ፎቶ👆ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሰሞኑን ግብር ያበሉበት አዳራሽ መግቢያ በር የቀድሞውና የአሁኑ ገፅታ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ያደርግ የነበረውን የግብር ቅናሽ አቆመ‼️
.
.
መንግስት ያገለጉሉ መኪናዎች ከውጭ ሲገቡ ያደርግ የነበረውን #የቀረጥ_ስሌት ቅናሽ ከትላንት ጀምሮ አቆመ።
መንግስት ከዚህ ቀደም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ላለማበረታታት እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል በተባለ የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ መመሪያም ያገለገሉ መኪናዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ ለመኪናዎቹ ቀረጥ ሲከፈል ፣ ከተሽከርካሪዎቹ ዋና ዋጋ ላይ የአገልግሎት ዋጋ ተብሎ እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ የይደረግ የነበረውን የቀረጥ ስሌት እንዲተው አድርጓል።
በዚህም መሰረት ከአሁን በሁዋላ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ የሚከፍሉት ቀረጥ የሚሰላው ከዋና ዋጋቸው ላይ መኪናው ላገለገለበት እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ ሳይሆን በዋና ዋጋቸው ይሆናል ማለት ነው። ይህም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡበት የነበረውን ማበረታቻ በእጅጉ ይጎዳዋል። የሀገር ውስጥ የመኪና ዋጋም ላይ ከፍተኛ ጭማሬን ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።
መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አዘው መመሪያው እስኪወጣ ያልገባላቸው አስመጪዎች በምን እንደሚታዩ ገና ግልጽ አልሆነም። መንግስት ይህን የታክስ አሰራር በማስቀረት ለነዳጅ ግዥ የሚያወጣውን ምንዛሬ ለመቀነስ እንዳሰበም ይነገራል።
Via #wazema

#update በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ የዝርፊያና ስርቆት ወንጀሎች ላይ ሲሳተፉ የነበሩ 194 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በትናትናው ዕለት በከተማዋ በሚገኙ ስምንት ክፍለ ከተሞች የፀጥታ አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በሰሩት የተቀናጀ ስራ የተለያዩ የስርቆት ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 194 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደገብርኤል ለfbc እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ሞተር ሳይክሎችን በመጠቀም በከተማዋ የተለያዩ የስርቆትን ዝርፊያ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ ናቸው።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ወንጀሉን ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 122 ታርጋ የሌላቸው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ። ከዚህ ባለፈም በከተማዋ ነዋሪዎች በተደረገ ጥቆማ 4 መኪና የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል።
ማህበረሰቡ ተጠርጣሪዎችና ህገ ወጥ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረገውን አስተዋፅኦ ያደነቁት ኮሚሽነሩ፥በቀጣይም መሰል ተግባራትን ለመከላከል ከፖሊስ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
Via #FBC

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሼር #Share የረመዳን ወርን በማስመልከት በአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት የተዘጋጀ አጭር ቪድዮ!
/ኢንጂነር ታከለ ኡማ/
"ይህ #በበረካ የተሞላ ወር ነው። ፍቅር፣ መተሳሰብ ፣አንድነት የረመዳን ባህሪያት ናቸው። እነዚህ ባህሪያት የሁል ጊዜ ተግባሮቻችን ይሁኑ! #ረመዳን_ከሪም" ኢንጂነር ታከለ ኡማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/ኢንጂነር ታከለ ኡማ/
"ይህ #በበረካ የተሞላ ወር ነው። ፍቅር፣ መተሳሰብ ፣አንድነት የረመዳን ባህሪያት ናቸው። እነዚህ ባህሪያት የሁል ጊዜ ተግባሮቻችን ይሁኑ! #ረመዳን_ከሪም" ኢንጂነር ታከለ ኡማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የተገነባ ህንጻ በሁለት ሰዓት ይፈርሳል እኛ ግን የማይፈርሰውን የአስተሳሰብ ለውጥ መገንባት ይገባናል፡፡" ፕ/ር ታከለ ታደሰ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት
"የ15 ደቂቃ የንባብ ልምድ ሀገርን ይለውጣል፡፡.....እኔ አንበሳ ስባል አልወድም ጅብ መሆን ነው ምኞቴ ምክንያቱም አንበሳ 20ሰዓት ይተኛል እኔ ግን 20 ሰዓት ማንበብ ፈልጋለሁ፡፡" ደራሲ ዘነበ ወላ
ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀው ሁለተኛው የንባብ ቀን የተላለፉ መልዕክታት ናቸው፡፡ የመርኃ-ግብሩ መሪ ቃል የንባብ ልምድ ለአስተሳሰብ ልህቀት የሚል ሲሆን ዝግጅቱን በበላይነት የሶሻል ሳይንስ የወላይትኛ ቋንቋ ት/ክፍል አዘጋጅቶት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የተሳተፉበት ነበር፡፡
Via #Bereket

ኦሮሞ❤️አፋር👆
የኦሮሞ እና አፋር ክልል ህዝቦች የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ ይካሄዳል።
በወንድማማችነትና አንድነት መድረኩ ላይ የሚሳተፉ በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የሚመራ ልዑክም በዛሬው ዕለት አዳማ ከተማ ገብቷል።
ልኡካኑ አዳማ ከተማ ሲደርሱም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በነገው ዕለት በሚካሄደው የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ወጣቶች እንዲሁም ከፍተኛ የክልል አመራሮችና ሃላፊዎች ይሳተፋሉ።
በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ይህ የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ የሁለቱን ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ትስስት በቀጣይነት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

#update ቦይንግ ኩባንያ አብራሪዎችን ይሰጡት የነበረውን ጥቆማ ትኩረት ሰጥቶ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋን ማስቀረት ይቻል እንደነበር ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ በተለይ የአሜሪካ አየር መንገድ አብራሪዎች ለኩባንያው በርካታ የማሻሻያ ሃሳቦችን አቅርበው ኩባንያው ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏቸዋል፡፡ ኩባንያው ችግሩን በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ አብራሪዎች ለማላከክ መሞከሩ ደሞ ይቅር የማይባል ነው፤ የፈጸመው ተግባርም አሳፋሪ ነው- ሲል ወቅሷል የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ማኅበር። ባለሙያዎች አውሮፕላኑ መሠረታዊ የንድፍ ስህተት እንዳለበት ያምናሉ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመብራት ነገር....
"...እኔ የምኖርበት አካባቢ መብራት ካጣን ዛሬ 6ኛ ቀናችን ነው። በየቀኑ የጥገና ሰራተኞች እየመጡ ይህንንማ አንችለውም እያሉ ይመለሳሉ። በጣም ሰዉ ሲመረው ገንዘብ አዋጥቶ ሰጣቸውና ሰርተነዋል መብራት ሲለቀቅ ይመጣላችኋል ብለው ሄዱ እስካሁን ሰዓት ድረስ መብራት የለንም። የምንበላውን እንኳ ማብሰል አልቻልንም።"

#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራን 28ኛ ዓመት የነፃነት በዓል አስመልክተው ለሀገሪቱ ህዝብና መንግስት የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ በመልዕክታቸውም ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በአሁኑ ወቅት የጋራ መተማመንና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በጥሩ ሁኔታ በመቀጠሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
በቀጣይም የሁለቱ እህትማማች ሀገራት ህዝቦች ግንኙነት የጋራ ፍላጎትና ጥቅምን መሰረት በማድረግ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍፍታት ቁርጠኛ አቋም ያላት መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ለኤርትራ ህዝቦች ሰላምና ብልፅግና መመኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Via #fbc

በጎሳ ግጭት ቢያንስ 11 ሰዎች ተገደሉ...
በኬንያ ውስጥ ኬሪዮ በተባለው አካባቢ ለሳምንታት ባጋጠመ የሽፍቶች ጥቃትና በጎሳ ግጭት ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ተፈናቀሉ።
በኬንያ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚገኘው ኬሪዮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የከብቶች ዘረፋ አጋጥሟል።
ረቡዕ እለት ምሽትም አንድ የጸጥታ ሰራተኛን ጨምሮ ሦስት የተገደሉ ሲሆን ባለፈው ሳምንትም ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ሦስት አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቀያቸውን እየተወ ከብቶቻቸውን በመያዝ ከአካባቢው እየሸሹ መሆኑም ተነግሯል። በሚያጋጥሙት ግጭቶች የተነሳም አራት ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን በርካታ መምህራንም በጥቃት ከሚታመሰው አካባቢ ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዲዘዋወሩ እየጠየቁ ነው።
በኬሪዮ አካባቢ ተደጋጋሚ የሽፍቶች ጥቃት አዲስ ነገር አይደለም። መንግሥትም ችግሩን በቁጥጥር ስር አውዬዋለሁ ቢልም በተደጋጋሚ እያገረሸ ነው። በአካባቢው በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉም የመንግሥት ባለስልጣናት ይናገራሉ።
Via #BBC

#update የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 21 የስራ አስፈጻሚ አባላትን መምረጡን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ በመንግስት ትይዩ በተዋቀረው ስራ አስፈጻሚ ውስጥ የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ምክትል መሪው አንዷለም አራጌን ጨምሮ 7 ሰዎች በአባልነት ተካተዋል፡፡ የፓርቲውን የዕለት ተዕለት በሚከታተለው ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ደሞ የፓርቲው ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ፣ ምክትላቸው ጫኔ ከበደ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ዋሲሁን ተስፋዬን ጨምሮ 14 የፓርቲው አባላት ተመርጠዋል፡፡
Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopi
Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopi
“ቪትዝ የተባለ መኪና ዋጋ በ70 ሺሕ ብር ገደማ፤ ኮሮላ በአንፃሩ 90 ሺሕ ብር ገደማ ሊጨምር ይችላል...”
.
.
የገቢዎች ሚኒስቴር ያገለገሉ ዕቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ከሚከፈልባቸው ቀረጥ በእርጅናቸው ምክንያት ይደረግ የነበረውን ቅናሽ አስቀርቷል። ውሳኔው በቀጥታ ከሚመለከታቸው መካከል ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አስመጪዎች ውሳኔው በይፋ እጃቸው አልደረሰም። አውቶ ኢቲ የተባለው የተሽከርካሪ መገበያያ ድረ-ገጽ መሥራች እና ባለቤት አቶ እዮብ ከበደ የገቢዎች ሚኒስቴር ውሳኔ ለገበያው "ዱብ እዳ ሆኗል" ሲሉ ይናገራሉ። "አገር ውስጥ መኪና ያስገቡ ሰዎች በአዲሱ ቀረጥ እንዲቀርጡ እየተደረገ ነው። ዛሬ ጉምሩክ ብትሔድ [መኪና አስመጪዎች] በአዲሱ ነው የምትስተናገዱት ተብለው መኪና እንዳይወጣ ተይዟል" የሚሉት አቶ እዮብ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ጭምር አዲሱ ውሳኔ ተፅዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ውሳኔውን በይፋ ካላሳወቃቸው የተሽከርካሪ ነጋዴዎች መካከል አንዱ አቶ ኑረዲን ሬድዋን ናቸው። "በስሚ ስሚ ነው የሰማንው። ፎቶ የተነሳ ወረቀት ምናምን እንጂ ሙሉ መረጃው ወይም መመሪያው የለም" ሲሉ ይናገራሉ።
አቶ ሬድዋን የጠቀሱት እና በገቢዎች ሚኒስቴር ምኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ግንቦት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ተፈርሞ የወጣ የተባለ ደብዳቤ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ሲዘዋወር ታይቷል። "የጸደቁ መመሪያዎች ስለመላክ" የሚል ርዕስ የተሰጠው ይኸው ደብዳቤ ለጉምሩክ ኮሚሽን የተላከ እንደሆነ ይጠቁማል። በደብዳቤው "ማንኛውም ያገለገለ ዕቃ ተሽከርካሪን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ቀረጥና ታክሱን ለመወሰን ምንም አይነት የእርጅና ቅናሽ አይደረግም።" የሚል ሐሳብ ተካቶበታል።
እስካሁን በነበረው በኢትዮጵያ መንግሥት አሰራር መሰረት የተሽከርካሪ ቀረጥ በመኪናው የሲሲ መጠን፣ በተመረተበት ጊዜ እና በተገዛበት ዋጋ ይተመናል። ከተመረተ አንድ አመት የሞላው ተሽከርካሪ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ከሚከፈለው ታክስ 10 በመቶ በእርጅና ሳቢያ ይቀነስለታል። ከተመረተ ሁለት አመት የሞላው ተሽከርካሪ የእርጅና ቅናሽ 20 በመቶ ነበር። ከሶስት አመት በላይ የሆናቸው ተሽከርካሪዎች ከሚከፈልባቸው ታክስ 30 በመቶ ቅናሽ ሲቀነስላቸው ቆይቷል።
ይኸ አሰራር በድንገተኛው ውሳኔ ሲቀየር በኢትዮጵያ ጎዳናዎች በብዛት የሚታየው ቪትዝ የተባለ መኪና ዋጋ በ70 ሺሕ ብር ገደማ፤ ኮሮላ በአንፃሩ 90 ሺሕ ብር ገደማ እንደሚጨምር አቶ እዮብ ተናግረዋል። አቶ እዮብ "ኢትዮጵያ ውስጥ ከድሮው በበለጠ ተሽከርካሪ የቅንጦት ነው የሚሆነው። አነስተኛ መኪና ከ500 ሺሕ ብር በታች አትገዛም። አንዲት ትንሽዬ መኪና 500 ሺሕ ብር ገዝቶ ሊጠቀም የሚችለው ምን ዓይነት ሰው ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ።አቶ ኑረዲን በበኩላቸው በዚህ ውሳኔ ምክንያት "አሁን ገበያ ላይ ያሉት መኪኖች ዋጋ ይጨምራል" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከአምስት አመት በላይ ያገለገሉ መኪኖች ወደ ገበያው እንዳይገቡ ልታግድ ትችላለች። የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች "የሚያስከተሉትን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን ለመቀነስ" በተዘጋጀ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ይመለከታቸዋል ካላቸው ጋር በትናንትናው ዕለት ውይይት አካሒዷል። አቶ እዮብ በኢትዮጵያ ተሽከርካሪ በመገጣጠም እና ያገለገሉትን ከውጪ አገራት ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ መሳተፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቼ እንሚቀርብ የተረጋገጠ ነገር የለም። አቶ እዮብ ግን በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ሒደቱ ተጠናቆ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል የሚል ግምት አላቸው።
Via #DW