TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ከባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋር❤️ኦሮሞ👆

የኦሮሞ እና አፋር ክልል ህዝቦች የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

በመድረኩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶች እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

መድረኩ የሁለቱን ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ትስስር በቀጣይነት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በወንድማማችነትና አንድነት መድረኩ ላይ የሚሳተፉ በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የሚመራ ልዑክም በትናንትናው ዕለት አዳማ ከተማ ገብቷል።

ልኡካኑ አዳማ ከተማ ሲደርሱም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ፦

ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በክልላችን የተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር መከሠቱና በሰው ህይበወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱና በርካቶች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀል የደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ የክልሉ መንግሥት ከመከላከያ ሠራዊት ፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከተጎራባች የኦሮሚያና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ጋር በመቀናጀት ግጭቶችን ለማስቆም ፣ ግጭት የተከሰተባቸውን አካባቢዎች ፀጥታ ለማረጋገት ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀድሞ ቀያቸው ለመመለስና በግጭቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑም ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም አጠቃላይ ሀገራዊና ክልላዊ የፀታና የሠላም ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም በተለይም በመተከል ዞን በዳንጉር ፣ በማንዱራ፣ በፓዊና በድባጢ ወረዳዎች ተከስተው በነበሩ ግጭቶች መሠረታዊ መነሻ ምክንያቶች ፣ ግጭቶቹን ለማስቆም በተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ፣ እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

ውሳኔ 1፦

ግጭት በተከሰተባቸውም ሆነ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ድምፅ አልባ መሣሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ውሳ 2፦

በልዩ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ የክልሉ ሚሊሻ ዓባላትም ሆኑ የቀበሌ ታጣቂዎች ህጋዊም ይሁን ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ውሳኔ 3፦

በተደራጀ መንገድም ሆነ በተናጠል ወደ አማራ ክልል አዋሳኞች ጥቃት ለመፈፀም የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት እንቅስቃሴዎች ፍፁም ህገ-ወጥ ፣ በየትኛውም አካላ ተቀባይነት የሌለውእና የተወገዘ ከመሆኑም ባለፈ በልዩ ሁኔታ በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡

ውሳኔ 4፦

ከመከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ውጭ በአስተዳደር ወሰን አካባቢዎች የክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ በ5 ኪሎ ሜትር ራዲዬስ ውስጥ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ ነው፡፡

የፀጥታ ምክር ቤቱ እነዚህን ውሳኔዎች ለጋራ ሠላምና ፀጥታ እጅግ በጣም ወሳኝና መሠራተዊ መሆናቸውን በጥልቀት በመገንዘብ የመተከል ዞንና ከፍ ሲል በተጠቀሱት አራት ወረዳዎች የተዋቀሩ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቶች በጥብቅ እንዲከታተሉና እንዲያስፈፅሙ ግልፅ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

ምክር ቤቱ ከዚህም በተጨማሪ በግጭቶቹ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ አካላት ወደነበሩበት እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቅርበት እንዲደግፍና የአካባቢው ሠላም ቀድሞ ወደነበረበት ሠላማዊ ይዞታው እንዲመለስ ከክልሉ መንግሥትና ከፀጥታ ሃይሉ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራት እንደሚጠበቅበት የአደራ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና በብጥብጡ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ የተጀመረውን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ ያልተቆጠበ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪው አቅርቧል፡፡

የክልሉን ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ በማስጠበቅ ረገድ ከማንም በላይና በፊት መላው የክልሉ ኗሪ ህዝብ ቀዳሚ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ በሁሉም የክልሉ አካባቢ የተፈጠረው አንፃራዊ ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል በየደረጃው ከሚገኙ ሠላም አስከባሪ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአደራ ጭምር አሳስቧል፡፡

የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት
ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም
አሶሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያና አፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ኮንፈረንስ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

• ኢትዮጵያ የሁላችንም እንድትሆን ሁላችንም በመተሳሰብ፤ በመቀራረብ መታገል አለብን፤ በጋራ ልንሰራም ይገባል፡፡

• ፈተናዎችን ማረም የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡

• አፋርና ኦሮሞ በአንድ ደም የተሳሰረ ህዝብ ነው፡፡ በአዋሽ ወንዝ ተጋምደዋል፡፡ ወደ ፊትም ግንኙነታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንክረን እንሰራለን፡፡

• ግጭቶችን በማስወገድ ሁሉም በነፃነት በፈለገበት ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እንዲለወጥ በጋራ መስራት ወሳኝ ነው፡፡

• የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለዘላቂ የጋራ ተጠቃሚነት ችግሮችን ለመፍታት የጀመረውን ስራ ቀን ከሌት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

• የአፋር ወንዶሞቻችን ወደ ቤታችሁ ወደ ቀያችሁ እንኳን በሰላም መጠያችሁ፤ ረመዳንን ከዚህ በኋላ ግማሹን በኦሮሚያ ግማሹን በአፋር እንፆማለን፡፡

• የረመዳን ወር የሰላም ወር፤ የእርቅ ወር፤ የፍቅር ወር፤ ከሁሉም በላይ ሰይጣን የሚታሰርበት ወር ሲሆን በዚህ በተቀደሰው ወር ግንኙነታችን እንዲጠናከር ቀን ከሌት እንሰራለን፡፡

• በሚቀጥሉት ጊዜያት አፋርኛና ኦሮሚኛ ተማምረን መድረኮቻችንን በአፋርኛ፣ በኦሮሚኛና በአማርኛ እናደርጋለን፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌስቡክ የጥላቻ ንግግሮችን እያስወገደ ነው...

ፌስቡክ በስድስት ወራት ውስጥ 3 ቢሊዮን የሀሰት አካውንቶችን ማጥፋቱን አስታወቀ፡፡ ከሰባት ሚሊዮን በላይ #የጥላቻ_ንግግሮችን በማስወገድም በታሪኩ ከፍተኛ የተባለለትን እርምጃ ወስዷልም ተብሏል፡፡

ፌስቡክ ጥላቻ ንግግርና በሀሰተኛ መረጃዎች እየቀረበበት ያለውን ወቀሳ ተከትሎ ለጀመሪያ ጊዜ ምን ያህል ሀሰተኛ አካውንቶችንና ልጥፎችን ጭምር እንዳጠፋ በግምገማዊ ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

የፌስ ቡክ ዋና አስተዳዳሪው #ማርክ_ዙከርበርግ በትላንተናው ዕለት ፌስቡክን ለመቆጣጠር በተለያየ መልኩ ተከፋፍሎ እንዲደራጅ ለቀረቡለት ጥሪዎች ችግሩን ለመፍታት አሰራሮችን ማዘመን ብቸኛው መፍትሄ ነው ሲል መልሷል፡፡

እንዲወገዱ የተደረጉት የሀሰተኛ አካውንቶች ሁሉም በሚባል ደረጃ በማኅበራዊ አውታር "ንቁ" ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ዕድል ከማግኘታቸው በፊት ካለፈው ጥቅምት እስከ መጋቢት ድረስ እርምጃው እንደተወሰደባቸው ተመልክቷል፡፡

ፌስቡክ እንዳለው ሪፖርቱ የሚያሳየው የኩባንያውን ግልጽነትና ለተጠቃሚዎቻችን ተጠያቂነታችንን እና ምላሽ ሰጭነታችንን ለማሳየትና እምነት ለመገንባት የሚያስችለን ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ የገል ገፅ-- በዚህ ቻናል ላይ የማይዳሰሱና ልዩ ልዩ መረጃዎችን የሚዳሰሱበት ነው፦
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-WeEn84b8FUyA
Audio
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምፅ👆

ቁጥራቸው 250 የሚሆኑ የጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምና ሳይንስ ኢንተርን ተማሪዎች ግቢውን ለቀው አንዲወጡ ከተደረገ ቀናት አልፈዋል። የጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምና ሳይንስ ኢንተርን ተማሪዎቹ እንደሚናገሩት ዩኒቨርስቲው በሆስፒታሉ ላይ ስላሉ ችግሮች ያነሳነውን ጥያቄ በ15 ቀን ውስጥ እመልሳለሁ ካለ በኃላ መልስ ስንጠብቅ ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሰማን ግቢውን ለቀን ወጥተናል ይላሉ።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርትና ስልጠና የፍኖተ-ካርታው ረቂቅ ዝግጅት ትግበራ የአንድ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

********************

የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት አማካሪ ካውንስል አባላት በተገኙበት የረቂቅ ትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅትና ትግበራ የአንድ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዴበታል፡፡

=================

የጥናቱን ውጤት መነሻ በማድረግ እስካሁን በተካዱ ህዝባዊ ውይይቶች ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ ወደ 3.5 ሚሊዮን ህዝብ በረቂቅ ፍኖተ-ካርታው ዝግጅት ዙሪያ እንዲወያዩ እና አስተያቶችን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ ተደርጎ በርካታ ግብአቶች የተሰባሰቡ መሆኑን ከሪፖርቱ ለማወቅ ተችሏል።

=================

እንደ ሪፖርቱ በጥናቱ ግኝት የተመላከቱና በህዝባዊ ውይይት ወቅት የተነሱ ምክረ ሃሳቦች ተብሎ ከቀረቡት፤

√ የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣
√ የአንደኛ ክፍል የመግቢያ ዕድሜ፣
√ የትምህርትና ሥልጠና እርከን፣
√ የትምህርትና ሥልጠና ቋንቋ፣
√ የትምህርት ምዘናና ፈተና፣
√ የመምህራን ምልመላና ሥልጠና ፣
√ የመምህራን የትምህርት ባለሙያዎች የትምህርትና ሥልጠና ዩንቨርሲቲ፣
√ አሃዳዊ የክፍል አደረጃጀት፣
√ የግብረገብ ትምህርት፣
√ የትምህርት ሕግ፣
√ የተማሪዎች ብሔራዊና በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመንግስትን ውሳኔ የሚጠይቁ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተነስተዋል።

****************************

በመድረኩ የ2012 ዓ.ም. ረቂቅ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታውን ተግባራዊ ለማድረግ የሽግግር ጊዜ መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ የሚቀርብበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጉጂና ጌዴዖ ዞኖች ዜጎችን በማፈናቀል፣ ንብረት በማውደምና በመግደል የተጠረጠሩ ከ270 በላይ ተጠሪጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢፌዲሪ ሠላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ የህግ የበላይነት ለማስከበሩ እየተደረገ ባለው ጥረት ወደ ቄያቸው የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጌዴዖ ዞን አስተዳደር ጋር በመሆን 15 የዓለምቀፍ ተቋማትና ረጅ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ዜጎችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ሂደት ያለበትን ደረጃ ለዓለምቀፍ ማኅበረሰብ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

Via #VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የብሪታንያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ የፊታችን ግንቦት 30 ስልጣን እንደሚለቁ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር በምትለያይበት ጉዳይ ላይ ከፓርላማ አባላት ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻላቸው ይታወሳል። የፍቺ ስምምነቱን ሦስት ጊዜ ፓርላማው አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ሰሞኑንም ስልጣን እንዲለቁ ወግ አጥባቂ የፓርላማው አባላትና ተቀናቃኛቸው ሌበር ፓርቲ ግፊት ሲያደርጉ ሰንብተዋል። ይህንንም ተከትሎ ቴሬዛ ሜይ ከደቂቃዎች በፊት ስልጣናቸውን የፊታችን ግንቦት 30 እንደሚያስረክቡ አስታውቀዋል።

Via #BBC/FBC/
@tsegabwolde @tikvahethiopia