TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሱዳኑ ፕሬዝዳንት #ኦማር_ሀሰን_አልበሽር በሀገራቸው አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የአረቡን ዓለም የጸደይ አብዩት ለመኮረጅ የሞከሩ ናቸው አሉ። አልበሽር በስም #ያልጠቀሷቸውን ነገር ግን ጎጂ ያሏቸው ድርጅቶች ቀጠናውን ለማመስ እየሰሩ ነው ብለዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሱዳን-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች‼️

ሱዳን ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች፡፡ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት #ኦማር_ሀሰን_አልበሽር በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን፣ የፌዴራልና የግዛት መንግሥታዊ መዋቅሮችን በሙሉ መበተናቸውንም ተናግረዋል፡፡ የግዛት አስተዳዳሪዎችም ሙሉ በሙሉ ተነስተው #በወታደራዊ_መኮንኖች መተካታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀደም ብሎ የሱዳን ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ተቋም አልበሽር ከስልጣን እንደሚወርዱ አስታውቆ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሱዳን የሚታየው ሕዝባዊ አመጽ ትኩረቱን ፕሬዝዳንት አልበሽር ላይ አድርጓል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በኦምዱርማን ከተማ ወደ መንገድ #ለተቃውሞ በርካቶች ቢወጡም ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ ለመበተን ጥረት እያደረገ ነው፡፡

አልበሽር በንግግራቸው የሀገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀጣይ ምርጫ ለመወዳደር የሚያስችላቸውን የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝምም ጠይቀዋል፡፡ በሀገሪቱ እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች ሱዳንን #እንዳትረጋጋ ለማድረግ ያለሙ እንደሆኑም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፌያለሁ፤ በፌዴራል ደረጃ ያለውን የመንግሥት መዋቅር በትኛለሁ፤ የሁሉንም ግዛቶች አስተዳዳሪዎችም እንዲሁ ሽሬያለሁ›› ነው ያሉት አልበሽር፡፡ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ከሰዓታት በኋላ ደግሞ የወታደራዊና #የደኅንነት_ኃላፊዎች 18 የሀገሪቱን ግዛቶች እንዲመሩ ሾመዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia