TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ለዜጎች ሰላም እና ከጦርነት ጭንቀት እረፍት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተስፋ ጭላጭል " ሙሉ በሙሉ " ይከስም ይሆን ? የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል። በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል ብሏል። ዜጎችን ከ "ህወሓት"…
#ተመድ #አፍሪካ_ህብረት
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገልፀዋል።
ይህን የገለፁት ፤ ዛሬ ከሚካሄድ የፀጥታው ም/ ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።
በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ በጣም ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን የገለፁት ጉተሬዥ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ተማፅነዋል።
" ኢትዮጵያውያን ትግራዋዮች፣ አማራዎች፣ ኦሮሞዎች ፣ አፋሮች ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።
" አጠንክሬ የምጠይቀው በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የመንግስትና የህወሓት የሰላም ድርድር እንዲቀጥል ነው " ብለዋል።
ጉተሬዥ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሙሉ ዋስትና እንዲሰጠው ፤ በተጨማሪ የህዝብ አግልግሎቶች ተመልሰው እንዲቋቋሙ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ፤ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኢትዮጵያ እንደገና ወታደራዊ ግጭት መፈጠሩን የሚገልፁ ሪፖርቶች መስማታቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፤ ሁኔታውን እየተከታተሉ መሆኑንም አመልክተዋል።
ሊቀመንበሩ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ንግግሩ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት #የሀገሪቱን_ጥቅም_ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሂደትን ለመደገፍ ከሁሉም ወገን ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል።
ለዚህም ሁሉም ወገኖች ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia