TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ክፍል 1-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!

ሐሳብን በነፃነት መግለጽ የዴሞክራሲ ማዕከላዊ መርህ ነው፡፡ ይህ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ #መብት ደግሞ በይበልጥ እንዲተገበርና እንዲከበር ካደረጉ የታሪክ ክስተቶች፣ የቅርብ ጊዜውና ትልቁ ተጠቃሽ የማኅበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያ በባህርይው በማዕከላዊነት የሚደረግ የይዘት ቁጥጥር ባለመኖሩ፣ ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን ጉዳይ ያለማንም ገምጋሚነትና አርታኢነት በመቶ ሺሕዎች ለሚቆጠሩ ተጠቃሚ ተከታዮቻቸው በአነስተኛ ወጪ ያስተላልፋሉ፡፡ ይህም ሳንሱር እንዲጠፋ የሚደረገው ትግልና ክርክር እርባን አልባ እንዲሆን በማድረግ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እሳቤ፣ ይህን ያህል ይሄዳል ተብሎ ያልተጠበቀበት ደረጃ አድርሶታል፡፡

በዚህም ምክንያት የማኅበራዊ ሚዲያው ለዴሞክራሲ ልምምድ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ዕሙን ነው፡፡ ዛሬ አንድ ግለሰብ በስልኩ የሚያደርገው ግንኙነት እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ ሮናልድ ሬገን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሳሉ ያደርጉት ከነበረው እንደሚልቅ፣ ከ20 ዓመታት በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቢል ክሊንተን ያገኙት ከነበረው መረጃ የበለጠ አንድ የ13 ዓመት ታዳጊ በስልኩ እንደሚያገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መረጃ ኃይል ነውና በዚህ ዘመን በቀላሉ የሚገኝ መረጃ ለዴሞክራሲ ልምምድ ብሎም በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለመስጠት ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ከመሪዎቹ የሚገዳደር መረጃ እጁ ጫፍ ላይ የያዘ ዜጋ የመንግሥትት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ይችላልና፡፡ ከአንድ የዓለም ጫፍ የተከሰተን ጉዳይ  ማግኘትና መተንተን፣ ከዚያም ለውሳኔ መዘጋጀት ከኢንተርኔት ዘመን አስቀድሞ የደኅንነት ተቋማት ተግባር ነበር፡፡ አሁን ግን ከደኅንነት ተቋማት በማይተናነስ ደረጃ ማንኛውም ዜጋ መረጃ አለው፡፡ ይህም መንግሥት የሚወስዳቸውን ዕርምጃዎች እየተከታተሉ ለምን? እንዴት? ለማን ተወሰኑ? በሚሉ ጥያቄዎች ማረምና ተጠያቂነትን ማምጣት ይቻላል፡፡

ይሁንና በ1980ዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሬገንና ከ20 ዓመታት በፊት በተመሳሳይ ሥልጣን ላይ የነበሩት ክሊንተን ያገኟቸው የነበሩ መረጃዎች፣ አሁን ላይ ማንም ከሚያገኛቸው መረጃዎች የሚለዩበት አንድ ነጥብ አለ፣ ተዓማኒነት፡፡ ፕሬዚዳንቶቹ ለሚያስተላልፏዋቸው ውሳኔዎች እንዲረዷቸው መረጃዎቹን ከታማኝ ምንጮች ያገኛሉ፡፡ ለመተንተን ይረዳቸውም ዘንድ ከባለሙያዎች ጋር ይነጋገራሉ፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ከስልኮቻችን፣ በተለይም ከማኅበራዊ ሚዲያ የምናገኛቸው መረጃዎች ተዓማኒነታቸው አናሳ በመሆኑ የሚተላለፉ ውሳኔዎች አደገኛ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፡፡

ለዚህ የቅርብ ጊዜ ማሳያ የሚሆነው በማይናማር (በርማ) በሮሂንጂያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈጸመው #ግድያ ነው፡፡ በዚህች የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገር የሚኖሩና እንደ አገሪቱ ዜጎች የማይቆጠሩት የሮሂንጊያ ማኅበረሰብ እ.ኤ.አ. በ2016 በአገሪቱ ወታደሮች በተፈጸመባቸው ጥቃት ከአሥር ሺሕ በላይ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ ከ700 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ በዚህች አብዛኛው ማኅበረሰብ #ዜናም ሆነ ተያያዥ መረጃዎችን ከማኅበራዊ ገጾች በተለይም #ከፌስቡክ እንደሚያገኝ በሚገለጽባት አገር፣ በሮሂንጂያ ማኅበረሰብ ላይ የተፈጸመው በደል ‹በዓለማችን እጅግ በጣም የተጨፈጨፉ ሰዎች› በመባል እንዲታወቅ ያደረገ ጥፋት እንዲፈጸም ያደረገው #በፊስቡክ የሚለቀቅ መረጃ ነበር፡፡

በማይናማር የቡድሂስት መነኩሴ የሆኑት #አሺን_ዊራቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ፣ ይኼንን የተከታዮቻቸውን መብዛት ለበጎ ሳይሆን የውሸት መረጃዎችን በማሠራጨት ለበርካቶች #ሞት መንስዔ ሆነዋል፡፡ እኚህ የማይናማር ቢን ላዲን በመባል የተሰየሙት መነኩሴ ለተከታዮቻቸው ሙስሊም የሆነ አንድ ባለድርጅት አሠሪ፣ የቡድሂስት እምነት ተከታይ የሆነችን ሴት ደፍሯል የሚሉ የሐሰት ማስረጃ ቢያስራጩም ተጠያቂ አልሆኑም ነበር፡፡ ፌስቡክም በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግለትም እ.ኤ.አ. እስከ 2018 ድረስ ዕርምጃ ባለመውሰዱ ከፍተኛ ጥፋት እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች በተንሰራፉበት ዓለም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉና አብዛኛው ኅብረተሰብ ያልተማረ በሆነባቸው አገሮች፣ የማይናማር ዕጣ ፈንታ ሊደገምባቸው እንደማይችል ማረጋገጫ እንደሌለ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡ ይህ በተለይ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፈር ካልተበጀለት #አጥፊነቱ ሊከፋ ይችላልም ይላሉ፡፡
.
.
ክፍል ሁለት 6:00 ላይ🔄

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣቷን #በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ #ሞት ተፈረደበት‼️
.
.
አንዲት ወጣት ላይ አሰቃቂ ግድያ ፈፅሟል ያለውን ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ፍርድ ቤቱ ቅጣቱ የወሰነው በሐረማያ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ በሆነው #ጫላ አህመድ ሙመድ የተባለው ግለሰብ ላይ ነው።

የፍርድ ቤቱ ዳኛ አቶ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በግለሰቡ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በቤት ሠራተኝነት ሕይወቷን ትመራ የነበረች ወጣትን በግፍ መግደሉ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ነው።

ሟች በአወዳይ ከተማ ከባለቤቷ ጋር ተጋጭታ በሐረር ከተማ በቤት ሠራተኛነት ስትሰራም ነበር።

“ግለሰቡ ወጣቷን ለትዳር እንደሚፈልጋት በመግለፅ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት በመውሰድ ከአቅም በላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከፈፀመባት በኋላ ጆሮዋ አካባቢ እንደመታትና አንቆ እንደገደላት ታውቋል” ብለዋል።

“ወጣቷ ላይ ግድያ ከፈፀመ በኋላ ቤቱ ቆልፎባት ጠፍቷል” ያሉት ዳኛው፣የቤቱ ባለቤቶች ግለሰቡ በመጥፋቱ መጋቢት 24 ቀን 2010 ቤቱን ለሌላ ግለሰብ ለማከራየት ፈልገው በሩን ሲከፍቱ አስከሬኑን እንዳገኙት አስረድተዋል።

“የተዘጋውን በር ሲከፍቱ ያልጠበቁት መጥፎ ጠረን ያጋጠማቸው አከራዮች ዘልቀው ሲገቡ በቤቱ ወለል ላይ የፈረሰ የወጣቷን አስከሬን አግኝተነዋል” ሲሉም አብራርተዋል።

የሐረማያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወንጀሉ ወደ ተፈፀመበት ቤት በማምራት አስከሬኑን ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ ከተደረገለት በኋላ መቀበሩን ተናግረዋል።

“ግለሰቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የወሲብ ጥቃት ይፈጽሟል በሚል ጥርጣሬ በመኖሪያ ቤቱ በተደረገ ፍተሻ የሟች አልባሳት፣ የተለያዩ ሴቶች ፎቶግራፎች፣ ማሰቃያ ሰንሰለትና ሌሎች ወንጀል መፈፀሚያ ቁሶች ተገኝተዋል” ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን የሕክምናና የሰው ማስረጃዎች በመመልከት ቅጣቱን መበየኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱዓ እና ምህላ እየተደርገ ነው!

የሰዎች ህይዎት ላይ እየደረሰ ያለው በደል #እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች አስታወቁ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው #ግጭት ምክንያት በሰዎች ህይዎት እየደረሰ ያለው ጉዳት #ምህረት እንዲያገኝ ነው #ምህላ እና #ዱዓ እየተደረገ የሚገኘው። በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች #ሞት#መፈናቀል እና #መሰደድ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶች አውግዘዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥንቃቄ አድርጉ‼️ #ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ።…
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️

በህገ ወጥ ደላሎች #ነፃ የትምህርት አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ #ነብያት_ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት በሚገኙ ህገ ወጥ ደላሎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹ አግኝታችሁታል የተባለው ነፃ የትምህርት እድል #ሀሰተኛ በመሆኑ ቻይና ሲደርሱ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ባለፈም በቻይና አደገኛ እፅ #በማዘዋወር እና #ጫትን ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና በማስገባት በህገ ወጥ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በቻይና በዚህ አይነት ወንጀል መሳተፍ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ #ሞት ቅጣት በሚደረስ ፍርድ የሚያስቀጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 47 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ተብለው የእርምት ጊዜያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን የቀሪዎቹ ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዜጎች ከተመሳሳይ ችግር ለመውጣት የትምህርት እድል አግኝታችኋል ሲባሉ ከተቋማቱ በቂ መረጃ መሰብሰብ እንደሚገባቸውም ቃል አቀባዩ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ቻይና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የታሸጉ ነገሮችን ወደ ቻይና አድርሱልን ተብለው ሲጠየቁ ስለእቃዎቹ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

እነዚህ ወንጀሎች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት እንዳያበላሹም መንግስታቱ እርስ በርስ የተሳሰሩ ደላሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት የሄዱ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ቃለ አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በተያዘው ሳምንት 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና 1 ሺህ 15 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ 500 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሁም ከፑንትላንድ 517 ዜጎች እንደሚመለሱ አውስተዋል።

እነዚህን ዜጎች ከሀገራት ለማስመለስ ከአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ዓመት ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ #ገድለዋል በተባሉ 3 ወታደሮች ላይ #ሞት ሲፈርድ በአንድ ወታደር ላይ ደግሞ የ10 ዓመት እሥራት በየነ። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ባለፈው ዓመት የተፈጸመው የዚህ ግድያ ዓላማ #ዘረፋ ነበር። ትናንት ያስቻለው ፍርድቤቱ ከወታደሮቹ ጋር ተባብረዋል ከተባሉ ሁለት ሲብሎች አንዱ እድሜ ይፍታህ ሌላኛው ደግሞ የ8 ዓመት እሥራት ተፈርዶበታል። አራቱም ወታደሮች ማዕረጋቸው ተገፎ ከጦር ኃይሉም መሰናበታቸው ተዘግቧል።

Via ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ እና ኢራን ወዴት እያመሩ ነው

ኢራን ለሲአይኤ እየሠሩ ነበር ያለቻቸውን 17 ሰላዮች በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ይፋ አደረገች። ከነዚህ ገሚሱ #ሞት ተፈርዶባቸዋል ተብሏል። የኢራን የደህንነት ሚንስትር እንዳለው፤ ተጠርጣሪዎቹ ስለ ኒውክሌር፣ መከላከያ እና ሌሎችም ዘርፎች መረጃ እየሰበሰቡ ነበር። የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ክስ "ሀሰት ነው" ሲሉ አጣጥለዋል። በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ሳቢያ ሁለቱ አገራት እንደተፋጠጡ ነው። ትራምፕ ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ስምምነት ባለፈው ዓመት ወጥተው ኢራን ላይ የንግድ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሠላም ለራስ ነው!

ሶሪያ፣ሊቢያ፣የመን...በእነዚህ ሃገራት ሰዎች እንደዋዛ ህይወታቸውን ያጣሉ፤ በአሁን ቅጽበትና ባሉበት ስፍራ መኖራቸውን እንጂ የሚቀጥለው ትንፋሻቸው ይኑር አይኖር ማረጋጋጥ አይችሉም። በማንኛውም ስፍራና ጊዜ #ሞት አለ። ሰርቶ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት አይቻልም፤ ስራ የለም። ሃብት ማፍራት የሚባለው ነገር የማይጨበጥ ቅዠት ነው። እነዚህ ሃገራት #የተተረማመሱት ለፖለቲካዊ ነጻነቶች በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ነው ቢባልም አሁን ግን ፖለቲካዊ መብትና ነጻነት የሚባሉት ነገሮች ትርጉም አጥተዋል። አመለካከትን ማራመድ፣ መደራጀት፣ ሃሳብን መግለጽ፣ ምርጫ፣ የስልጣን ውክልና፣ መንግስት፣ የህግ የበላይነት የሚባሉት ነገሮች ማረፊያ መሬት አጥተዋል፤ ማረፊያቸው ሰላም ነበርና።

ሰላም ለሰዎች ተለጣፊ ነገር ሳይሆን መሰረታዊና የህልውና ጉዳይ ነው!

የፅሁፉ ባለቤት ኢብሳ ነመራ--TIKVAH-ETH ለዛሬው ቀን እንዲሆን መርጦ የወሰደው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dr.ABIY

"...እንድገደል የሚፈለግባቸው ጊዜዎች #በርካታ ናቸው!" የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

"...መስቀል አደባባይማ #የቅርብ ነው። ብዙ ጊዜ ሞት እንደዚሁ ዝም ብሎ እያየሁት አላየሁም እያለ ይሄዳል ለዚህ ነው #ሞት የማልፈራው እኔም። ብዙ ጊዜ እድገደለ የሚፈለግባቸው ጊዜዎች በጣም በርካታ ናቸው። ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል። ለምሳሌ ባለቤቴ ከመሄዷ በፊት ኢንሳን ለቅቄ እንደወጣሁ በየጊዜው ማታ ማታ በግቢያችን ድንጋይ ይወረወርብናል ስንወጣ ለመምታት፤ ሌላም ብዙ ሙከራዎች ተደርገውብን ያውቃሉ ግን ሞት #አልፈለገኝም እስካሁን እንግዲ አንድ ቀን ሲመጣ..." ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በሸገር ቅዳሜ ጨዋታ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከል የሚቻለው በሕግ እና በስርዓት ስንመላለስ ብቻ ነው' - ከፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተላለፈ መልዕክት!

በዚህ ፈታኝ የአደጋ ወቅት ህዝብን የሚያሸብሩ የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት ፣ በዜጎች ላይ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲደርስ ማድረግ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትል ወንጀል ነው።

መንግስት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመጣስ ተላላፊ በሽታዎችን የሚያሰራጭ፣ የህዝብን ጤና ለአደጋ የሚያጋልጥ፣ ህዝብን የሚያሸብር ሰው በወንጀል ህግ አንቀፅ 514 ፣ አንቀፅ 830 እና አንቀፅ 485 መሰረት እንዲሁም በምግብ ፣ በመድሃኒትና በጤና አዋጅ መሰረት ከቀላል እስራት እስከ #ሞት ድረስ ሊቀጣ ይችላል።

በአንዳንድ ሰው ስህተት ምክንያት ህዝብ እንዳይጠቃ የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] አስመልክቶ የህግ መተላለፎችን ሲመለከቱ 6044 ላይ በመደወል ጥቆማ ይስጡ። ይህን በማድረግ እራሶን፣ ወገኖንና ሀገሮን ይታደጉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ በአንድ ቀን 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በኬንያ 883 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰላሳ (30) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 465 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል የሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች #ሞት ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 24 ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ትላንት 15 ሰዎች ማገገማቸው ተገልጿል፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 167 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!

በደቡብ ሱዳን ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡ ተሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ በአንድ ቀን 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 231 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በማዳጋስካር የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!

በማዳጋስካር የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ቅዳሜ ምሽት መሞቱ የተገለጸው ግለሰብ የ57 ዓመት የህክምና ባለሞያ እንደሆነና ተጓዳኝ በሽታዎች እንደነበሩበት ተሰምቷል፡፡

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት ሃያ አንድ (21) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 304 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኪም ጆንግ ኡን ሀገር ሰሜን ኮሪያ ወጣቶቿን የደ/ኮሪያ መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳሰበች።

የሰሜን ኮሪያ መንግስት መገናኛ ብዙኃን ወጣቶች የደቡብ ኮሪያ መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ እንዳይጠቀሙ አሳስቧል፤ ወጣቶች የሰሜን ኮሪያን መደበኛ ቋንቋ እንዲገለገሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

ወጣቶች ከደቡብ ኮሪያ የተቀዱ የፋሽን፣ የፀጉር ስታይል እንዳይጠቀሙም እና ሙዚቃ እንዳያዳምጡ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጋዜጦች አዲስ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር።

ይህ የውጭ ጫናን ለማስቆም ያለመና ከባድ ቅጣት የሚያስከትለው አዲስ ሕግ አካል ነው።

ሕጉን ጥሰው የተገኙም ከእስራት እስከ #ሞት ድረስ ሊቀጡ ይችላሉ።

ሮዶንግ ሲንመን ጋዜጣ ወጣቶች የደቡብ ኮሪያን የፖፕ ባህል መከተላቸው የሚያደርስባቸውን ተፅዕኖ አስጠንቅቋል።

"በተዋበና በቀለም ባሸበረቀ ስክሪን ሰርስረው የሚገቡ ርዕዮተ ዓለሞችና እና ባህሎች የጦር መሣሪያ ከያዙ ጠላቶች ይበልጥ አደገኛ ናቸው" ብሏል ጋዜጣው።

አክሎም ፥ ወጣቶች ኮሪያ ላይ የተመሠረተ የፕዮንግያንግ ቋንቋን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስቧል።

የውጭ ተፅዕኖ ኪም የሚመሩት የሰሜን ኮሪያ ኮሚዩኒስት ሥርዓት ስጋት ተደርጎ ይታያል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን 'ኬ ፖፕ' [ደቡብ ኮሪያ መሰረቱ የሆነ የሙዚቃ ስልት] የሰሜን ኮሪያ ወጣቶችን አዕምሮ ጨምድዶ የያዘ 'የማይለቅ ካንሰር' ሲሉ መጥራታቸውን ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

ከደቡብ ኮሪያ፣ ከአሜሪካ ወይም ጃፓን ከፍተኛ መጠን ያለው ሙዚቃ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው የሞት ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህንን ሲመለከት የተያዘ ሰውም የ15 ዓመታት እስር ይተላለፍበታል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#Monkeypox

(Europe)

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአውሮፓ ሀገራት እጅግ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሶስት እጥፍ መጨመሩን አሳውቀዋል።

እንደ አሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (CDC) መረጃ እስካሁን በዓለም ደረጃ ከ5,000 የሚበልጡ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኬዞች ከ51 ሀገራት ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን በአውሮፓ ውስጥ ያለው ኬዝ ከአጠቃላዩ ኬዝ 90 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል።

እስካሁን ድረስ ባለው #ሞት ስለመመዝገቡ ሪፖርት አልተደረገም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢትዮጵያ ከፍላዋለች ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል " - ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ አሁን ላይ በስደት #በካናዳ_ሀገር የምትገኝ ሲሆን የወንድሟን ህልፈት በሰማችበት ወቅት እራሷን ስታ ሆስፒታል እንደነበረች ተናግራለች።

ድምፃዊት ትዕግስት ፤ የወንድሟን ህልፈት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ላሳየው ልዩ ክብር ምስጋናዋን አቅርባለች።

ወንድሟን እስላም ፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው አንድም ሳይለያይ አልቆሶ በክብር መቀበሩን የገለፀችው ትዕግስት ባየችው ነገር እንደተፅናናች ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እየጠፋ ያለው የሰው ህይወት ይቆም ዘንድና ሁሉም ወደ ፍቅር እንዲመለስ እያለቀሰች ተማፅናለች።

ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፦

" ... ወንድሜን ኢትዮጵያ ከፍላዋለች። እግዚአብሔር ይመስገን የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አክብሮታል።

እንደ ንጉስ በክብር ተቀብሯል።

ፌንት አድርጌ ሆስፒታል ነበርኩኝ ፤ ወንድሜ ለኔ ልጄ ነው ፤ የስደት ጓዴ ነው፤ ሁሉ ነገሬ ነው። የጀግና ሞት ነው የሞተው፤ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው።

የማስተላልፈው መልዕክት ፤ ወንድሜ እንዲሁ እንደ ንጉስ እንደተቀበረ  ፤ #ኢትዮጵያን እንዳለ እንደዘፈነ ፤ ኢትዮጵያን እንደወደደ የክብር ሞት ነው የሞተው የኢትዮጵያ ህዝብም ብድሩን መልሶለታል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ኢትዮጵያን ሰላም ያድርጋት።

ነገር ግን አንድ የሚያመኝ ነገር ወንድሜ እንዲህ እንደ ንጉስ ተከብሮ ተቀብሮ እንዲህ አንጀቴ ፣ ልቤ የተቆረጠ ፤ የሚያልቀው ህዝብ ፣ ምንም በማያውቀው ፣ ደጉ ባለሀገሩ ፣ ምስኪኑ የሚጨፈጨፈውስ ... ስለነሱ ነው መልዕክቴ።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደድሯችን #አንድ ልንሆን ይገባል፤ ሞት ሊቆም ይገባል። እኔ ወንድሜ በክብር ተቀብሮ እንደዚህ ያመመኝ ተዋግቶ በማያውቀው ተጋድሎ የሚሞተው ህዝብ ፤ ለእሱ ህዝብ ሞት ሊቆም ይገባል ነው መልዕክቴ።

ወንድሜማ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው ግን እንደዛም ሆኖ አንጀቴ ተቆርጧል። ማዲንጎ ኢትዮጵያን ነው ያሳየው እስላም፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው ሁሉ አልቅሶ ነው የቀበረው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው።

እባካችሁ ወገኖቼ ፣ ወንድሜ እንዲህ በክብር ተቀብሮ እንኳን አዝኛለሁ አንጀቴ ተቆርጧል፤ እያየች ልጇ የሚገደልባት እናት አባት ፣ እህት ወንድም የሚያልቅው እባካችሁ ... እባካችሁ ሞት ይቁም ኢትዮጵያ ላይ ፤ እግዚአብሔርን አምላክን ፍሩ ፤ ሁላችንም እንፍራ ወደ ፍቅር እንምጣ።

ማዲንጎ ይጠበቃል ዱብእዳ ነው የሆነብኝ፤ ቀኝ እጄ ነው የተቆረጠው ... በሰው ሀገር ፌንት ነው ያደረኩት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ አፅናናኝ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደዛ ሲሆንለት ሳይ ፣ ህዝቡ እንደዛ ሲወጣ አንድ አደረጋት ፣ #አንድ_ናት_ኢትዮጵያ እያለ ዘፍኖ ቀብሩ ላይ እስላም ፤ ክርስቲያን ሳይል ሁሉም አንድ ሆኖ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ አንድ ሆኖ ነው አልቅሶ የቀበረው እናም ይሄ ህዝብ ፍቅር ነው የሚያስፈልገው ፤ ለእሱ ስንል መታሰቢያነቱ ለወንድሜ ይሁን አንድ ያድርገን እባካችሁ ፤ #ሞት_ይብቃን !! "

(ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፤ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ላይ ለሚሰራጨው " ታዲያስ አዲስ " ለተሰኘው የሬድዮ ዝግጅት ከሰጠችው ቃል የተወሰደ)

@tikvahethiopia