#ጋምቤላ_ዩኒቨርሲቲ
በጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን ለዞኑ ወጣቶችና ነዋሪዎች ስራ ለመፍጠር እንዲያግዘው የጋምቤላ ዩኒቨርስቲን ጠየቀ። የሳይስንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በትናትናው ዕለት በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን የሚገኘውን አልዌሮ ሰው ሰራሽ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡
ፕሮፌሰር አፈወርቅ በከፍተኛ አሳ ምርት የሚታወቀውን ግድብ የጎበኙት ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር በመሆን ነበር፡፡ የአኙዋክ ዞን አስተዳዳሪ ለዩኒቨርስቲው የድጋፍ ጥያቄያቸውን ያቀረቡትም በጉብኝቱ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡
የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኡጁሉ ኦኮክ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ በጥናት ላይ በመመስረት ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው በበኩላቸው ዩኒቨርስቲዎችና ማህበረሰቡ በትስስር በጋራ በመስራት የሚታዩ ችግሮችን ተጋግዘው መቅረፍ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ከሳይስንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአልዌሮ ግድብ የመስኖ ቦዮችን በማልማት በአሁኑ ሰዓት በአከባቢው ሩዝ እና ጥጥ እየተመረተ ይገኛል፡፡
የመስኖ ቦዮቹ እስከ 10,000 ሄክታር መሬት የማልማት አቅምም አላቸው፡፡ ይህ ግድብ 2220 ሄክታር ስፋት እና 13 ሜትር ጥልቀት አለው፡፡ አልዌሮ ሰው ሰራሽ ግድብ በአልዌሮ ወንዝ ላይ የተሰራና በአኙዋክ ዞን አቦቦ ወረዳ የሚገኝ ነው፡፡
Via #epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia