TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢፍጧር

በኢትዮጵያ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለአራተኛ ጊዜ ነገ መጋቢት 18/2016 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የከናወናል።

የነገው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መሪ ቃል " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " የሚል ነው።

ዓላማው በታላቁ የረመዳን ወር ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ በጋራ ጾማቸውን እንዲያፈጥሩ በማስቻል የአብሮነትና የመተባበር መንፈስ ለማዳበር ነው ተብሏል።

በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የህዝበ ሙስሊሙ፦
- አንድነት የሚንፀባረቅበት ፣
- ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣
- ወረሐ ረመዷን ከመሆኑ አንፃር የቁርአን ክብር በአደባባይ የሚልቅበት እንደሚሆን ተነግሯል።

ዝግጅቱ ሀላል ፕሮሞሽንና ከነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢፍጧር በኢትዮጵያ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለአራተኛ ጊዜ ነገ መጋቢት 18/2016 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የከናወናል። የነገው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መሪ ቃል " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " የሚል ነው። ዓላማው በታላቁ የረመዳን ወር ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ በጋራ ጾማቸውን እንዲያፈጥሩ በማስቻል የአብሮነትና የመተባበር መንፈስ ለማዳበር ነው ተብሏል። በዚህ ታላቅ…
#ኢፍጧር

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን

- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ

- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ

- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ

- ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ #ኢፍጧር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

Photo Credit : Abel Gashaw

#ኢፍጧር #ረመዷን

@tikvahethiopia