽነትን ለማስፋት ከሁሉም ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የቤተ-እምነት የይዞታ ጥያቄዎችን በተመለከተ የከተማ አስተዳደሩ ከሁሉም ቤተ-እምነት ከተውጣጡ ኮሚቴዎች ጋር እየሰራ እንደሆነ እና ለሁሉም ቤተ-እምነቶች የሚገባቸውን ብቻ እንዲወስዱ እንደሚደረግ እና የማይገባቸውንም በስምምነት እንዲመልሱ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ከ1000 በላይ የሚሆኑ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤትን ለማደስ ዕቅድ እንደያዘ እና የቦሌ ክፍለከተማ ነዋሪዎችም በአከባቢያቸው ያሉ የአረጋዊያን እና እናቶችን ቤት እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የየርገን ክሎፕ እርግማን በዋንጫ ተገታ!!
ሊቨርፑል የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆኗል። ቀያዮቹ በነጫጮቹ ላይ የ2 ለ 0 ድል አስመዝግበዋል። ጨዋታው እንደተጀመረ ግብፃዊው መሀመድ ሳላህ በፍፁም ቅጣት ምት እና ተቀይሮ የገባው ቤልጂየማዊው ዲቮክ ኦሪጊ በጨዋታ የመርሲ ሳይዱን ቡድን ድል ያወጁ ጎሎቾ አስቆጥረዋል። ይህ ድል ለሊቨርፑል ስድስተኛ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሆኖ ተመዝግቧል። አሁን በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም You will never walk alone የሚለው ልብ ገዥ ዝማሬ ከፍ ብሎ እየተዘመረ ነው። አንፊልድን እና መርሲ ሳይድን ይሄኔ ላየው ...
Via artstv

"ተፈናቃዮች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ" - የሰላም ሚኒስቴር
በኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውንም ገልጿል።
በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ተግባር “በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና ክብራቸውን በጠበቀ” መልኩ የተከናወነ ነው ብለዋል። “ተፈናቃዮች አለፍላጎታቸው እየተመለሱ ነው” በሚል የሚቀርቡ ወቀሳዎችም “ሀሰት” ሲሉ ሚኒስትሯ አስተባብለዋል።
ወ/ሮ ሙፈሪሃት በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሁለት ሚሊዮን 332 ሺህ ገደማ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውሰዋል። ከእነዚህ መካከል ግማሽ ያህሉ የተፈናቀሉት ከመጋቢት 2010 ዓ ም በፊት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በክልላቸው ውስጥ የተፈናቀሉ መሆኑንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ስልጣን ከያዙ ከሚያዝያ 2010 ዓ. ም. ወዲህ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 1.1 ሚሊዮን ነው ተብሏል።
Via #DW

ከአዳማ...
"በአሁን ሰዓት በአዳማ ከተማ (ኮሌጅ አካባቢ) የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር ያዘጋጀው የዙር ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።"
(ፎቶ ብሩክ)