TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለTIKVAH-ETH አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ቤተሰብ አባላት በሙሉ፦

"ሰብአዊነት ለሰላም መሰረት" እግር ጉዞ

የአለም ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን አስመልክቶ "ሰብአዊነት የሰላም መሰረት" በሚል መሪ ቃል መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የ5 ኪ.ሜ እግር ጉዞ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ከልዩ ልዩ ደማቅ ዝግጅቶች ጋር ይካሄዳል። ስለሆነም የዚህን የእግር ጉዞ ለማድመቅ የተዘጋጀውን ቲ-ሸርት በመግዛት እና በጉዞው ላይ በመሳተፍ የማህበሩ አጋር እና ደጋፊ እንዲሆኑ በገቢውም ሰብአዊ አገልግሎቱን እንዲያጠናክሩ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ዋጋው:- ቲ-ሸርት 130.00 ብር
ኮፍያ 50.00 ብር መሆኑን እያሳወቅን። ቲ-ሸርት እና ክፍያ በመግዛት ለመሳተፍ ለምትፈልጉ :-
1. ጋንዲ ሆ/ል አጠግብ በሚገኘው የኢትዮጽያ ቀይ መስቀል ማህበር
2. ፖሊስ ሆ/ል አካባቢ በሚገኘው አዲስ አበባ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ በስልክ ቁጥሮች 0911606337 , 0912055811, 0910122953, 0911642556, 0911448128 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

ቅድሚያ ለስብአዊነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባለፉት 6 አመታት ውስጥ ለሴቶች ኢንተፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጄክት 3 ቢሊየን ብር መለቀቁ ተሰማ፡፡

የአለም ባንክ እና ሌሎች የውጭ ለጋሽ ድርጅቶች ለፌደራል ከተሞች ስራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ስር ለሚገኘው የሴቶች ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጄክት ዌዴፕ ነው ብሩ የተለቀቀው፡፡

እርዳታው ከአለም ባንክ፣ ከጃፓን፣ ከጣሊያን እና ከሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች እንደፈሰሰ ሰምተናል፡፡ በዚህ ፕሮጀክትም ሴቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታት፣ የበዛ ችግሮችንም ለመፍታት ረድቷል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ ከተጀመረም አንስቶ እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ተመዝግበው የስራ ማስኬጃና ለኢንቨስትመንት እጃቸው ላጠረባቸው 3 ቢሊዮን ብር ብድር ተለቋል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም ባንክ ባገኘው ብድር በስድስት የክልል ከተሞች ወደ ስራ መግባቱን ከኤጀንሲው ተሰምቷል፡፡

Via #Sheger
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ👆ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሰሞኑን ግብር ያበሉበት አዳራሽ መግቢያ በር የቀድሞውና የአሁኑ ገፅታ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ያደርግ የነበረውን የግብር ቅናሽ አቆመ‼️
.
.
መንግስት ያገለጉሉ መኪናዎች ከውጭ ሲገቡ ያደርግ የነበረውን #የቀረጥ_ስሌት ቅናሽ ከትላንት ጀምሮ አቆመ።

መንግስት ከዚህ ቀደም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ላለማበረታታት እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል በተባለ የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ መመሪያም ያገለገሉ መኪናዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ ለመኪናዎቹ ቀረጥ ሲከፈል ፣ ከተሽከርካሪዎቹ ዋና ዋጋ ላይ የአገልግሎት ዋጋ ተብሎ እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ የይደረግ የነበረውን የቀረጥ ስሌት እንዲተው አድርጓል።

በዚህም መሰረት ከአሁን በሁዋላ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ የሚከፍሉት ቀረጥ የሚሰላው ከዋና ዋጋቸው ላይ መኪናው ላገለገለበት እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ ሳይሆን በዋና ዋጋቸው ይሆናል ማለት ነው። ይህም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡበት የነበረውን ማበረታቻ በእጅጉ ይጎዳዋል። የሀገር ውስጥ የመኪና ዋጋም ላይ ከፍተኛ ጭማሬን ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።

መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አዘው መመሪያው እስኪወጣ ያልገባላቸው አስመጪዎች በምን እንደሚታዩ ገና ግልጽ አልሆነም። መንግስት ይህን የታክስ አሰራር በማስቀረት ለነዳጅ ግዥ የሚያወጣውን ምንዛሬ ለመቀነስ እንዳሰበም ይነገራል።

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ የዝርፊያና ስርቆት ወንጀሎች ላይ ሲሳተፉ የነበሩ 194 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በትናትናው ዕለት በከተማዋ በሚገኙ ስምንት ክፍለ ከተሞች የፀጥታ አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በሰሩት የተቀናጀ ስራ የተለያዩ የስርቆት ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 194 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደገብርኤል ለfbc እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ሞተር ሳይክሎችን በመጠቀም በከተማዋ የተለያዩ የስርቆትን ዝርፊያ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ ናቸው።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ወንጀሉን ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 122 ታርጋ የሌላቸው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ። ከዚህ ባለፈም በከተማዋ ነዋሪዎች በተደረገ ጥቆማ 4 መኪና የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል።

ማህበረሰቡ ተጠርጣሪዎችና ህገ ወጥ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረገውን አስተዋፅኦ ያደነቁት ኮሚሽነሩ፥በቀጣይም መሰል ተግባራትን ለመከላከል ከፖሊስ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሼር #Share የረመዳን ወርን በማስመልከት በአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት የተዘጋጀ አጭር ቪድዮ!

/ኢንጂነር ታከለ ኡማ/

"ይህ #በበረካ የተሞላ ወር ነው። ፍቅር፣ መተሳሰብ ፣አንድነት የረመዳን ባህሪያት ናቸው። እነዚህ ባህሪያት የሁል ጊዜ ተግባሮቻችን ይሁኑ! #ረመዳን_ከሪም" ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የተገነባ ህንጻ በሁለት ሰዓት ይፈርሳል እኛ ግን የማይፈርሰውን የአስተሳሰብ ለውጥ መገንባት ይገባናል፡፡" ፕ/ር ታከለ ታደሰ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት

"የ15 ደቂቃ የንባብ ልምድ ሀገርን ይለውጣል፡፡.....እኔ አንበሳ ስባል አልወድም ጅብ መሆን ነው ምኞቴ ምክንያቱም አንበሳ 20ሰዓት ይተኛል እኔ ግን 20 ሰዓት ማንበብ ፈልጋለሁ፡፡" ደራሲ ዘነበ ወላ

ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀው ሁለተኛው የንባብ ቀን የተላለፉ መልዕክታት ናቸው፡፡ የመርኃ-ግብሩ መሪ ቃል የንባብ ልምድ ለአስተሳሰብ ልህቀት የሚል ሲሆን ዝግጅቱን በበላይነት የሶሻል ሳይንስ የወላይትኛ ቋንቋ ት/ክፍል አዘጋጅቶት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የተሳተፉበት ነበር፡፡

Via #Bereket
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሞ❤️አፋር👆

የኦሮሞ እና አፋር ክልል ህዝቦች የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ ይካሄዳል።

በወንድማማችነትና አንድነት መድረኩ ላይ የሚሳተፉ በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የሚመራ ልዑክም በዛሬው ዕለት አዳማ ከተማ ገብቷል።

ልኡካኑ አዳማ ከተማ ሲደርሱም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በነገው ዕለት በሚካሄደው የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ወጣቶች እንዲሁም ከፍተኛ የክልል አመራሮችና ሃላፊዎች ይሳተፋሉ።

በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ይህ የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ የሁለቱን ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ትስስት በቀጣይነት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቦይንግ ኩባንያ አብራሪዎችን ይሰጡት የነበረውን ጥቆማ ትኩረት ሰጥቶ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋን ማስቀረት ይቻል እንደነበር ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ በተለይ የአሜሪካ አየር መንገድ አብራሪዎች ለኩባንያው በርካታ የማሻሻያ ሃሳቦችን አቅርበው ኩባንያው ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏቸዋል፡፡ ኩባንያው ችግሩን በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ አብራሪዎች ለማላከክ መሞከሩ ደሞ ይቅር የማይባል ነው፤ የፈጸመው ተግባርም አሳፋሪ ነው- ሲል ወቅሷል የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ማኅበር። ባለሙያዎች አውሮፕላኑ መሠረታዊ የንድፍ ስህተት እንዳለበት ያምናሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia