አምቦ ዝግጁ❓
የኦሮሚያና የአማራ ክልል #የህዝብ_ለህዝብ መድረክ የፊታችን እሁድ በአምቦ ከተማ ይካሄዳል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒከሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ለfbc እንደገለጹት÷ ለውይይት መድረኩ በነገው ዕለት ከአማራ ክልል እንግዶቹ ወደ አምቦ ከተማ ያቀናሉ፡፡
በፍቼ በኩል ለሚገቡት ከአባይ ወንዝ ጀምሮ፣ በደብረ ብርሃን በኩል ለሚገቡት ደግሞ በየከተሞቹ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም አቶ አድማሱ ተናግረዋል፡፡
መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ባልተገባ ትርክት ህዝብን ለማጋጨት የተወጠኑ ሴራዎችን በማክሸፍና ወንድምና እህት ህዝቦች በጋራ በመቆም ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚያስችል መሆኑንም ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡
በውይይት መድረኩ ላይም የሁለቱ ክልልሎች ከፍተኛ አመራሮች የፌደራል መንግስትና ከሁለቱ ክልሎች የተወከሉ ተሳታፊዎች ይገኙበታል፡፡
የምስራቅ ሸዋ ዞንና የአምቦ ከተማም እንግዶቻቸውን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቃቸውን ገልጸዋል፡፡
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia