TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአርባ ምንጭ...🔝

"ፀግሽ በአሁኑ ሰዓት በጎፋ ዛን ከመኖርያ ስፍራዎች ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ ለማድረግ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች እና አባቶች በጋራ በመሆን ወደጰስፍራው እያቀናን እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የአርባምንጭ ከተማን ነዋሪ አመስግንልን!!" #ፋሪስ ነኝ!

#ኢትዮጵያዊነትን ከመናገር በዘለለ #በተግባር ያገረጋገቹ የአርባምንጭ ከተማ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ ላደረጋቹት መልካም ተግባር በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮማንድ ፖስቱ ማሳሰቢያ!

በሀዋሳ ከተማ ችግር ፈጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት ሰላሙን ለመጠበቅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ሊተባበር እንደሚገባ የከተማዋ ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳሰበ፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በከተማዋ ጊዜያዊ የፀጥታ ሁኔታና ቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ዛሬ ከነዋሪዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ኮሎኔል ተክለብርሀን ገብረመድኅን “የሲዳማ ህዝብ የጠየቀው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ ነው “ብለዋል፡፡ ሆኖም ጥያቄውን በነውጥ ለማስመለስ መጣር ኢ-ህገመንግስታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሎኔሉ እንዳሉት ከጥያቄው ጋር ተያይዞ በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ወረዳዎች የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ የህብረተሰቡም ድጋፍ የራሱ ሚና ነበረው፡፡ ነውጡን የማይደግፉ እንዳሉ ሁሉ ከህብረተሰቡ መሀል #በተግባር ጭምር የደገፉና የተሳተፉ መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በነውጡ ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸውና በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪ ህብረተሰብ ሠላምና ደህንነት ሥጋት ላይ የሚጥሉ ወንጀሎች አሁንም እንዳሉ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ አስታውቀዋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በየክፍለ ከተማው መቋቋሙንና እስከ ቀበሌዎች በመውረድ ሕግ የማስከበርና የህብረተሰቡን ደህንነት የማስጠበቅ ተግባራት እንደሚያከናውን ገልጸዋል።

የከተማው ነዋሪ ህዝብም #በያለበት አካባቢ አጥፊዎችን አጋልጦና አሳልፎ በመስጠት ከፀጥታ አካላት ጋር ሊተባበሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ሰላሙን አጥብቆ በመጠበቅም የኮማንድ ፖስቱን ሥራ ማቃለል እንዳለበትም አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HAWASSA-08-07